ወልድ ተወለደልን!

ኧረ ይህች ቀን ምንኛ ድንቅ ናት!

በዓይን የማይታየው የተገለጠባት

የማይዳሰሰው በአካል የተገኘባት

አንድ አምላክ ፈጣሪ የተወለደባት

እርሱ ነው ተስፋችን የዓለም መድኃኒት

የሆነው ቤዛ ለሁሉ ፍጥረት!

ወልድ ተወለደልን መድኃኒዓለም

በከብቶች በረት በቤተ ልሔም!

‹‹ወደ ቤተ ልሔም እንሂድ!›› (ሉቃ.፪፥፲፭)

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን! ትምህርት እንዴት ነው? አሁንማ ፈተና ደርሷል አይደል ልጆች? ስለዚህ ጨዋታ ሳያታልላችሁ በትኩረት በማጥናት፣ ያልተረዳችሁትን በመጠየቅ፣ የግማሽ ዓመት ፈተናውን በጥሩ ውጠየት ለማለፍ ማቀድ አለባችሁ!

ታዲያ በቀደሙት ትምህርታችን ስለ ጾመ ነቢያትና ስለ ነቢያት አባቶቻችን ስንማማር ነበር፤ አሁን ደግሞ የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እናከብራለን፤

ሰባቱ ኪዳናት

ኪዳን በሰውና በእግዚአብሔር እንዲሁም በሰውና በሰው መካከል የሚመሠረት ስምምነት ነው።ዋናው ጉዳያችን እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር የሚያደርገው ቃል ኪዳን ነው። በባሕርይ የማይታየው እግዚአብሔር ምሕረቱ የበዛ ስለሆነ ብዙ ጊዜ ከፍጥረቱ ጋር መሐላ ፈጽሟል። ከብዙ አበው ጋርም ቃል ኪዳን አድርጓል። የማይታይና ኃያል እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር የሚያደርገውን ውል ለተመለከተ ቸር አምላክ እንዳለው ያውቃል።

የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን

ጾም፣ ጸሎት፣ ምጽዋትና ስግደት መንፈሳዊ ትጥቆችና ሥጋችንን ለነፍሳችን እንዲሁም ለእግዚአብሔር የምናስገዛበት መንገዶች ናቸው!

ልደተ አቡነ ተክለ ሃይማኖት

እንኳን ከጻድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ልደት በዓል በሰላም አደረሰን!

የልደቱም ነገር እንዲህ ነው!….

በዓለ ቅዱስ ገብርኤል

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? ሳምንቱ እንዴት አለፈ? በሰንበት ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ መንፈሳዊ ትምህርት እየተማራችሁ እንደሆነ ተስፋችን እሙን ነው፤መልካም! ለዛሬ ልንነግራችሁ የተዘጋጀነው ቅዱስ ገብርኤል ከእሳት ስላዳናቸው ሦስቱ ሕፃናትና እና ይህን በዓል አስመልክቶ ክብረ በዓል ከሚከበርባቸው ቅዱሳን መካናት መካከል አንዱ ስለ ሆነው ስለ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ነው!

ብርሃንህን ላክልን!

ድቅድቁ ጨለማ ተጋርዶ ከፊቴ
ሰላም ቢያሳጣኝ ካለሁበት ቤቴ
ነፍሴን ካስጨነቃት ጥንቱ ጠላቴ
በእስራቱ ኖርኩኝ ጸንቶ ፍርሃቴ
ከልጅነት ጸጋ ለይቶኝ ከአባቴ

ነገረ ማርያም በነገረ ድኅነት

ነገረ ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ትምህርት ሲሆን አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ ከምልአትነቱ ሳይጎድል ሰው ሆኖ በተገለጠ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ደንግል ማርያም በሰው ልጅ መዳን ላይ ያላትን ድርሻ (ምክንያትነት) የሚዳስስ ትምህርት ነው፡፡

በጸሎትህ ጠብቅ!

ከቅዱሳን አበው የሆነ ውልደትህ
የጸሎታቸው መልስ ለእናት ለአባትህ
ክብርህ እጅግ በዛ ተወደደ ሥራህ

ፍጥረት ያስደሰተ የውልደትህ ዜና
ገና ሕፃን ሳለህ የጀመርክ ምሥጋና፡፡
ጽድቅን ተጎናጽፈህ ወንጌል ተጫምተሃል
በጉብዝናህ ወራት መስቀሉን ሽተሃል፡፡

እንደ ጠዋት ጤዛ በምትረግፈው ዓለም
ልብህ ሳይሸነፍ ለምቾት ሳትደክም
ከትዳርህ ይልቅ ምንኩስናን መርጠህ
ከጫጉላ ቤት ወጥተህ በረኃ ተገኘህ፡፡

ፍቅር ግን እርሱ ነው!

ፍቅር ግን ምንድነው? ብዬ ስጠይቀው
ሁሉም ሊያብራራልኝ ሊገልጸው አቃተው!
ፍቅር ግን እርሱ ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወሰብእ የሆነው
ራሱን በመስቀል ለእኛ ሲል የሰዋው!