Entries by Mahibere Kidusan

በዓለ ግዝረት

በዚህ ጊዜ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ‹‹አባት ሆይ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው፤ ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ›› አለ፡፡ ያንጊዜም ያለ ሰው እጅ በጌታችን ላይ ግዝረት ተገለጠ (የግዝረት ምልክት ታየ)፡፡

‹‹ለራስህ እና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ›› (፩ኛ ጢሞ. ፬ ፥፲፮)

በአሁኑ ወቅት በአንድም በሌላ አንዳንድ የይዘት፣ የትርጉም፣ የፍቺ ግድፈቶች ከዛ የባሰም የዶግማ ችግር ያለባቸው ለቤተክርስቲያን ትምህርት ስጋት የሆኑ ከስንዴ መሐል የተቀላቀሉ ጥቂት እንክርዳድ የተቀላቀለባቸው መጻሕፍት በቤተ ክርስቲያን ስም እየወጡ ነው፡፡ ስለዚህ እንክርዳዱን ከስንዴው ለቅሞ መለየትና ማረም ያስፈልጋል፡፡

‹‹የገሃነም ደጆችም አይችሏትም›› (ማቴ.፲፮፥፲፰)

ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው ‹‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ÷ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፡፡ እኔም እልሃለሁ÷ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚያች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ÷ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም፡፡››(ማቴ.፲፮፥፲፫—፳)

ጌታችን ኢየሱስ ተወለደ

ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን በዓለም ላይ ሠልጥኖ የነበረውን ጨለማ ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ ሰው ሆነ፡፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው አማናዊው ብርሃን ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው እንዳለው ‹‹ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኵሉ ሰብእ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም፤ በጨለማ ውስጥ ለሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው›› (ኢሳ. ፱፥፪)፡፡

ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሚታወሱባቸው በዓላት መካከል ታኅሣሥ ፳፬ ቀን የሚከብረው በዓለ ልደታቸው አንደኛው ነው፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ዜና ልደታቸውን ሲናገር ‹‹ሐዲስ ሐዋርያ›› በማለት በክብር ጠርቷቸዋል፡፡

‹‹ደስ ይበልሽ÷ ጸጋን የተመላሽ ሆይ÷ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ›› (ሉቃ. ፩፥፳፰-፳፱)

ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም በአምሳለ አረጋዊ እንዲህ አላት ‹‹ደስ ይበልሽ÷ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ÷ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ፡፡›› (ሉቃ. ፩፥፳፰-፳፱) ድንግል ማርያምም ‹‹እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንዴት ይደረግልኛል?›› ብላ ጠየቀችው፡፡

‹‹እጅህን ከአርያም ላክ፤ አድነኝም›› (መዝ. ፻፵፫፥፯)

በየዘመኑ የተነሡ ነቢያትም ምንም እንኳን አምላክ ይህን ዓለም እንዴት እንደሚያድነው በግልጽ ባይረዱትም እግዚአብሔር ዓለሙን የሚያድንበትን ቀን እንዲያቀርበው እንዲህ እያሉ ይማፀኑ ነበር፤ ‹‹አቤቱ ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው፤ ውረድም፤ ተራሮችን ዳስሳቸው ይጢሱም፡፡ መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፤ በትናቸውም፤ ፍላጾችን ላካቸው፤ አስደንግጣቸውም፡፡ እጅህን ከአርያም ላክ፤ አድነኝም›› (መዝ. ፻፵፫፥፭-፯)፡፡

የዩኒቨርሲቲዎች የታሪክ እይታ ከድጥ ወደ ማጡ

በመጀመሪያ ደረጃ ቤተ ክርስቲያን መንግሥትን እየተከተለች፣ በጦር እያስፈራራች ሃይማኖቷን እንዳስፋፋች አድርጎ ማቅረብ የተዛባ አስተሳሰብ የወለደው መሆኑን መናገር እንፈልጋለን። ይህ ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኗን ታሪክ በማዛባት የቀረበው ሐሳብ እንዲስተካከል እንጠይቃለን። እውነቱ ግን በተቃራኒው ነው። ቤተ ክርስቲያን ያለሰለሰችው የአረማውያን እና የአሕዛብ ልቡና ወደ ማእከላዊ መንግሥት ለመታቀፍ እንዳላስቸገረ እና መንግሥት የራሱን ሥራ ለመሥራት እንዳገዘው መረዳት ይገባል። ያለፈው ሥርዓት ፈጽሞታል ለሚሉት ጥፋት ቤተ ክርስቲያንን ተጠያቂ ማድረግ አንደበቷን ዘግታ እንድትቀመጥ ለማድረግ የተሸረበ ሴራ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ገለጻው እውነታን ያላገናዘበ መሆኑን መረዳት እና ተገቢውን መልስ መስጠት አስፈላጊ ሲሆን በሕግ መጠየቅ ይገባል።

የዩኒቨርሲቲዎች የታሪክ እይታ ከድጥ ወደ ማጡ

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በአራት የዩኒቨርሲቲ መምህራን “የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ታሪክ፤The History of Ethiopia and the Horn” በሚል እርስ ለመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማስተማሪያ የሚሆን ጥራዝ አዘጋጅቷል። ዝግጅቱ ለመስከረም አልደርስ ብሎ ይሁን ሌላ ምክንያት ኖሮት ባይታወቅም ለሁለተኛው መንፈቀ ዓመት ሊሰጥ መታሰቡ ተሰምቷል። ስርጭት ላይ ሊውል የተቃረበ የሚመስለው ጥራዝ በሙያው ብቃት ባላቸው ምሁራን መዘጋጀቱም ተገልጧል፡፡ የታሪክ ትምህርት እንዳይሰጥ ተከልክሎ የቆየው የገዥው መደብ መጠቀሚያ ሆኖ ስለኖረ እንደ ገና በአዲስ መልክ መጻፍ አለበት ተብሎ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል።

‹‹አንተም÷ የሰው ልጅ ሆይ÷ ጡቡን ወስደህ በፊት አኑራት፤ የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት፤ ክበባት›› (ሕዝ.፬፥፩)

ቅዱሳት ሥዕላትን ለጸሎት እና ለተለያዩ አገልግሎቶች በምንጠቀምበት ጊዜ ልናስተውላቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ በዋነኛነትም እንዳይበላሹ እና እንዳይደበዝዙ በክብር ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ሥዕላቱ የሚገልጹት የሥዕሉ ባለቤት የሆነውን አምላክ ወይም ቅዱስ፤ ጻድቅ ወይም ሰማዕት ስለሆነ ተገቢውን ክብር እና ሥርዓተ አምልኮ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ምእመናን ትክክለኛዎቹን የሥዕሉን ባለቤቶች አውቀው እንዲያከብሩ እና እንዲማጸኑባቸው ሠዓሊዎች የሚሥሉትን ቅዱስ ሥዕል በትክክል መሣልም አለባቸው፡፡