Entries by Mahibere Kidusan

“ሰውን በአርአያችንና በአምሳላችን እንፍጠር” (ዘፍ.፩፥፳፮)

በዕለተ ዐርብ እግዚአብሔር አራት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ እነርሱም በእግር የሚሽከረከሩ፣ በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ፣ በየብስ፣ የሚኖሩ በደመ ነፍስ ሕያዋን የሆኑ ፍጥረታትን ነው፡፡ በመጨረሻም እግዚአ ዓለም ሥላሴ “ሰውን በአርአያችንና በአምሳላችን እንፍጠር” ብለው በነግህ አራቱን ባሕርያተ ሥጋ አምስተኛ ባሕርየ ነፍስን አዋሕደው የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ አድርገው በማዕከለ ምድር በቀራንዮ ፈጠሩት፡፡ (ዘፍ.፩፥፳፮)

ጌታችን ጾመ፤ በዲያብሎስም ተፈተነ (ማቴ.፬)

ጌታችን በገዳመ ቆሮንቶስ ሲጾም “ወቀርበ ዘያሜክሮ፤ ሰይጣን ሊፈትነው ቀረበ” ይላል፡፡ በመጀመያም እንዲህ አለው፤ “እመሰ ወልደ እግዚአብሔር አንተ በል ከመ እላ አዕባን ኅብስተ ይኩና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።” (ማቴ. ፬፥፫) ሰይጣን የመጀመርያውን ሰው አዳም በመብል ድል ነሥቶት ስለነበር በለመደበት ክርስቶስን ድል ሊነሣ መጣ። ይኸውም አብ በደመና “የምወደው ልጄ እርሱ ነው” ሲል ሰምቶ ነበርና ይህን ተናግሯል። (ማቴ.፫፥፲፯) ሰይጣን እንዲህ ያለው በትርጓሜ ወንጌል እንደምናገኘው በአንድ እጁ ደንጋይ ይዞ በሌላ እጁ ደግሞ ዳቦ ይዞ በመቅረብ ነበር። ምን ነው ከያዝከው አንበላም ቢለኝ አዳምን ድል እንደነሣሁት እርሱንም ድል እነሣዋለሁ። ቢያደርገው ደንጋዩን ወደ ዳቦ ቢቀይረው ለሰይጣን ታዛዥ ብየ እዳ እልበታለሁ ብሎ ቀረበ። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ አንድንምታ ትርጓሜ)

ኪዳነ ምሕረት!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? የዕረፍት ጊዜ እንዴት ነበር? መቼም ቁም ነገር ሠርታችሁበት እንዳሳለፋችሁ ተስፋችን ነው፡፡ ልጆች! ዛሬ የምንማማረው ስለ እመቤታችን ኪዳነ ምሕረትና ከአምላካችን ስለተሰጣት ቃል ኪዳን ነው፡፡

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ወር በገባ በ፲፮ኛው (ዐሥራ ስድስት) ቀን “ኪዳነ ምሕረት” ብለን የምናከብረውና የምንዘክረው ታላቅ በዓል አለ፡፡ ይህ በዓል ለምን የሚከበር ይመስላችኋል?

“ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ” (ኢዩ.፩፥፲፬)

ከጾም የሥጋ ንጽሕና፣ የነፍስ ቅድስናና ድንግልና ይወለዳሉ።  ይህች ጾምም የጽድቅ ሥራዎች ሁሉ መርከብ ናት፤ በውስጧ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ይኖራሉ። ሩቅ ሀገር የሚሄዱት ያለ መርከብ በባሕር ላይ ፈጽሞ መሄድ እንዳይቻላቸው ሁሉ እንዲሁ ስለጽድቅ የሚጓዙትም በመንፈሳዊት ሐመር ካልታሳፈሩ አንዲት እርምጃ ስንኳን መራመድ አይቻላቸውም።” (ርቱዓ ሃይማኖት ገጽ ፺፩-፺፪)

ግሩማን ፍጥረታት

ከአዳም ትውልድ ሰባተኛ የሆነው ነቢዩ ሄኖክ ያልተመረመሩ እጅግ አስደናቂ (ግሩማን) ፍጥረታትና አዕዋፍ ስለመኖራቸው ጨምሮ ሲጽፍ “ከዚያም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ሄድኹ፤ በዚያም ታላላቅ አውሬዎችን አየሁ፤ አንዱ ከሌላው ልዩ ነው፤ የወፎቹም ፊታቸው ይለያያል፤ መልካቸው ቃላቸውም አንዱ ከሌላው ይለዋወጣል” ይላል፡፡ (ሄኖክ ፰፥፳፱)