ማኅበረ ቅዱሳን በአርሲ ለሞቱት ኦርቶዶክሳውያን የ፯ኛ ቀን መታሰቢያ በጸሎተ ፍትሐት እንዲታሰቡ አደረገ።
ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም በአርሲ ዞን በደረሰው ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ ኦርቶዶክሳውያን ፯ኛ ቀን መታሰቢያ ጸሎተ ፍትሐትና የጸሎተ ቅዳሴ ሥርዐት በመንበረፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል።
በዕለቱ በተከናወነው ጸሎተ ፍትሐትና ሥርዓተ ቅዳሴ ለሞቱት ምእመናን እግዚአብሔር አምላክ መንግሥተ ሰማያትን እንዲያወርሳቸው፣ ለቀሩት ቤተሰቦቻቸውና ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መጽናናትን እንዲሰጥ ጸሎት ተደርጓል። በሃይማኖታቸው ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ክርስቲያኖች የቤተ ክርስቲያን ክብርና ጥንካሬ ናቸው። የተጎዱ ቤተሰቦችን በመደገፍና በመጠየቅ ረገድ ማኅበሩ የበኩሉን አደራና ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን ገልጾ፣በጉዳቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በማሳወቅ
ኦርቶዶክሳዊያን የተጎዱትን በጸሎትም ሆነ በቁሳቁስ ለማገዝ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርቧል።
በመጨረሻም ይህን በማስመልከት ዛሬ ጥቅምት ፳፩/ ፳፻፲፱ ዓ.ም online የጸሎት መርሐ ግብር ተዘጋጅል።
🔷ሰዓት🔷
· ምሽት 1:00 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር
ቦታ :- online
· ቴሌግራም https ://t.me/mkpublicrelation
✝️ ለበለጠ መረጃ✝️
• 0943000403 / 0962171717 / 0966636363
