የምርጫው ሂደት በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ ሁሉም በጸሎት እንዲያስብ ተጠየቀ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ6ኛ ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ የካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለፓትርያርክነት እጩ ሆነው የሚቀርቡ ጳጳሳትን ለመምረጥ ካህናትና ምእመናን ጥቆማ እንዲያደርጉ ከየካቲት 1 – 8 ቀን 2005 ዓ.ም. የሰጠው የጊዜ ገደብ መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
አስመራጭ ኮሚቴው በአንድ ሳምንት ውስጥ አከናወንኳቸው ያላቸውን ሥራዎች ባቀረበበት በዚሁ መግለጫ በርካታ ምእመናን ለቤተ ክርስቲያኒቱ 6ኛ ፓትርያርክ ሊሆኑ ይገባቸዋል ያሉትን አባት በአካል በመቅረብ እንዲሁም በፋክስ መልእክት በመላክ ጥቆማ መስጠታቸውን ገልጧል፡፡ ከካህናትና ምእመናን የተገኘው ጥቆማም ለአስመራጭ ኮሚቴው በግብአትነት የሚያገለግል ሲሆን ከየካቲት 9 -14 ቀን 2005 ዓ.ም. በወጣው የፓትርያርክ ምርጫ ሕገ ደንብ መሠረት አስመራጭ ኮሚቴው ለይቶ ከሦስት ያላነሱ ከአምስት ያልበለጡ እጩ ፓትርያርኮችን የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደሚያቀርብ መግለጫው አመልክቷል፡፡ የምርጫው ሂደት በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድም ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት ፤ ካህናትና ምእመናን እግዚአብሔርን በጸሎት እንዲጠይቁ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አስመራጭ ኮሚቴው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ምላሾችንም ሰጥተዋል፡፡
ከጋዜጠኞች ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ምርጫው ከሌሎች ተጽእኖ ምን ያህል የፀዳ ነው? የሚለውን ለቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ የአስመራጭ ኮሚቴው ጸሐፊ ምላሽ የሰጡ ሲሆን አስመራጭ ኮሚቴው ከሌሎች አካላት ተጽእኖ የጸዳና ራሱን ችሎ የተሰጡትን ኃላፊነቶች በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የአኀት ቤተ ክርስቲያንና የሲቪክ ማኅበራት ምርጫውን ለመታዘብ ይገኛሉ? የሚለውን ሲመልሱም ከአኀት ቤተ ክርስቲናት፤ ከአለም አብተ ክርስቲናት ምክር ቤት፤ ከአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፤ ከታዋቂ አገር ሽማግሌዎችና ከመንግስት አካላት በታዛቢነት እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
በስፋት ጥቆማ እየሰጡ የሚገኙት የአዲስ አበባ ካህናትና ምእመናን ናቸው፡፡ ሌሎቹ አህጉረ ስብከቶችስ? በሚል ለቀረበው ጥያቄም ሲመልሱ “በርቀት ምክንያት በአካል መቅረብ ያልቻሉ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም. አስመራጭ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ ላይ ሁለት ፋክስ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡ ፋክሶቹም 24 ሰዓት በመስራት ከአውሮፓና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ጥቆማዎችን እንደተቀበሉና በአካል ቀርበው ጥቆማቸውን የሚሰጡትንም በተዘጋጀው ቅጽ ላይ ሞልተው በታሸገው የጥቆማ መስጫ ሳጥን ውስጥ እያስገቡ ይገኛሉ” ብለዋል፡፡
በፓትርያርክ ምርጫ ሕገ ደንብ ላይ እጩ የሚሆኑትን አባቶች ከተለዩ በኋላ ከምእመናን የሚቀርቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ለመቀበል የ15 ቀናት የጊዜ ገደብ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን አስመራጭ ኮሚቴው የገለጸው በሦስት ቀናት ልዩነት ፓትርያርክ ሆነው የሚመረጡት አባት እንደሚታወቁ ነው፡፡ ይህ አካሔድ ከሕገ ደንቡ ጋር አይጋጭም? የሚለውንም ሲመልሱ “ከምርጫ ሕገ ደንቡ ጋር ተያዞ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጸድቆ ለአስመራጭ ኮሚቴው የተሰጠ ተጨማሪ ሕግ አለ፡፡ አስመራጭ ኮሚቴውን በሚያስመርጥበት ወቅት ኮሚቴው ሊሰሯቸው የሚገባውን ተግባራት ቋሚ ሲኖዶስ እየተከታተለ አስፈላጊውን ለውጥ ማድረግ እንደሚችል የተገለጸበት ሕግ ነው፡፡ ይህንን ሕግ ተከትሎ የድርጊት መርሐ ግብር አዘጋጅቶ ነው አስመራጭ ኮሚቴው ለቋሚ ሲኖዶስ ያቀረበው፡፡ ቋሚ ሲኖዶስ የቅዱስ ሲኖዶስም ምልዓተ ጉባኤ በሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት አስመራጭ ኮሚቴው ያቀረበውን የጊዜ ሰሌዳ ትክክል ነው ብሎ አጽድቆ ሰጥቶታል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ሕግ የማውጣትም ሆነ ሕግ የመለወጥ ስልጣን የለውም” በማለት የመለሱ ሲሆን ስለቀኑ ማጠር ሲያብራሩም ወደ አብይ ጾም የተቃረበ በመሆኑ ከዚያ በፊት ማጠናቀቅ እንደሚገባ ግንዛቤ ተወስዶ እንደተከናወነ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ከ53ቱም አህጉረ ስብከቶች ለመራጭነት ይገኛሉ ተብሎ ይፋ የተደረገው 800 መራጮች ብቻ ናቸው ፡፡ ነገር ግን ሲሰላ ከዚያ በላይ ስለሚሆኑ እንዴት ይታያል? በማለት ለቀረበው ጥያቄም በፓትርያርክ ምርጫው ላይ በመራጭነት የሚሳተፉ ሰዎች 800 ይሆናል የሚለውም እንደ መነሻ የተያዘ እንጂ የመጨረሻ ቁጥር ያለመሆኑን ያብራሩ ሲሆን የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትም ከጋዜጠኞች ለቀረቡት ጥያቄዎች ተጨማሪ ምላሽ በመስጠት ተሳትፈዋል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አቃቤ መንበረ ፓትርያርክን ጨምሮ 13ቱም አስመራጭ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል፡፡
ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም. አስመራጭ ኮሚቴው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የካቲት 18 ቀን አምስቱ እጩ ፓትርያርኮች ለምእመናን በይፋ እንደሚገለጹ፤ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ የተመረጡት ፓትርያርክ በመገናኛ ብዙሃን እንደሚገለጽና የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. በዓለ ሲመት እንደሚከናወን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
የካቲት 9 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስሰ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ6ኛ ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ የካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለፓትርያርክነትእጩ ሆነው የሚቀርቡ ጳጳሳትን ለመምረጥ ካህናትና ምእመናን ጥቆማ እንዲያደርጉ ከየካቲት 1 – 8 ቀን 2005 ዓ.ም. የሰጠው የጊዜ ገደብ መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አስመራጭ ኮሚቴው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ምላሾችንም ሰጥተዋል፡፡
ከጋዜጠኞች ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ምርጫው ከሌሎች ተጽእኖ ምን ያህል የፀዳ ነው? የሚለውን ለቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ የአስመራጭ ኮሚቴው ጸሐፊ ምላሽ የሰጡ ሲሆን አስመራጭ ኮሚቴው ከሌሎች አካላት ተጽእኖ የጸዳና ራሱን ችሎ የተሰጡትን ኃላፊነቶች በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የአኀት ቤተ ክርስቲያንና የሲቪክ ማኅበራት ምርጫውን ለመታዘብ ይገኛሉ? የሚለውን ሲመልሱም ከአኀት ቤተ ክርስቲናት፤ ከአለም አብተ ክርስቲናት ምክር ቤት፤ ከአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፤ ከታዋቂ አገር ሽማግሌዎችና ከመንግስት አካላት በታዛቢነት እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
በስፋት ጥቆማ እየሰጡ የሚገኙት የአዲስ አበባ ካህናትና ምእመናን ናቸው፡፡ ሌሎቹ አህጉረ ስብከቶችስ? በሚል ለቀረበው ጥያቄም ሲመልሱ “በርቀት ምክንያት በአካል መቅረብ ያልቻሉ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም. አስመራጭ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ ላይ ሁለት ፋክስ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡ ፋክሶቹም 24 ሰዓት በመስራት ከአውሮፓና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ጥቆማዎችን እንደተቀበሉና በአካል ቀርበው ጥቆማቸውን የሚሰጡትንም በተዘጋጀው ቅጽ ላይ ሞልተው በታሸገው የጥቆማ መስጫ ሳጥን ውስጥ እያስገቡ ይገኛሉ” ብለዋል፡፡
በፓትርያርክ ምርጫ ሕገ ደንብ ላይ እጩ የሚሆኑትን አባቶች ከተለዩ በኋላ ከምእመናን የሚቀርቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ለመቀበል የ15 ቀናት የጊዜ ገደብ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን አስመራጭ ኮሚቴው የገለጸው በሦስት ቀናት ልዩነት ፓትርያርክ ሆነው የሚመረጡት አባት እንደሚታወቁ ነው፡፡ ይህ አካሔድ ከሕገ ደንቡ ጋር አይጋጭም? የሚለውንም ሲመልሱ “ከምርጫ ሕገ ደንቡ ጋር ተያዞ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጸድቆ ለአስመራጭ ኮሚቴው የተሰጠ ተጨማሪ ሕግ አለ፡፡ አስመራጭ ኮሚቴውን በሚያስመርጥበት ወቅት ኮሚቴው ሊሰሯቸው የሚገባውን ተግባራት ቋሚ ሲኖዶስ እየተከታተለ አስፈላጊውን ለውጥ ማድረግ እንደሚችል የተገለጸበት ሕግ ነው፡፡ ይህንን ሕግ ተከትሎ የድርጊት መርሐ ግብር አዘጋጅቶ ነው አስመራጭ ኮሚቴው ለቋሚ ሲኖዶስ ያቀረበው፡፡ ቋሚ ሲኖዶስ የቅዱስ ሲኖዶስም ምልዓተ ጉባኤ በሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት አስመራጭ ኮሚቴው ያቀረበውን የጊዜ ሰሌዳ ትክክል ነው ብሎ አጽድቆ ሰጥቶታል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ሕግ የማውጣትም ሆነ ሕግ የመለወጥ ስልጣን የለውም” በማለት የመለሱ ሲሆን ስለቀኑ ማጠር ሲያብራሩም ወደ አብይ ጾም የተቃረበ በመሆኑ ከዚያ በፊት ማጠናቀቅ እንደሚገባ ግንዛቤ ተወስዶ እንደተከናወነ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ከ53ቱም አህጉረ ስብከቶች ለመራጭነት ይገኛሉ ተብሎ ይፋ የተደረገው 800 መራጮች ብቻ ናቸው ፡፡ ነገር ግን ሲሰላ ከዚያ በላይ ስለሚሆኑ እንዴት ይታያል? በማለት ለቀረበው ጥያቄም በፓትርያርክ ምርጫው ላይ በመራጭነት የሚሳተፉ ሰዎች 800 ይሆናል የሚለውም እንደ መነሻ የተያዘ እንጂ የመጨረሻ ቁጥር ያለመሆኑን ያብራሩ ሲሆን የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትም ከጋዜጠኞች ለቀረቡት ጥያቄዎች ተጨማሪ ምላሽ በመስጠት ተሳትፈዋል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አቃቤ መንበረ ፓትርያርክን ጨምሮ 13ቱም አስመራጭ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል፡፡
ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም. አስመራጭ ኮሚቴው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የካቲት 18 ቀን አምስቱ እጩ ፓትርያርኮች ለምእመናን በይፋ እንደሚገለጹ፤ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ የተመረጡት ፓትርያርክ በመገናኛ ብዙሃን እንደሚገለጽና የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. በዓለ ሲመት እንደሚከናወን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል አስተባበሪነት “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስስቲያን ተልዕኮ በሉላዊቷ ዓለም እና በዘመናዊው ማኅበረሰብ” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀረበ፡፡
ሕጎችን፤ መገናኛ ብዙኀንን በትጋት በመጠቀም ላይ እንደሚገኝና ፤በአንጻሩ ቤተ ክርስቲያን ከእነዚህ ተቋማትና ቴክኖሎጂዎች ራሷን በማግለል ትጠቃለች፡፡ይህንን ጥቃት ለመቀልበስ ቤተ ክርስቲያን ተገዳዳሪ ሉላዊ ኃይል ለማድረግ በተለያዩ አውዶች በተሰሚነትና በከፍተኛ አቅም ለማሳተፍ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ የጥናታቸውን ማጠቃለያ ያሉትን አቅርበዋል፡፡ ባቀረቡት ማጠቃለያም ክርስትና ሉላዊ ሆኖየሚቀጥለው የቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ማዕቀፈ እሳቤ ክርስቶሳዊ ማድረግና ማእቀፈ አሳቤውን የሚገልጽ አኗኗር ተግባራዊ ማድረግ፤ በማንኛውም የዘመናዊ ትምህርት የሚያድጉ የቤተ ክርስቲያን ልጆቿ በቂ የሆነ ክርስቲያናዊ ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ፤ ራሷን በመሠረታዊ ፍላጎቶች በመቻልና ከጥገኝነት የማላቀቅ ዕድሎችን ማስፋት፤በሴኩላር ሂዩማኒዝም ማዕቀፈ እሳቤ አመንጪነት የሚፈሰውን የመረጃ ጎርፍ የሚመጥን ክርስቲያናዊ መረጃ የመስጠት ዝግጅት ማጎልበት፤ ለምግባር እንቅፋት የሆኑ የዕለት ተዕለት ኑሮ ጥያቄዎችን በግልጽ በመመለስ ክርስቲያኖች የተበታተነ የግል ውሳኔእንዳይከተሉ መርዳት፤ የተቀደሰ ቤተሰብ አስተዳደርን በሚመለከት የሴኩላር ፍትሕ ዳኝነትን ከቤተ ክርስቲያን አንጻር እንዲያውቁ ማድረግና የመሳሰሉትን ጠቅሰዋል፡፡
ስድስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ለማስመረጥ የተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ ከምርጫው ሂደት ጋርና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ምርጫው ተከናውኖ፣ በዚሁ ዕለት ምሽት 12 ሰዓት ላይ፤ ውጤቱ ለሕዝቡ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡

ቄጤማ በመጎዝጎዝ ቀሳውስቱና መዘምራን በዝማሬ ፤ ምእመናን በሆታና በእልልታ አጅበው አቅራቢያቸው ወደሚገኘው ጥምቀተ ባህር አምርተዋል፡፡
አድርጎ ወደ ባሕረ ዮርዳኖስ ዮሐንስ ወዳለበት ቦታ ለመጠመቅ መጥቷል፡፡ ዮሐንስን አጥምቀኝ ማለቱ ለእኛ አብነት ለመሆንና ለቤተ ክርስቲያን ሥርዓትን ለመመሥረት ሲል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ፡፡ ዮሐንስ ወደ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሔዶ አጥምቆት ቢሆን ኖሮ ምእመናን ቀሳውስቱን እቤታችን ድረስ መጥታችሁ አጥመቁን እንጂ ወደ ቤተ ክርስቲያን አንሔድም ባሉ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የሌላት እንዳትሆን ሥርዓትን ለማስተማር ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ባሕር፤ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ” ብለዋል፡፡
እየተስፋፋች ነው፡፡ በዓሉ እጅግ የደመቀ ነው፡፡ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ እጅግ የደመቀ በዓል ስላዘጋጃችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ” በማለት ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን የግብጽ አምባሳደር፤ አንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ ክቡር አቶ ታደሰ በንቲ ንግግር አድርገዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የምትገኘው ታሪካዊቷና ተአምረኛዋ የደብረ ምጥማቅ የጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እሰከ 25 ሚሊዮን ብር በሚደርስ ወጪ የቤተ ክርስቲያኑን ሕንፃ እየተገነባ መሆኑን በአዲስ አበባ የተቋቋመው የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ገለጸ፡፡
በአዲስ አበባ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር አማረ አበበ ባቀረቡት ሪፖርትም ቤተ ክርስቲያኑ ከተሠራ ረጅም ዘመናትን ማስቆጠሩ፤ ጣሪያው ማፍሰሱ፤ በደርግ ዘመነ መንግሥት በነበረው ጦርነት አደጋ ስለደርሰበት፤ እንዲሁም ከተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የሚመጡ ምእመናን ቁጥር ከፍተኛ መሆኑና ቤተ ክርስቲያኑ በመጥበቡ ምክንያት በአዲስ መልክ ለመገንባት ታስቦ ወደ ሥራ ለመግባት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት የቤተ ክርስቲያኑ የመሠረት ሥራ ተጠናቆ ወደ ዋናው ግንባታ የተገባና ሥራውን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማከናወን እንዲቻል የምክክር መርሐ ግብር እንደተዘጋጀ ገልጸዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም. የሚካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ለዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚመክር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፣ የደቡብና ምዕራብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከትና የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በተለይ ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት “በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ እንዲሁም የሕግ ታሪሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት እንኳን ለ2005 ዓ.ም. የጌታችን የአምላካችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ፡፡” ካሉ በኋላ “በጌታችን ቤዛነት እንድን ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮአልና፤ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር በዚህ አውቀናል፡፡ እግዚአብሔር ከፍጡራን ሁሉ የተለየና ከአእምሮ በላይ የሆነ መለኮታዊ ኀይል ያለው አምላክ በመሆኑ የባሕርዩን ጥልቅነት በምልአት ማወቅ ፈጽሞ የማይቻል ቢሆንም እርሱ ራሱ በገለጸልን መጠን የተወሰኑ ነገሮችን እናውቃለን፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” ብሎ ምልአተ ፍቅሩን ካስረደ በኋላ በማስረጃ ሲያብራራ ቤዛ ሆኖ የሰውን ልጅ ያድን ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮአልና ፍቅሩን በዚህ አውቀናል” ይላል፡፡ እግዚአብሔር በልጁ መሥዋዕትነት ዓለምን ለማዳን ያደረገው ፍቅር ከሌላው ሁሉ የበለጠ በመሆኑ ልቆ ተነገረ እንጂ የእግዚአብሔር ፍቅር ከፍጡራን የተለየበት ጊዜ እንደሌለ ሁላችንም እናውቃለን፤ በስፋትም ልንገነዘብ ይገባልና፡፡” ብለዋል፡፡