Entries by Mahibere Kidusan

መራሕያን

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ባለፈው ትምህርታችን ላይ አኀዝ ወይንም የግእዝ ቊጥሮችን አይተን ነበር፡፡ በዚያም መሠረት ለሰጠናችሁ መልመጃ ምላሽና የዚህን ሳምንት ትምህርት ‹መራሕያን› በሚል ርእስ አዘጋጅተን አቅርበንላችኋልና በጥሞና ተከታተሉን፡፡

ጸሎት በቤተ ክርስቲያን

የተወዳዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች! እንደምን ሰነበታችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን አላችሁ? መልካም፤ እግዚአብሔር አምላካችን የተመሰገነ ይሁን፡፡ በቤታችሁ ሆናችሁ ትምህርታችሁን በጥሞና ተከታተሉ!

ልደቱ ለቅዱስ ማርቆስ

ቅዱስ ማርቆስ ትውልዱ ዕብራዊ ነው፤ ቤተሰቦቹ ግን ይኖሩ የነበሩት በሰሜን አፍሪካ ሲረኒካ  (ቀሬና) በተባለችውና በዛሬዋ ሊቢያ ምዕራባዊ ጠረፍ በተቆረቆረችው ደማቅ ነበር፡፡ ነገር ግን የሰሜን አፍሪካ  ዘላን ጎሳዎች የሆኑት በርበሮች በየጊዜው በከተማዋ ጥቃት እየነሰዘሩ ሀብት ንብረታቸውን እየዘረፉ ስላስቸሯቸው እናቱ ማርያምና አባቱ አርስጦቡሎስ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢየሩሳሌም በመመለስ ቤት ሠርተው ተቀመጡ፡፡…

አማኑኤል- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ

ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች›› በማለት ትንቢት እንደተናገረው የተስፋው ቃል ይፈጸም ዘንድ በዘመነ ሥጋዌ እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ እንደሚወለድ መልአኩ እንዲህ ሲል አበሠራት፤ ‹‹እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ስሙንም አማኑኤል ትይለዋለች፤  አማኑኤል  ማለት  እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።›› (ኢሳ.፯፥፲፬፣ማቴ.፩፥፳፫)

ቸሩ እረኛዬ

ሰላምን ስሻ በአንተ አምኜ
በጭንቅ በነበርኩበት እጅጉን አዝኜ
በዚህች በከንቱ ዓለም በጨለማ ሆኜ
ፈጥነህ ደረስክልኝ ሆነኸኝ አጽናኜ

‹‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም›› (ዘዳ. ፴፫፥፳፮)

ከጠፈር በላይ ርቀቱ፣ ከባሕር በታች ጥልቀቱ፣ ከአድማስ እስከ ናጌብ ስፋቱ የማይታወቅ፣  ነፋሳት ሳይነፍሱ፣ አፍላጋት ሳይፈሱ፣ ብርሃናት ሳይመላለሱ፣ የመባርቅት ብልጭታ ሳይታይ፣ የነጎድጓድ ድምጽ ሳይሰማ፣ መላእክት ለቅዳሴ ከመፈጠራቸው አስቀድሞ፣ በአንድነቱ ሁለትነት፣ በሦስትነቱ አራትነት ሳይኖርበት፣ ለቀዳማዊነቱ ጥንት፣ ለማዕከላዊነቱ ዛሬ፣ ለደኃራዊነቱ ተፍጻሜት የሌለበት፣ በባሕርዩ ሞት፣ በሥልጣኑ ሽረት፣ በስጦታው ንፍገት የማይስማማው፣ የማይሾሙት ንጉሥ፣ የማይጨበጥ እሳት፣ የማይነጥፍ የፍቅር ጅረት፣ የነበረ ያለና የሚኖር፣ እንደ አምላካችን እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም፡፡

ዕውቀት ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

ዕውቀት ‹ዖቀ› ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው፤ ትርጓሜውም ‹ዐወቀ› ወይም አንድን ነገር በአግባቡ መረዳትንና መገንዘብን እንዲሁም አንድን ነገር ለመፈጸምና ለማከናወን  የሚያስችለንን ችሎታ የሚገልጽ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ዕውቀት አንድን ችግር ለማስወገድ የሚያስችል አቅም ወይም ችሎታ መሆኑ ይታመናል፡፡  በግሪኩ ግኖስ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ዕውቀትን የሁሉም ነገር መፍቻ ቁልፍ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌም ያለው ሲሆን ሰው በዕውቀቱ የዘለዓለም ሕይወትን ድኅነትን እንደሚያገኝ በግኖስቲኮች ዘንድ ይታመናል፡፡ በአንጻሩ ዕውቀት የላቸውም ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች አላዋቂዎች ወይም አግኖስ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን እነዚህ አካት ያልበራላቸው በጨለማ ውስጥ ያሉ እንደሆነ በግሪክና በሮማ ሥልጣኔ ዘመን ይታመን እንደነበር እንገነዘባለን፡፡

ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ

የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤ ከዚያም ዲያቆን ሆኖ ተሾሟል፤ ይህም ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡