ማኅበረ ቅዱሳን የህብር ሚዲያ መካነ ድር አገልግሎት ጀመረ
በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ
"multimedia.eotc-mkidusan.org" በሚል አድራሻ የተለቀቀው ይኸው መካነ ድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓት እምነትና ክርስቲያናዊ ትውፊት የጠበቁ የምስል ወድምጽ ስብከቶችና ተከታታይ ትምህርቶች፣ ዜማዎችና፣ መዝሙራት እንዲሁም የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጓሜና ንባብ ያስተላልፋል። ቅዱሳት ሥዕላትና የቅዱሳት መካናት ፎቶዎችም ከመግለጫ ጋር ይኖሩታል::(http://multimedia.eotc-mkidusan.org/video/?video=2364766985)
“ታሪክ የሚሠራው ከታሪክ ነው።”
በኪ/ማርያም
በአዲስ አበባ የስብሰባ ማዕከል አዳራሽ ጥር 01 ቀን 2003 ዓ.ም በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ‘ሕያው እውነት’ በሚል ርዕስ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የኦዲዮ ቪዥዋልና ሥነ ጥበባት ሥራዎች ማእከል አማካኝነት የተዘጋጀው መንፈሳዊ ፊልም ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተመረቀ።
የዚህን የፊልም ምረቃ ከሌሎች በሀገራችን ከተመረቁ ፊልሞች ለየት የሚያደርገው፣ ብዙ ሕዝብ ተገኝቶ የመረቀው ፊልም በመሆኑ ነው። የመርሐ ግብሩ መሪ ዲ/ን አባይነህ ካሴ ከዚህ በፊት በሌሎች የፊልም ምርቃት ላይ መገኘቱን አውስቶ ብዙዎቹ ፊልሞች ሲመረቁ የሚገኘው የሕዝብ /የተመልካች/ ብዛት እምብዛም ነው በማለት በመድረክ ላይ አስታውቋል።
በፊልሙ ምርቃት ላይ ሊቀመዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ ዝማሬ አቅርበዋል፣ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ “የተደፈኑትን ጉድጓዶች አስቆፈረ”ዘጸ 26፥18 በሚል ርዕስ ትምህርተ ወንጌል ሠጥተዋል። ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሲሳይ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሰብሳቢ የማኅበረ ቅዱሳንን መልእክት አስተላልፈዋል።
የማኅበሩን አመሠራረት ከመነሻው ጠቅሰው የአገልግሎቱን ዘርፈ ብዙነትም፤ ይህም አገልግሎት ከሀገራችን አልፎ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እንዲሁም በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በልዩ ልዩ የህትመት ውጤቶች፣ በራዲዮ፣ በመካነ ድርና የተለያዩ ዐውደ ርዕዮችን በማዘጋጀት ቤተ ክርስቲያንንና ሀገራችን ኢትዮጵያን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት አስተዋውቋል፤ በማስተዋወቅም ላይ ይገኛል። አሁንም አገልግሎቱን በማጠናከር በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን መንፈሳዊ ፊልም አዘጋጅቶ አቅርቦላችኋል በማለት ገልጸዋል።
በመቀጠል የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያንም የሥነ ጽሑፍና የሥነ ጥበብ ምንጭ እንደመሆኗ መጠን ያላት ታሪክና የሥነ ጽሑፍ ሀብት ገና በአግባቡ ያልተዳሰሰና ብዙ የሚያሠራ ነው። በዚህም ምክንያት ማንኛውም የፊልም ጸሐፊ የመረጠውን ጭብጥ የማቅረብ እድሉ እጅግ ሰፊ ነው። በዚህም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሰ/ማ/መ/ ማኅበረ ቅዱሳን የኦዲዮ ቪዥዋልና ሥነ ጥበባት ሥራዎች ማእከል ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችን ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በዋናነት በማንሳትና የሀገራችንን ባህልና ወግ የሚያንፀባርቅና በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሠራውን ደባ መንፈሳዊ ቀናኢነት፣ ሃይማኖትን ሥልጣኔን የአባቶቻችን ጽኑ ሀገራዊ ጀግንነት በጉልህ የሚታይበት መንፈሳዊ ፊልም ሰርቶ እነሆ ዛሬ ለምረቃ አቅርቧል።
ፊልሙም በእውነት ኢትዮጵያዊ በሆነ አቀራረብ የተዘጋጀ ሲሆን በተመስጦ በዘመናት መካከል ወደ ኋላ ወስዶ የቤተ ክርስቲያንን የሥልጣኔ በር ከፋችነት በማስረዳት በቁጭት የሚያነሳሳ፣ የሚያስተምር፣ ማንነትን የሚያሳውቅ፣ አርዓያና ምሳሌ እንዲሁም ማሣያ የሚሆን መንፈሳዊ ፊልም ነው።
ዝግጅቱም በታዋቂ አርቲስቶችና ከተለያዩ የቤተ ክርስቲያኗ አካላት የተውጣጡ ከ400 በላይ በሆኑ የቤተ ክርስቲያኗ ልጆች የተሠራ ነው። ‘ሕያው እውነት’ ፊልም አጠቃላይ ሥራው በአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት መሥራት የተቻለ ሲሆን የአርቲስቶቹንና የተሳታፊዎችን ነፃ ድጋፍ ሳይጨምር ከ285,000.00 ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት ለመረዳት ተችሏል።
በፊልሙ የሚገኘው ገቢ ማኅበሩ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩ ወጣት ተማሪዎችን ለማስተማርና ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት ማኅበራዊ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም የአባላትንና የምዕመናንን ጉልበትና እውቀት አስተባብሮ ገዳማትና አድባራትን በጊዜያዊነት እንዲረዱና በቋሚነት ከችግር እንዲወጡ ለማድረግ የሚውል ይሆናል።
በአጠቃላይ በዚህ ደረጃውን ጠብቆ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐትና ትውፊት ሣያፋልስ ቤተ ክርስቲያን ለሀገሪቱ ያበረከተችውን ሥልጣኔ እንዲያሳይ እንዲሁም የሀገራችንን ባህልና ወግ እንዲያንፀባርቅ ተደርጎ በተሠራው መንፈሳዊ ፊልም ላይ ለተሳተፋችሁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች፣ አርቲስቶች እንኳን ደስ! አላችሁ እያልኩ በቀጣይም ምክራችሁና የሙያ ድጋፋችሁ እንዳይለየን በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ፤ ከፊልሙ ጋር መልካም ቆይታ እንድታደርጉ እጋብዛለሁ። በማለት ንግግራቸውን ጨርሰው የፊልሙን ምርቃት አብስረዋል።
ፊልሙም ታይቶ ሲያበቃ በምረቃው ላይ በተገኙ ብጹአን አባቶች፣ ከቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት፣ ከፊልም ባለሞያዎችና አርቲስቶች አንዲሁም ከተሣታፊዎች መካከል አስተያየቶቻቸውን እንዲሰጡ እድሎች ቀርበው ሃሳብ ተሰጥቷል።
ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም መለሠ በመጀመሪያም ይህን ፊልም ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ላደረገ ለማኅበረ ቅዱሳን ምስጋናቸውን አቅርበው ከፊልሙም ያገኙትን ጭብጥ “ፊልሙ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ያለው ነው በማለት አስረድተዋል። ይህ ደግሞ ለአዲሱ ትውልድ ፈር ቀዳጅና አስተማሪ ነው። ወደ ኋላ ራሱን እንዲያስተውል የሚያደርግና ጽናቱን የሚፈትሽ በመሆኑ ፍጹም አስተማሪ ነው። ታሪክ የሚሠራው ከታሪክ ነው። ታሪክ ሕይወት አለውና በየዘመኑ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል። ታሪክ እንደ ሰው አካል ስላለው አካሉ እንደተጠበቀ መቆየት ይኖርበታል። አካሉን ማጉደል ተጠያቂ ያደርጋልና ከዚህ መንፈሳዊ ፊልም የተማርነው መንፈሳዊ የፍትሕ አሰጣጥ፣ ጥንታዊ እይታን ወደ ኋላ እንድናስብ፣ የሽማግሌዎች ሚና እንዲሁም ባህሎቻችን፣ ሥርዐቶቻችን ምን ያህል ጠንካራ እንደነበሩ እንደናስተውልም የሚያስተምር መንፈሳዊ ፊልም ነው። ታሪክ የአንድ ሕዝብ መለኪያ መነሻና መደረሻ እንደመሆኑ መጠን ራሱን ማየት የሚችለው ራሱን ሆኖ በመሆኑ ይህ ፊልም ለኢትዮጵያውያን ራሳችንን በመስታወት እንድናይ ያስቻለ ፊልም ነው። ዘመኑንም ራስን እንዳለ ጠብቆ ነገር ግን ወደኋላ ራሱን እንዲያይ ዘመኑን እንደ መስታወት ተጠቅሞ /ቴክኖሎጂውን/ በእድገት ላይ እድገት ለመጨመር መጀመሪያ ከራስ እድገት መነሣት ስለሚገባ ፍጹም አስተማሪ ነው።” በማለት በዚህ ፊልም መደሰታቸውንና ሌሎች ፊልሞች ተዘጋጅተው አማራጮች ቢኖሩ የቤተ ክርስቲያንንም ሆነ የሀገራችንን ታሪክ እንድናስተውል ያደርጋል ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል።
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር የሆኑት መምህር ደጉዓለም ካሣ ይህን ፊልም ያዘጋጁትን አካላት አመስግነው ይህ ፊልም በከተማ ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር በተለይም በገጠሪቷ የሀገራችን ክፍል የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን ያልተበረዘ እምነት የያዙ ምዕመናንን ቢያዩት ለዚህም የተለየ ቦታ ተፈልጎ ችግሩን የማያውቁት እነርሱ ናቸውና ፊልሙ ቢታይ በጣም ጥሩ ነው ብለዋል። በመጨረሻም በአቡጊዳ ትምህርት፣ በመልእክተ ዮሐንስ፣ በዳዊት፣ በዜማ፣ በቅኔ ብዙ ያልሄዳችሁ በዘመናዊ ትምህርት የበለጸጋችሁ ስትሆኑ የእናንተን አካሄድ በቤተ ክርስቲያን ቀጥ አድርጎ ያቆመ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን በማለት ንግግራቸውን ቋጭተዋል።
ከመንፈሳዊና ከሙያዊ አንጻር የተሰጡ አስተያየቶችን የመድረክ መሪው በይፋ በመቀበል በመጨረሻም ስፖንሰር ላደረጉ ድርጅቶች፣ በፊልሙ ለተሳተፉ አርቲስቶችና የተለያዩ እገዛዎችን ላደረጉ ሰዎች በብጹአን አባቶች የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን በብጹእ አቡነ ሚካኤል ቡራኬ የፊልሙ ምርቃት መርሐ ግብር ፍጻሜ ሆኗል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን።
የገና በዓል አከባበር በቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያናት
በተጨማሪ ኢአማንያን ይህንን መንፈሳዊ ቦታ ካዩ በኋላ ከሥላሴ ልጅነት አግኝተው ወደተለያዩ ዓለም ተመልሰዋል። ይህም በዓሉ ለአካባቢውና ለሀገራችን ብሎም ለውጭ ሀገር ዜጎች በየዓመቱ እንዲናፈቅ ሆኗል።
የጻድቁ የቅዱስ ላሊበላ ረድኤትና በረከትም ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን።
ማኅበረ ቅዱሳን የመጀመሪያ ፊልሙን ሊያስመርቅ በዝግጅት ላይ ነው፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን ኦዲዮ ቪዥዋልና የሥነ ጥበባት ሥራዎች ማእከል ‹‹ሕያው እውነት›› በሚል ርዕስ የተሠራው ፊልም በአዲስ አበባ የስብሰባ ማእከል ጥር 1 ቀን 2003 ዓ.ም ይመረቃል፡፡
በፋሲል ግርማ የተዘጋጀው ይህ ፊልም የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ ለሀገሪቱ ሥልጣኔ ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በዋናነት ያወሣል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሰራው ደባ፣ መንፈሳዊ ቀናዒነት፣ ሃይማኖትና ስልጣኔ የአባቶቻችን ጽኑ ሀገራዊ ጀግንነት ከታሪክ ማኅደር እየተቀዳ በጉልህ የሚታይበት ነው፡፡
ከ400 በላይ ሰዎች የተሳተፉበት ይህ ፊልም ከ250.000 ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፡፡ ወጪውን የትራንስፖርት፣ የምግብ፣ የቁሳቁስ፣ የአልባሳት፣ ወዘተ ወጪ ብቻ ሲሆን ታዋቂ ተዋንያን በፊልሙ ላይ የተወኑት ያለ ክፍያ ለአገልግሎት እንደሆነ አርቲስት ቶማስ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም የኪነጥበብ ምንጭ ቤተ ክርስቲያን ናት፤ ማንኛውም ክርስቲያን ሙያዊ አስራት ማቅረብ አለባቸው፡፡ የኪነ ጥበብና የሙያ ሰዎችም በሙያቸው ቤተክርስቲያንን ሊያገለግሉ ይችላሉ ብለዋል፡፡
አሁንም ሊሠራ ተጽፎ ኤዲቶሪያል ቦርድ የገባ እንዲሁም ገና እየተዘጋጀ ያለ ፊልም አለን በእነዚህ ፊልሞች የካሜራ ባለሞያዎች፣ ኤዲተሮች፣ ዳይሬክተሮች የራሳቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት የልጅነት ድርሻቸውን ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል ሊወጡ ይችላሉ ብለዋል፡፡
የፊልሙ ገቢም በዋናነት የማኅበሩን የስብከተ ወንጌል ለመደገፍ እንደሚውል የገለጹት አቶ ቶማስ በተጨማሪም የማኅበሩን ህንጻ ማስፈጸሚያ ገቢ እንደሚስያስገኝ ይታመናል፡፡ ስለሆነም ምዕመናን በፊልሙ እየተማሩ ትሩፋትን እንዲሠሩ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በማለት ይጠቀልላሉ፡፡
ፊልሙ በማኅበሩ የሀገር ውስጥ 39 ማእከላትና በውጭም በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ፣ በኬንያ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በግብጽ፣ በጅቡቲ፣ በኢየሩሳሌም፣ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስና በሌሎችም አገሮች ለእይታ ይቀርባል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ቴአትር ቤቶች በመከራየትና በቤተክርስቲያን ልዩ ልዩ መድረኮች ለዕይታ ይበቃል፤ በመጨረሻም በዲቪዲና ሲዲ ታትሞ ለገበያ ይቀርባል፡፡
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል
የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን አስመልክቶ በመካነ ድር አድራሻችን እንዲሁም በስልክ ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቁ ይኽንን አስመልክተን ከማኅበረ ቅዱሳን የሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ከሆኑት ከዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ጋር ጥቂት ቆይታ አድርገን የሚከተለውን ምላሽ አግኝተናል መልካም ንባብ፡፡
ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ፡- ከላይ የጠቅስናቸው ሦስቱም በዓላት በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐት መሠረት ቅዳሴያቸው በመንፈቀ ሌሊት ይከናወናል፡፡ ከቆረብን በኋላም ፆሙን በመበል፣ በመጠጥ፣ በፍፁም መንፈሳዊ ደስታ ማሰናበት እንደሚገባን በመጽሐፍ ላይ ተጠቅሷል፡፡ መንፈሳዊ ደስታ ሲባል ግን ጥቅም (ረብ) የሌለው ነገር በመናገር ማክበር እንደሌለብን (እንደማይገባን) የተረዳ ነው፡፡ አንድ ሰው መብል መጠጥ በማብዛት ሊደሰት አይገባውም፤ በእውነት ሌሎችም በዚህ አልተጠቀሙም፡፡ እህልን ልንሄድበት ልንቆምበት ነው እንጂ ልንሰናከልበት አልተሰጠንምና፡፡
አማርኛ መካነ ድር፡- በመጨረሻም የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ?
የሃይማኖት አባቶች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን ወክለው ይቅርታ አቀረቡ።
መ/ር መንግስተአብ አበጋዝ
የአራት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን የይቅርታ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት አቀረቡ።
«ብፁዓን ገባርያነ ሠላም፥ እስመ እሙንቱ ውሉደ እግዚአብሔር ይሰመዩ።
የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና» ማቴ 5፥9