Entries by Mahibere Kidusan

ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤ ስደተኛው ኢየሱስ የስደተኞች  ተስፋቸው ነህ (ሰቆቃወ ድንግል)

                                                            በመጋቤ ሐዲስ በርሄ ተስፋ መስቀል መጽሐፍም ታሪክም እንደሚነግረን በዓለም ብዙ ዓይነት ስደት አለ። ሁሉም ስደቶች ግን የአዳምንና የሔዋንን ስደት ተከትለው የመጡ ናቸው። ቀደምት ወላጆቻችን ሕገ […]

ሁለት አገልጋዮች በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ዐለፈ

በካሣሁን ለምለሙ የነቀምቴ ማእከል አገልጋይ የነበሩት ዲ/ን መልካሙ ረጋሳ እና ዲ/ን ሽፈራው ከበደ በገተማ ወረዳ ለአገልግሎት ሲፋጠኑ መስከረም ፳ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም በደረሰባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ዐለፈ፡፡ ዘማሪ ዲ/ን መልካሙ ረጋሳ የነቀምቴ ማእከል ጸሐፊ የነበረ ሲሆን በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም ከእናቱ ከወ/ሮ አሙሴ ተፈራ እና ከአባቱ አቶ ረጋሳ ተወለደ፡፡፡ ዘማሪ ዲ/ን መልካሙ ገና በልጅነቱ የብዙ ሙያዎች ባለቤት […]

የኢትዮጵያውያን ይዞታ በሆነው በዴርሱልጣን ገዳም የቅዱስ ሚካኤል ቤተመቅደስ እድሳት ላይ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባላት ያሳዩትን ሕገወጥ ተቃውሞ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፤

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱአምላክ አሜን! ሁላችሁም እንደምታውቁት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኢየሩሳሌም ካሏት ጥንታውያንና ታሪካውያን ቅዱሳት መካናት ውስጥ አንዱና ዋናው በዴርሱልጣን የሚገኘው የመድኀኔዓለም፣ የአርባዕቱ እንስሳ እና የቅዱስ ሚካኤል ገዳማት ናቸው፡፡ከታሪክ እንደምንረዳው ኢትዮጵያውያንበምድረ እስራኤል የነበራቸው ርስት ከሦስት ሽህ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የአሁኗ ኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ መገኛዋን ከዓባይ ምንጭ ጋር በማያያዝ ያለምንም ማሳሳት ከአርባ […]

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻው ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ሲያካሒድ ሰንብቶ ማህበራዊና መንፈሳዊ ለቤተ […]

ከሰላም የምታደርሰንን መንገድ እንያዝ

  ብዙዎቻችን ስለ ሰላም እንናገራለን እንጂ ሰላም በውስጣችን አለመኖሩን የሚያሳዩ ተግባራትን ስንፈጽም እንታያለን፡፡ ሰላም የምንሻ ከሆነ ሰላማውያን ከመሆን በተጨማሪ ሌሎችም ሰላማውያን እንዲሆኑ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ከጥፋት ልንድን ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ከጥፋት ልንታደግ እንደሚገባ “ወንድሞቻችን ሆይ ከእናንተ ከጽድቅ የሳተ ቢኖር ከኃጢአቱ የመለሰውም ቢኖር ኃጢአተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ራሱን ከሞት እንዳዳነ ብዙ ኃጢአቱንም እንደአስተሰረየ ይወቅ” (ያዕ. […]