Entries by Mahibere Kidusan

ልሂድ አደን!

ልቤ ተነሣስቶ ጽድቅህን ፍለጋ

ከማዳንህ ጋራ አንተኑ ሊጠጋ

ልሂድ ወደ ዱሩ ከአባቶች ማደሪያ

ከለምለሙ መስክህ ከጽድቅ መነኻርያ

ተአምራትን ፍለጋ

በዚህ ምድር እንደ ክርስቲያን ሆነን ስንኖር የሚገጥሙን ፈተናዎችና አጣብቂኞች ይኖራሉ፡፡ የሚገጥሙንም አንዳንድ ፈተናዎችም ከማስጨነቃቸው የተነሣ በእግዚአብሔር ተአምር እናመልጣቸው ዘንድ እንመኝ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ፈተናዎቹ ጸጋና ክብር ሊያሳጡንም ጭምር ስለሚችሉ ተአምራት ተደርገውልን ከምናመልጣቸው በሃይማኖትና በምግባር ጸንተን፣ በጾም በጸሎት ታግሠናቸው ድል ብንነሣቸው የበለጠ ክብርን ልናገኝባቸው እንችላለን፡፡ ከጻድቁ ኢዮብ፣ ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፣ ከደቀ መዝሙሩ ከቅዱስ ጢሞቴዎስም ተግባራዊ ሕይወት ይህን እንማራለን፡፡

እግዚአብሔርን ለማመን በቤቱ ጸንቶ ለመኖር ለሚገጥሙን የዚህ ዓለም መሰናክሎች ሁል ጊዜ ተአምራትን መሻት እግዚአብሔር የሚወደው መንገድ አይደለም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌ በሚያስተምርበት ወራት ጻፎችና ፈሪሳውያን ወደ እርሱ ቀርበው ‹‹መምህር ሆይ ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን›› አሉት፡፡ እርሱ ግን መልሶ ‹‹ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ይሻል፤ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም፡፡ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል፤ የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ፡፡ ንግሥተ አዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፡፡ አነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ›› አላቸው፡፡ (ማቴ.፲፪፥፴፰‐፵፪)

ምልክትን (ተአምርን) የሚፈልግ ትውልድ ለምን ክፉና አመንዝራ ተባለ? ‹ክፉ› የተባለው እምነቱን በተአምራት ላይ ስላስደገፈና ስለሚያስደግፍ ነው፡፡ ‹አመንዝራ› የተባለበትም ምክንያት አመንዝራ ሰው ነገሩ አንድ ሲሆን ዕለት ዕለት ሴት (ወንድ) ሊለወጥለት እንዲወድ አይሁድና የአይሁድን መንገድ የሚከተሉ ሰዎችም ዕለት ዕለት ትምህርትና ተአምራት ሊለወጥላቸው ይወዳሉና ነው፡፡

‹‹የለመንከኝን ሁሉ አደርግልህ ዘንድ ቃል ኪዳንን ሰጥቼሃለሁ››

ለሰማንያ ዓመት በጫካ ውስጥ ከአንበሶችና ከነብሮች እንዲሁም ከአራዊት ጋር መኖርን ሳይፈሩ እስከ ሞት ድረስ የታገሡ እንዲሁም በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቃል ኪዳን የተቀበሉበትን ጥቅምት አምስት ቀን እናከብር ዘንድ ይገባል፡፡ በሀገረ ግብጽ የተወለዱት ጻድቁ አባት የእግዚአብሔር ትእዛዝ ሆኖ ስለ ኢትዮጵያ ይለምኑና ይማልዱ ዘንድ ፈቃዳቸውም ስለነበር ቤተሰቤን ሆነ ሕዝቤን ሳይሉ ወደ ሀገራችን በመምጣት በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ደማቸው ፈሶ እስኪያልቅና ሥጋቸውም አልቆ አጥንቶቻው እንደበረዶ እስኪሆን ድረስ የጸለዩ ታላቅ አባታችን ናቸው፡፡

ውኃ የሌለባቸው ምንጮች

ውኃ ከምንጭ ተገኝቶ እየፈሰሰ የፍጥረትን ጥማት ያረካል፡፡ በውኃ ሰው ሕይወቱን ያለመልማል፤ እንስሳትና አራዊትም እንዲሁ፡፡ ዕፅዋትና አዝርዕትም ያለ ውኃ አይለመልሙም፤ አይበቅሉምም፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ የአገባቡ መምህራን በውኃ ምንጭ ተመስለዋል፡፡ ከምንጭ ንጹሕ ውኃ ተገኝቶ ፍጥረትን እንደሚያረሰርስ ከመምህራንም አንደበት በውኃ የሚመስል ቃለ እግዚአብሔር እየፈሰሰ የሰው ልጆችን በጽድቅ እንዲኖኑ ያደርጋል፡፡ ምእመናን ውኃ ቃለ እግዚአብሔር ከሚገኝባቸው እውነተኞች መምህራን እግር ሥር ተገኝቶ በመማር ከድርቀት ኃጢአት ወደ ልምላሜ ጽድቅ ይመጣሉ፤ የመንፈስ ፍሬንም ያፈራሉ፡፡

ቅድስት አርሴማ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁ! የክረምት ወቅት አልፎ አዲሱን ዓመት ተቀብለናልና ለዚህ ያደረሰንን ፈጣሪያችንን ማመስገን ይገባል! ልጆች! መስቀል በዓል እንዴት ነበር? በሰላም በፍቅር አከበራችሁ አይደል? የእኛን ምክርም ተቀብላችሁ ለመጪው የትምህርት ዘመን ዝግጅት ስታደርጉ እንደቆያችሁ ደግሞ ተስፋችን ነው፡፡ አሁን ደግሞ ትምህርት ስለጀመራችሁ በርትታችሁ መማርን እንዳትዘንጉ! ከአሁኑ ጀምራችሁ መምህራን የሚነግሯችሁን በንቃት ተከታተሉ፤ መጻሕፍትን አንብቡ፤ ያልገባችሁን ጠይቁ፤ የቤት ሥራችሁን በአግባቡ ሥሩ፤ የጨዋታ ጊዜያችሁንና ቴሌቪዥን የምታዩበትን ጊዜ መቀነስ አለባችሁ፤ አሁን የእናንተ ተግባር፣ እይታ፣ ሥራ፣ ጉዳይ ሁሉ ትምህርት እና ትምህርት ብቻ ስለሆነ ጎበዝ ተማሪዎች ሁኑ፤ መልካም!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁ ታሪክ የቅድስት አርሴማን ነው፤

ቃላተ አንጋር

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! በዘመነ ሉቃስ የመስከረም ወር ሁለተኛ ክፍለ ጊዜያችን የሆነውን ትምህርት ከማቅረባችን በፊት በባለፈው ትምህርታችን በግእዝ ቋንቋ የምንጠቀምባቸውን ዓረፍተ ነገሮች ከቤተሰቦቻችሁ፣ ከዘመዶቻችሁ፣ ከጓደኞቻችሁ እንዲሁም ከጎረቤቶቻችሁ ጋር እንድትለማመዷቸው አቅርበንላችሁ እንደነበር በማስታወስ በሚገባ ተረድታችሁ እንደተለማመዳችሁትና በቃላችሁ እንደያዛችኋቸውም ተስፋ እናደርጋለን!

የዚህ ሳምንት ትምህርታችን ደግሞ በግእዝ ቋንቋ ውስጥ የምንጠቀምባቸው የንግግር ስልቶች (ቃላተ አንጋር) ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ስለዚህም በመጀመሪያ በግእዝ ቀጥሎም በአማርኛ ስልቶቹን አከታትለን አቅርበንላችኋልና ተከታተሉን!

የጽጌ ወር

ምድር በአበቦችና በዕፅዋቶች ተሞልታ የምታሸበርቅበት ወቅት የጽጌ ወር በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ የመዳኛችን ተስፋ የሆነችውና የዓለምን ቤዛ የወለደችን ቅድስት ድንግል ማርያም አበባውን በሚያስገኙት ዕፀዋትና በምድር፣ የተወደደ ልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ በአበባው እንደሚመሰሉ ቀደምት ነቢያት አስተምረውናል፡፡

ግሽን ማርያም

በሀገራችን ኢትዮጵያ በወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ የሚገኘው ታላቁ የግሸን ማርያም ደብር የግማደ መስቀሉ መገኛ በመሆኑ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ትልቅ ተስፋና መመኪያ ነው፡፡ መስቀል የክርስትናችን መገለጫ፣ የብርሃናችን ዐምድ እንዲሁም የሰላማችን መገኛ ነውና፡፡

ጉባኤ ኒቅያ

ጉባኤ ኒቅያ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን የጠበቀችበት፣ አርዮስና አርዮሳውያን የተወገዙበት፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት፣ አዳኝነት፣ ጌትነት፣ መድኃኒትነት የተመሠከረበት፣ ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ትምክህት የሆነበት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህን ጉባኤ ትቀበላለች፤ ትልቅም ስፍራ አላት፡፡

ጨረቃ

እስኪ እንጀምር ከልደቷ

በፍጥረቱ በውልደቷ

ከቀን በዐራተኛ መገኘቷ

በረቡዕ በዐራተኛ

ከተራራ ከፍ ያለች ከፀሐይ መለስተኛ