ብሥራተ ገብርኤል
ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጦ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ መወለድ ያበሠራት ዕለት ታኅሣሥ ፳፪ ‹‹ብሥራተ ገብርኤል›› ታላቅ በዓል ነው፡፡
ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጦ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ መወለድ ያበሠራት ዕለት ታኅሣሥ ፳፪ ‹‹ብሥራተ ገብርኤል›› ታላቅ በዓል ነው፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው፤ ‹‹ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ሆይ ተመራምሮ ለማይደረስበት ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል›› እንዲል፡፡ (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)
የከበረ ገድለኛ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም ደግሞ ዓመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጋግ ናቸው፤ እነርሱም በአክሱም ሀገር ሲኖሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ። አንደኛው ስሙ ገብረ ክርስቶስ ሲሆን ይህ ሁለተኛው ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው አባ ሳሙኤል ነው።
ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዕፅም ፍልሠታቸው በዚህ በቅዱስ ጎርጎርዮስ እንዲደረግ ሆነ፤ ይህም ታኅሣሥ ስድስት ቀን ነው፡፡ እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው። ከዚያም በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው እንዲሁ አከበሩበት።
ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተመረጡ የተመረጠች፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተከበሩ የተከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ መቅደስ የገባችበት ታኅሣሥ ፫ ቀን ‹‹በዓታ ለማርያም›› በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡
በተከበረች በኅዳር ፳፮ ቀን ንዑድ ክቡር ንጹሕ መነኰስ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ቅዱስ አባት የትውልድ ሀገሩ የራውዕይ በምትባል በስተ ምሥራቅ ባለች ሀገር ውስጥ ሲሆን በዚያም ስሙ ፍሬ ቡሩክ የሚባል አንድ ደግ ሰው ነበረ። ይህም ከክቡራን ሰዎች ወገን የሆነ ሰው እጅግ ሀብታምም የነበረ ሲሆን በሕጋዊ ጋብቻ ያጋቡት ቡርክት የሆነች ስሟ ዮስቴና የምትባል ሚስት ነበረችው። እርሷም በበጎ ምግባርና ሥራ የተጌጠች ናት። ይህችውም ደግ እናታችን በሕግ ተወስና ሳለች በጽኑዕ ገድል፣ በጾም በጸሎት በምጽዋትና በስገድትም ትጋደል ነበር።…
የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፤ አባቱንኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፤ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ ‹መርቆሬዎስ› ማለትም የአብ ወዳጅ ማለት ነው፤ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡
በኅዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡
ቅድስት ሐና የትውልድ ሐረጓ ከአብርሃም ዘር ነው፡፡ አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ያዕቅብን፣ ያዕቆብ ደግሞ ሌዊንና ዐሥራ አንድ ወንድሞቹን ወለዱ፡፡ ከዚህም በኋላ ሌዊ ቀዓትን፣ ቀዓት እንበረምን፣እንበረም አሮን ካህኑን ወለዱ፡፡ ቅዱስ አሮን አልዓዛርን፣ አልዓዛር ፊንሐስን እንዲህም እያለ እስከ ቴክታና በጥርቃ ይወርዳል፡፡…
ደብረ ቊስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወደደ ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ከሚፈልጉት ሸሽተው መጠጊያ ያገኙበት እንዲሁም ቅዱስ ገብርኤል ንጉሥ ሄሮድስ መሞቱን ለቅዱስ ዮሴፍ በሕልሙ የገለጸበት ስፍራ ነው፡፡ ‹‹የሕፃኑን ነፍስ የሚሹ ሞተዋልና፥ ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ›› እንዲል። (ማቴ.፪፥፲፱-፳)