ዕረፍተ ሕፃን ቂርቆስ ወቅድስት ኢየሉጣ

በሮም ግዛት በሚገኝ አንጌቤን በሚባል ሀገር በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በክርስትና ሃይማኖት እና በበጎ ምግባር ጸንታ ትኖር የነበረች ኢየሉጣ የተባለች ደግ ሴት ነበርች፡፡ እርሷም ቂርቆስ የተባለ በሥርዓት ያሳደገችው ሕፃን ልጅ ነበራት፡፡ በዚያን ዘመን እለእስክንድሮስን የተበላ አረማዊ መኰንን  ነበር፤ ይህችም ቅደስት ከልጇ ጋር ከሮም ወደ ጠርሴስ ተሰደደች፡፡…

በዓለ ልደቱ ለአቡነ አረጋዊ

የጻድቁ የአቡነ አረጋዊ አባት ይስሐቅ እናቱም እድና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የተባረከውን ልጅ ሰጣቸው፤ይህም የሆነው በጥር ፲፬ ቀን ነው፡፡

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ታሪኩ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈ እንዲህ ይነበባል፡፡…

ግዝረቱ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪት ሕግ የሆነውን ግዝረት የፈጸመበት ዕለት ጥር ስድስት ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋ ግዝረትን ተቀበለ፣ ለአባቶች የተሰጠውን ቃልኪዳን ይፈጽም ዘንድ›› ብሎ መስክሯል፡፡ (ሮሜ ፲፭፥፰)

መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን

መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፤ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ የተዘጋጅ ነው፡፡ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጽሔቱን ያንብቡ!

ጾመ ገሀድ

የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ አዝዘዋል፤ ይህም ጾመ ገሀድ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።

በእንተ ልደቱ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት

የዳሞት አውራጃ ገዚ ሞተለሚ በነበረበት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ በኢቲሳ መንደር ካህኑ ጸጋዘአብና እግዚኀረያ በትዳር ተወስነው ይኖሩ ነበር። ጸጋ ዘአብ በክህነቱ እግዚኀረያ በደግነቷና በምጽዋት ጸንተው በመኖራቸው በሕጉና በሥርዓቱ ለሚኖሩት ቀናዒ በመሆኑ እግዚአብሔር አምላክ ጎበኛቸው። ሃይማኖታቸውን የሚረከብ፣ እንዳባቱ ጸጋዘአብ የሚባርክ የአብራካቸውን ክፋይ ሊሰጣቸው ወደደ።

ብሥራተ ገብርኤል

ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጦ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ መወለድ ያበሠራት ዕለት ታኅሣሥ ፳፪ ‹‹ብሥራተ ገብርኤል›› ታላቅ በዓል ነው፡፡

ዕረፍቱ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

የከበረ ገድለኛ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም ደግሞ ዓመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጋግ ናቸው፤ እነርሱም በአክሱም ሀገር ሲኖሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ። አንደኛው ስሙ ገብረ ክርስቶስ ሲሆን ይህ ሁለተኛው ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው አባ ሳሙኤል ነው።

ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ

ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዕፅም ፍልሠታቸው በዚህ በቅዱስ ጎርጎርዮስ እንዲደረግ ሆነ፤ ይህም ታኅሣሥ ስድስት ቀን ነው፡፡ እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው። ከዚያም በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው እንዲሁ አከበሩበት።