ማኅበረ ቅዱሳን የጠራው ሰልፍ እንደሌለ አስታወቀ
ጥቅምት 7 ቀን 2007 ዓ.ም.
በተለያዩና ባልታወቁ አካላት ለማኅበሩ አጋርነት ለማሳየት በመጪው እሑድ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰልፍ ለማድረግ በማኅበራዊ ሚዲያው የሚሽከረከረውን አስመልክቶ ከአባላቱ ለቀረበለት ጥያቄ የሚያውቀው ነገር እንደሌለና ማኅበሩም ምንም ዓይነት ጥሪም እንዳላካሔደ የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1445 entries already.
ጥቅምት 7 ቀን 2007 ዓ.ም.
በተለያዩና ባልታወቁ አካላት ለማኅበሩ አጋርነት ለማሳየት በመጪው እሑድ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰልፍ ለማድረግ በማኅበራዊ ሚዲያው የሚሽከረከረውን አስመልክቶ ከአባላቱ ለቀረበለት ጥያቄ የሚያውቀው ነገር እንደሌለና ማኅበሩም ምንም ዓይነት ጥሪም እንዳላካሔደ የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡
ጥቅምት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ የ33ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሀገረ ስብከቶችን የ2006 ዓ.ም. የሥራ ክንውን ሪፖርት አደመጠ፡፡ ሦስተኛ ቀኑን የያዘው ይህ ጉባኤ በሀገረ ስብከቶች አማካኝነት የቀረበውን ሪፖርቶች ያደመጠ ሲሆን በአብዛኛው የሀገረ ስብከቶች ሪፖርት ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን የሚያደርገውን ሁለገብ ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን በሪፖርቶቹ የቀረቡ ሲሆን የጉባኤው ታዳሚም አድናቆቱን […]
ጥቅምት 6 ቀን 2007 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 5 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም የተጀመረው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ቀጥሏል፡፡ በጥቅምት 5 ቀን የከሰዓት ውሎና ጥቅምት 6 ቀን ጠዋት 24 አህጉረ ስብከቶች ሪፓርቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡
ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በ33ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ባቀረቡት ሪፖርትና በዐዋጅ ነጋሪ መጽሔት 6ኛ ዓመት ቁጥር 10 ጥቅምት 2007 ዓ.ም ላይ በተገለጸው ሪፖርት ውስጥ የማኅበረ ቅዱሳን የ2006 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ከነጻ ሞያ አገልግሎት ውጭ ከ13,948.984.7 /አሥራ ሦስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዐርባ ስምንት ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ዐራት ብር/ በላይ ወጪ በማድረግ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት መደገፉ ተገልጿል፡፡
ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ 33ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በስብከተ ወንጌል አዳራሽ የተጀመረው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መሪነት ጸሎተ ኪዳን ተደርሶ “ወንድምህ ቢበድልህ ምከረው፣ ይቅር በለው” የሚለው የማቴ.18፡15 ከተነበበ በኋላ ነው፡፡
ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም
በዲ/ን ፍቃዱ ዓለሙ
በኑፋቄ ትምህርታቸው ምእመናንን ሲቀስጡና የማኅበረ ካህናቱንና ምእመናኑን አንድነት ሲጎዱ የቆዩት “ቄስ” ገዳሙ ደምሳሽ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ከቅስናና ከቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት እንዲሁም ከማንኛውም ክህነታዊ አገልግሎትና ትምህርተ ወንጌል ከመስጠት ታገዱ፡፡
ጥቅምት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 33ኛው መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 5-8 ቀን 2007 ዓም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በመንፈሳዊ ጉባኤው ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤በሀገር ውስጥና […]
ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን ለአንጋፋውና የሊቃውንት መፍለቂያ ለሆነው የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ 90 ሺሕ ብር የሚያወጡ ኮምፒዩተሮች፤ ፕሪንተሮችና መጻሕፍት ጥቅምት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ለኮሌጁ ደቀመዛሙርት አገልግሎት እንዲውል ድጋፍ አደረገ፡፡
መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
የጅማ ሀገረ ስብከት ያስገነባው ባለ 5 ፎቅ ሁለገብ ዘመናዊ ሕንፃ መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በቅዱስ ፓትርያርኩና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንት ተመረቀ፡፡
መስከረም 20 ቀን 2006 ዓ.ም.
በዲ/ን ፍቃዱ ዓለሙ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ታሪካዊት እንደ መሆኗ፣ ሁሉም ሃይማታዊ በዓላት ከመንፈሳዊ ባህላዊ ሥርዓቶች ጋር ተሣሥረው እንዲከበሩ መሠረት ናት፡፡ ለዚህ ነው ከሀገራዊና ከሃይማታዊ በዓላት ጋር ተያይዘው የሚከናወኑት መንፈሳዊና ባሕላዊ ሥርዓቶች ምንጫቸው/መነሻቸው/ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ናት የምንለው፡፡ ቀድሞም በኦሪቱ በኋላም በሐዲሱ ሕግጋት ጸንታ የቆየች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ ተዟዙራ አስተምራለች፡፡ ለመስቀሉም ሆነ ለሌሎች ሃይማታዊ በዓላት መነሻቸው የቀደሙት አባቶቻችን ከ4ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የዘሩት የወንጌል ዘር ነው፡፡