የዘመናችን የቤተ ክርስቲያን ፈተና
የተከበራችሁ አንባብያን በዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታና በየአካባቢው እና በየክልሉ በቤተ ክርስቲያንና በክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት አስመልክቶ ክፍል አንድና ሁለትን ጽሑፍ ማቅረባችን ይታወቃል፡ ፡ከፍል ሦስት እነሆ ብለናል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት የተነሡ አካላት ለጥፋታቸው የሚጠቅሱትን የፈጠራ ታሪክ ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ልደት እስከ አሁን ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በመጠኑ አሳይተናል፡፡ የገጠማትን ፈተና፣ ሊወጓት የመጡትን ያለዘበችበትን መንፈሳዊ ጥበብ […]