ነቢዩ ሶምሶን

ሶምሶንም “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት” አለ፤ ተጎንብሶም ምሰሶቹን በሙሉ ኅይሉ ገፋ፤ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው በዙ። ወንድሞቹም የአባቱ ቤተ ሰቦችም ሁሉ ወረዱ፤ ይዘውም አመጡት በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ቀበሩት፤ እርሱም በእስራኤል ላይ ሃያ ዓመት ፈረደ።

በዓለ ደብረ ቁስቋም

በከበረች በኅዳር ስድስት ቀን የምናስበው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ከመድኃኒዓለም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር ከስደት መመለስ እንዲሁም በቁስቋም ተራራ መገኘት ታላቅ በዓል ነው፡፡

ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ

ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ፣ የዜማ ደራሲና ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ድንቅ ተጋድሎን ፈጽሞ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ግንቦት ፲፩ የከበረች እንደመሆኗ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡

ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ

ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለ ታላቅና ክቡር የሆነ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ የምስክርነት ፍጻሜ የሆነበት ቀን ሚያዚያ ፳፫ የከበረ ነው፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ አባት ቀጰዶቅያ አገር ይኖር የነበረ አንስጣስዮስ የተባለ መስፍን ነው፡፡ እናቱም ቴዎብስታ የተባለች ፍልስጥዔማዊ ነበረች፤ የዚህ ቅዱስ አባትም የሞተው በልጅነቱ ስለዚህም ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ አሳደገው፡፡ መስፍኑም በጦር ኃይል አሰለጠነው፡፡ ሃያ ዓመትም በሞላው ጊዜ መስፍኑ የ፲፭ ዓመት ልጁን ሊያጋባውና ሀብቱን ሊያወርሰው ድግስ ደገስ፤ ነገር ግን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አልመረጠውምና  የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ኀዘኑን ከጨርሰ በኋላ ወደ ቤሩት ሀገር ሄደ፡፡ በዚያም ደራጎንን ያመልኩና ሴት ልጆቻቸውን ይገብሩለት ነበር፤ ሰማዕቱም ደራጎኑን በኃይለ መስቀል ድል ነሥቶት ገድሎታል፤ ሕዝቡንም ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልሷቸዋል፡፡

በዓለ ጥምቀት

እንኳን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት ለበዓለ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

የጥምቀት ትርጉም፡- ጥምቀት የሚለው ቃል “አጥመቀ” (አጠመቀ) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በተከማቸ ውሃ ውስጥ መነከር፡ መዘፈቅ፡ ገብቶ መውጣት ማለት ነው። ጥምቀት በፅርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒ፣ በግእዝ አስተርእዮ፣ በአማርኛ መገለጥ ይባላል፡፡ ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጥለቅ ማለት ነው፡፡ ምሥጢረ ጥምቀት በምሥጢራዊ ፍቺው በተጸለየበት ውሓ (ማየ ሕይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብሎ የመውጣት ሂደት ነው (ማቴ ፳፰፡፲፱)።

ምሥጢር ማለት የተደበቀ፣የተሸሸገ፣ለሁሉ የማይገለጥ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ለአመኑት እንጅ ላላመኑት የማይነገር በመሆኑና በሚታይና በሚሰማ አግልግሎት በኢየሱስ ክርስቶስ ማይ ገቦ ተጠምቀን የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን እንገኛለን፤ ይህን በእምነት የምንቀበለው ስለሆነ ነው፡፡ ካህኑ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ስመ ሥላሴን ጠርቶ ጸሎት ሲደርግና መጸሐፈ ክርስትና ጽሎት ሲያደርግበት ውሐው ወደ ማይ ገቦ (ማየ ሕይወት ሲሆን) ስለማይተየን ምሥጢር ጥምቀት ተብሏል፡፡

ጥምቀት የምሥጢራት ሁሉ በር ከፋች ነው፡- ጥምቀት “የክርስትና መግቢያ በር” ናት፡፡ ምክንያቱም ከሌሎች ምሥጢራት ስለሚቀድምና ለእነርሱም መፈጸም ቅድመ ሁኔታ ስለሆነ ነው፡፡ ጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማሕፀነ ዮርዳኖስ ተወልደን ከሥላሴ ልጅነትን የምናገኝበት (ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና) ምሥጢር ነው። ሰው ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ለመካፈል አስቀድሞ መጠመቅና ከማኅበረ ክርስቲያን መደመር አለበት፡፡ ስለዚህም ምሥጢረ ጥምቀት ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት እንዲሁም ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ የእምነታችን መሠረትም፣ የጸጋ ልጅነት የሚገኝበትም ምስጢር ነውና ከሁለቱም ይመደባል፡፡ የጥመወት ትርጉም እና በር ከፋችንት ይህ ከሆነ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን እንደተጠመቀ በጥቂቱ እንደሚከተለው እናያለን፡፡

ጌታችን ለምን ተጠመቀ?፡- ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እከብር አይል ክቡር የባሕርይ አምላክ ሆኖ ሳለ በዮርዳኖስ ወንዝ በአገልጋዩ (በፍጡሩ) በዮሐንስ የተጠመቀበት ምክንያት፦

፩ኛ አንድነቱን ሦስትነቱን ለመግለጽ

፪ኛ-የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ ነው፡፡

አዳምን እና ሔዋንን ሰይጣን ካሳታቸው በኋላ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ መከራ አጸናባቸው ÷ ቀጥሎም የባርነታችሁን ስም ጽፋችዉ ብትሰጡኝ መከራውን ባቀለልኩላችሁ ነበር አላቸውወ እነርሱም አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ ይሁንብን ይደረግብን ብለው ተናገሩ፡፡ እርሱም በሁለት ዕብነ ሩካብ ጽፎ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲኦል ጥሎታል። ኢየሱስ ክርስቶስ የጠፋውን ሰው አዳምን ለመፈለግ በመጣ ጊዜ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ ያንን የዕዳ ደብዳቤ ደምስሶታል ፡፡ ወደሲኦል ተጥሎ የነበረዉን ደግሞ በእዕለተ ዐርብ በአካለ ነፍስ ወደሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ባወጣ ጊዜ አጥፍቶታል ፡፡

፫ኛ- በእርሱ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት ለመቀደስ

፬ኛ ለጥምቀታችን ኀይልን ለመስጠት፤

፭ኛ ለአብነት እርሱ ተጠምቆ እናንተም ተጠመቁ ብሎ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በ፴ ዘመኑ ጥር ፲፩ ከሌሊቱ በ፲ኛው ሰዓት፤ ማክሰኞ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጥቶ ተጠመቀ፡፡

ጌታ በማን ተጠመቀ?፡-በዘመነ ሥጋዌ በናዝሬት ከተማ፤ ዮርዳኖስ ወንዝ የእስራኤል ሕዝብ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ተራ ይዘው በሚጠብቁበት ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ እያለ ይሰብክ ነበር፤ ‹‹እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው መቅሠፍት ታመልጡ ዘንድ ማን ነገራችሁ? እንግዲህ ለንስሓ የሚያበቃችሁን ሥራ ሥሩ፤ አብርሃም አባታችን አለን በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች የአብርሃም ልጆችን ማንሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁ፡፡ እነሆ፥ ምሳር በዛፎች ላይ ተቃጥቶአል፤ መልካም ፍሬ የማያፈራውን ዛፍ ሁሉ ይቈርጡታል፤ ወደ እሳትም ይጥሉታል፡፡›› (ሉቃ.፫፥፯-፱)

ሕዝቡም ምን ቢያደርጉ እንደሚሻል በተራ በተራ ይጠይቁት ጀመር፤ እርሱም ለእያንዳንዱ ሲመልስ፤ ሁለት ልብስ ያለው አንዱን ለሌለው እንዲሰጥ፣ ለተራበ እንዲያበላ፣ ቀራጮችን ደግሞ ከታዘዙት አትርፈው እንዳይውስዱ እንዲሁም ጭፍሮችን በማንም ላይ ግፍ እንዳይፈጽሙ እየመከረ አጠመቃቸው፡፡ እነርሱም በልባቸው እጅግ እያደነቁ ከጌታችን ኢየሱስ ጋር መሰሉት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን እንዲህ አላቸው ‹‹እኔ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ግን የሚበልጠኝ የጫማውን ማሰሪያ እንኳን ልፈታለት የማይገባኝ ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ፣ በእሳትም ያጠምቃችኋል፡፡›› (ሉቃ.፫፥፲፮-፲፯)

ሕዝቡ ሁሉም ከተጠመቁ በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሊጠመቅ ወደ እርሱ ሲጠጋ ቅዱስ ዮሐንስ ግን ‹‹እኔ በአንተ ልጠመቅ እሻለሁ፤ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን?›› በማለት ከለከለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ አሁንስ ተው፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናልና›› አለው፡፡ እርሱም ተወው፤ ጌታችን ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ ከውኃ ወጣ፤ በዚህች ቅጽበትም ሰማይም ተከፈተ፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፡፡ እነሆም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣ፡፡›› (ማቴ.፫፥፲፫-፲፯) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ ልጁ መሆኑን እግዚአብሔር አብ ልጄ ብሎ መሰከረ፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ፤ወልደ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ተጠምቆ በማእከለ ዮርዳኖስ ታየ፡፡

የጥምቀት አመሠራረት፡-የምሥጢረ ጥምቀት መሥራች ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ነገር ግን ከጌታችን ጥምቀት በፊት አይሁድ ለመንጻትና ለኃጢአት ሥርየት (ይቅርታ) የሚጠመቁት “ጥምቀት” ነበራቸው፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥባቸው የተቀደሱ ዕለታትና ቦታዎች ሁሉ ሰውነትንና ልብስን ማጠብ የእግዚአብሔር ቤት ማገልገያ የሆኑ ዕቃዎችን ሁሉ ማጠብ ማንጻት ሥርዓትና ልማድ ነበር፡፡ ይህም የእግዚአብሔርም ፈቃድ ያለበት አሠራር ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቤት ከመቅረባቸውና ለተቀደሰው አገልግሎት ከመግባታቸው አስቀድመው እግሮቻቸውንና እጆቻቸውን የመታጠብ ግዴታም ነበራቸው፡፡ ሰውነታቸውን ከአፍአዊ (ከውጫዊ) እድፍ በማጠብና ንጹሕ በማድረግ በባሕርይ ንጹሕና ቅዱስ በሆነው አምላክ ፊት ውስጣዊ ሕይወትን ንጹሕ አድርጎ የመቅረብን ሥርዓትና ምሥጢር የሚያመለክት መንፈሳዊ ሥርዓት ነበር፡፡ (ኢያሱ፫፡፲፬)፤(ዘፍ ፲፯ ፥፲፬)፡፡

ክፍል ሁለት ይቀጥላል ይቆየን፡፡አሜን፡፡

መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን

መጽሔተ ተልእኮ

መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን መጽሔት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን በሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ የሚዘጋጅ ነው፡፡ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጽሔቱን ያንብቡ!

 

ቃና ዘገሊላ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጥር ፲፪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በተደረገ ሠርግ ቤት ያደረገውን ተአምር በማሰብ በዓልን ታደርጋለች፡፡ ጌታችን ከጥምቀቱ በኋላ በዶኪማስ ሠርግ ቤተ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታጋብዞ በነበረበት ጊዜ ለእንግዶች ወይን ጠጅ አለቀባቸው፡፡

“ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው” (ዘፍ.፲፩፥፯)

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢያት የተገነባውን የሰናኦር ግንብ ያፈረሱበትና አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ቀን ጥር ሰባት የከበረ በዓል ነው፤

በዓለ ግዝረት

በከበረች በጥር ስድስት ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ፤ ልሳነ ዕፍረት ሐዋርያው ጳውሎስ “ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ፤ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ” ብሎ እንደተናገረ።

ዓለመ ምድር

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምድር በገነት ወይም በሲኦል ልትመሰል እንደምትችል ያስረዳሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ወርቃማ ዘመናት ተብሎ የሚጠሩትንም በመጥቀስ የተመረጡ ቅዱሳን ነገሥታት የነገሡበት፣ ደጋግ አባቶች የኖሩበት፣ ሊቀ ጳጳሳትና ጳጳሳት እንዲሁም ቀሳውስትና ካህናት በበጎና በመልካም መንገድ ምእመናንን መርተው በቅድስና ሕይወት ለርስተ መንግሥተ ሰማያት ባበቁበት ጊዜ ምድር በገነት ትመሰል እንደነበር ያስረዳሉ፡፡