‹‹የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ›› (፩ቆሮ.፩፥፴፩)
እግዚአብሔር አምላክ ኃያልና ገናና ነው፤ የሚሳነውም የለምና ሁሉን ነገር በምክንያት ያደርጋል፡፡ ሰዎችም በሥነ ተፈጥሯችን የእርሱን ህልውና በማወቅ ለፈጣሪያችን እንገዛ ዘንድ ይገባል፡፡ ድኃም ሆነ ሀብታም፣ ባለሥልጣንም ሆነ ተራ ሰው በፈጣሪው መመካት ይችል ዘንድም ተገቢ ነው፡፡ በትንቢተ ኤርምያስም እንደተገለጸው ‹‹ጠቢቡ በጥበቡ አይመካ፤ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፤ ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፡- ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅን በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና›› ሲል አምላካችን እግዚአብሔር ነግሮናል፡፡ (ኤር. ፱፥፳፫)