በዓታ ለማርያም

ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተመረጡ የተመረጠች፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተከበሩ የተከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ መቅደስ የገባችበት ታኅሣሥ ፫ ቀን ‹‹በዓታ ለማርያም›› በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡

ዕረፍተ አቡነ ሀብተ ማርያም

በተከበረች በኅዳር ፳፮ ቀን ንዑድ ክቡር ንጹሕ መነኰስ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ቅዱስ አባት የትውልድ ሀገሩ የራውዕይ በምትባል በስተ ምሥራቅ ባለች ሀገር ውስጥ ሲሆን በዚያም ስሙ ፍሬ ቡሩክ የሚባል አንድ ደግ ሰው ነበረ። ይህም ከክቡራን ሰዎች ወገን የሆነ ሰው እጅግ ሀብታምም የነበረ ሲሆን በሕጋዊ ጋብቻ ያጋቡት ቡርክት የሆነች ስሟ ዮስቴና የምትባል ሚስት ነበረችው። እርሷም በበጎ ምግባርና ሥራ የተጌጠች ናት። ይህችውም ደግ እናታችን በሕግ ተወስና ሳለች በጽኑዕ ገድል፣ በጾም በጸሎት በምጽዋትና በስገድትም ትጋደል ነበር።…

ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ

የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፤ አባቱንኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፤ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ ‹መርቆሬዎስ› ማለትም የአብ ወዳጅ ማለት ነው፤ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡

በዓሉ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል

በኅዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡

ዕረፍተ ቅድስት ሐና

ቅድስት ሐና የትውልድ ሐረጓ ከአብርሃም ዘር ነው፡፡ አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ያዕቅብን፣ ያዕቆብ ደግሞ ሌዊንና ዐሥራ አንድ ወንድሞቹን ወለዱ፡፡ ከዚህም በኋላ ሌዊ ቀዓትን፣ ቀዓት እንበረምን፣እንበረም አሮን ካህኑን ወለዱ፡፡ ቅዱስ አሮን አልዓዛርን፣ አልዓዛር ፊንሐስን እንዲህም እያለ እስከ ቴክታና በጥርቃ ይወርዳል፡፡…

ልደቱ ለቅዱስ ማርቆስ

ቅዱስ ማርቆስ ትውልዱ ዕብራዊ ነው፤ ቤተሰቦቹ ግን ይኖሩ የነበሩት በሰሜን አፍሪካ ሲረኒካ  (ቀሬና) በተባለችውና በዛሬዋ ሊቢያ ምዕራባዊ ጠረፍ በተቆረቆረችው ደማቅ ነበር፡፡ ነገር ግን የሰሜን አፍሪካ  ዘላን ጎሳዎች የሆኑት በርበሮች በየጊዜው በከተማዋ ጥቃት እየነሰዘሩ ሀብት ንብረታቸውን እየዘረፉ ስላስቸሯቸው እናቱ ማርያምና አባቱ አርስጦቡሎስ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢየሩሳሌም በመመለስ ቤት ሠርተው ተቀመጡ፡፡…

ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ

የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤ ከዚያም ዲያቆን ሆኖ ተሾሟል፤ ይህም ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡

ዕረፍቱ ለሊቀ ጳጳስ አባ ድሜጥሮስ

ቅዱስ ድሜጥሮስ የእስክንድርያ ዐሥራ ሁለተኛ ጳጳስ ከመሆኑ በፊት የቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ያልነበረው በግብርና ሥራ የሚተዳደር ሰው ነበር፡፡አባቱ ደማስቆ ወይም እንድራኒቆስ አጎቱ ደግሞ አርማስቆስ ወይም አስተራኒቆስ ይባላሉ፡፡ ሁለቱም በዘመነ ሰማዕታት ከኢየሩሳሌም ርቀው በባዕድ ሀገር በፋርስ ባቢሎን በስደት ለረጅም ዘመናት ይኖሩ ነበር፡፡ በዚህ የስደት ዘመናቸው ከሁለቱ (ደማስቆና አርማስቆስ) በስተቀር በሀገሩ የሚኖሩት አሕዛብ ነበሩ፡፡…

ክብረ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ ፻ (መቶ) ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዕረፍታቸው እንዲሁም ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት በሀገራችን ኢትዮጵያ በድምቀት ይከበራል፡፡

ጼዴንያ ማርያም

የሁሉ አምላክን በማኅፀኗ የተሸከመችው ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም በሥዕሏ ወዝ ብዙ ሕሙማንን ትፈውሳለች፡፡ ከቅዱሳን ልብስና ጥላ የእርሷ ሥዕል ይከብራልና በየዓመቱም መስከረም ፲ ቀን ቤተ ክርስቲያናችን ከእመቤታችን ፴፫ቱ በዓላት ውስጥ አንዱ አድርጋ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡