Entries by Mahibere Kidusan

የጳጉሜን ወር

በዓመት ውስጥ ካሉት ወራት የተለየች፣ ቀኖቿም ጥቂት እንዲሁም አጭር በመሆኗ የጳጉሜን ወር ተናፋቂ ያደርጋታል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን ኢትዮጵያ ካደላት ስጦታ አንዷ የሆነችውም ይህች ወር በዘመነ ዮሐንስ ስድስት ቀናት እንዲሁም ደግሞ በዘመነ ማርቆስ፣ በዘመነ ሉቃስና በዘመነ በማቴዎስ አምስት ቀናት ብቻ አላት፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን አስትምህሮ የጳጉሜን ወር የዓመት ተጨማሪ ወር እንላታለን፡፡  ምዕራባዊያኑ ግን ተጨማሪ ቀን እንደሆነች በማሰብ በዓመቱ ባሉ ወራት ከፋፍለዋታል፡፡

ጳጉሜን የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ጭማሪ” ማለት ነው፡፡ በግእዝ “ወሰከ-ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ተውሳክ (ተጨማሪ) ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)

ዕረፍተ ዘአበዊነ አብርሃም፣ይስሐቅ ወያዕቆብ

የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብን መታሰቢያቸውን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን አዘውናል፤ ከእርሳቸው ዘለዓለም የሚኖር ርስትን ተቀብለናልና፡፡ የእነዚህንም አባቶች ገድላቸውን እንዘክር ዘንድ ተገቢ ነው፡፡

ነገረ ግሥ ወአገባብ

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! ባለፉት ክፍሎች ዘመድ የሙሻ ዘርን የመጨረሻውን ክፍል አቅርበንላችኋል። በዚህ የትምህርታችን ክፍለ ጊዜ ደግሞ ስለ ‹‹የነገረ ግሥ ወአገባብ›› ይዘንላችሁ ቀርበናል። በጥሞና ተከታተሉን!

በዓለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት

አምላካችን እግዚአብሔር ለነቢዩ ኤርምያስ “በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ፤ ከማኅፀን ሳትወጣ ቀድሸሃለሁ” በማለት እንደተናገረ የገናናው ጻድቅ የአባታችን ተክለ ሃይማኖት ዜና ሕይወቱን እንዘክራለን፡፡ (ኤር.፩፥፭)

ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች!  ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁ? የጾመ ፍልስታ ወቅት እንዴት ነበር? እንኳን አደረሳችሁ!  የክረምት ወቅት አልፎ አዲሱን ዓመት ልንቀበል ቀናት ብቻ ቀርተውናል! እህቶቻችንን ለዚህ ያደረሰንን ፈጣሪ በዝማሬ ያመሰግናሉ፤ ልጆች! ለመሆኑ አበባ አየሽ ወይ? እያልን የምንዘምረው “የተዘራው ዘር በቅሎ ቅጠል ከዚያም ደግሞ አበባን ሰጥቷል፤ ቀጥሎ ደግሞ ፍሬን ይሰጣል” በማለት የምሥራችን እያበሠሩ ለዚህ ያደለንን ፈጣሪ ያመሰግናሉ፡፡ ልጆች! ሌላው ደግሞ መዘንጋት የሌለባችሁ ነገር ለመጪው የትምህርት ዘመን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባችሁ ነው፤ መልካም!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁ ታሪክ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ነው፤

ምሬሃለሁ በለኝ!

በቀን በሌሊት ለዓይን ጥቅሻ ሳያርፉ

ለምስጋና በትጋት ዘወትር በሚሰለፉ

ስለ መላእክቱ ተማጽኜሃለሁ

በለኝ ምሬሃለሁ

ዘይታቸው ሳይነጥፍ መብራቱን አብርተው ከጠበቁህ ጋራ

ነፍሴን አሰልፋት ከምርጦችህ ተራ

ስለመረጥካቸው ምሬሃለሁ በለኝ

ዳግም ስትመጣ በቀኝህ አቁመኝ!

መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን

መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን መጽሔት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን በሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ የሚዘጋጅ ነው፡፡ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጽሔቱን ያንብቡ!

ጌቴሴማኒ

ሥርወ ቃሉ ከዕብራይስጥ ቋንቋ የሆነው ጌቴሴማኒ “ጋት እና ስሜኒ” ከሚሉ ከሁለት ጥምር ቃላት የተገኘ ነው፡፡ ትርጉሙም “የዘይት መጭመቂያ”  ማለት ነው፡፡ ጌቴሴማንኒ የአትክልት ቦታ ዙሪያውን በወይራ ዛፎች የተከበበ ነው፡፡…ይህም ስፍራ አምላካችን እግዚአብሔር ፍርዱን የሚያደረግበት እንደሆነ ይታመናል፡፡

ታላቁ አባ መቃርስ

ከ፹ ዓመት በላይ በበረሃ የተጋደሉ፣ በአስቄጥስ ገዳም ፭፼ መነኮሳትን በመመገብ የመሩ፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ስለ ሥጋ ወደሙ ክብር ሲሉ ለ፷ ዓመት ምራቃቸውን ሳይተፉ የኖሩት ታላቁ አባት አባ መቃርስ በነሐሴ ፲፱ ፍልሰተ አጽማቸው ሳስዊር ከሚባል ሀገር ወደ አስቄጥስ የተፈጸመበት የከበረ በዓል ነው፡፡

በዓለ ትንሣኤ ወዕርገታ ለቅድስት ድንግል ማርያም

ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድና ድካም በ፷፬ ዓመቷ በጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓ.ም ያረፈችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤዋም ሆነ ዕርገቷ በክብር የተፈጸመ እንደመሆኑ እኛም ልጆቿ ይህችን የተባረከች ቀን እናከብራለን፡፡