በቤተ ክርስቲያናችን ከላይ እስከ ታች ወጥ የሆነ የሰው ሀብት አስተዳደር መመሪያ ያስፈልጋል ” ከሐመር መጽሔት ” የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ዐምድ ግንቦት 2018 ዓ.ም
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦#ግንቦት ፳፻፲፰ ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በሚዲያ አገልግሎት ተቋም በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት ፴፫ኛ ዓመት ቁጥር ፭ ግንቦት ፳፻፲፰ ዓ.ም መልእክት #ዘማኅበረ ቅዱሳን ” በላቀ ትጋት የኋለውን እየረሳን ከፊታችን ያለውን አገልግሎት እናስቀጥለሰ “በሚል በመልእክት ዐምዷ ታስነብባለች።
.#ዐውደ ስብከት ሥር” «የአዳም ተስፋ “በሚል ርእስ በሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የተዘጋጀ ስብከት በስፋት ታስነብባለች።ሃይማኖት የሚጸናው በተስፋ ሲሆን ተስፋም የሚፈጸመው በሃይማኖት ነው፡፡ ተስፋ የሌለው ሃይማኖት የለውም፡፡ የሚያሳርፍ ተስፋ ያለው በሃይማኖት ነው፡፡
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#የአባቴን ተስፋ በእናንተ እልካለሁ ” በሚል ዐቢይ ርእስ ስለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ ተዘጋጅቷል ።
ይህቺን ቤተ ክርስቲያን የቋንቋዎች ሁሉ ባለቤት ያደረጋት መንፈስ ቅዱስ ነው። ይህች በቀራንዮ መካን በመልዕልተ መስቀል በፈሰሰ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተች አማናዊት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት ናት። መሠረቷና ጉልላቷ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሷ ክርስትናን የተቀበለችው ከቅዱሳን ሐዋርያት ነው፥ እነርሱ ደግሞ ከጌታ ተቀብለዋል።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ ከሀብት መነጠቅ እስከ ተቋማዊ ዐቅም መሸርሸር ” በሚል ሰፊ ጉዳዮች ይዛለች። ቤተ ክርስቲያን በውስጧ የምታከናውናቸው ጥቃቅን የገቢ ምንጮች፣ ተቋሙ በራሱ እግር እንዲቆም የሚያደርጉ የመደጎሚያ ዘዴዎች እንጂ የንግድ ሥራዎች አይደሉም።በአሁኑ ወቅት የኑሮ ውድነቱ እጅግ በከፋበት ሁኔታ፣ አጥቢያዎች ለካህናት አነስተኛ ደመወዝ የሚከፍሉት ካሏቸው ጥቂት ሱቆች በሚያገኙት ገቢ ነው።
• #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ “የሕይወት ውሳኔ ” በሚል ርእስ ጋብቻን በሚመለከት ሰፊ ጹሑፍ ታስነብባለች።
#በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኘውን “የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ” ክፍል _፪ ታስቃኛለች ። ቅዱስ ያሬድን በመላው አላማ እንደሚገባው የማስተዋወቅ ሥራ በእቅድ ተዘጋጅቶ ፕሮጀክት በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ እየተሠራ ነው ።ሙሉውን ከመጽሔቱ እንድታነቡ እጋብዛለሁ ።በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ሂደትና ውጤት ይዛለች።
በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን በርካታ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ መገባቱን መልአከ ገነት ዘማርያም ሙጬ የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ ይገልጻሉ፡፡የአብነት ትምህርት ቤት ለመገንባት አንዱ የደብሩ ፕሮጀክት ነው።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “ “ለሠመረ የካህናት አገልግሎት የሚጠበቅ ሚና “በሚል ።ሰፊ ጹሑፍ ታስነብባለች።ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ዛሬ ከገጠሟት ዐበይት ተግዳሮቶች አንዱ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ (Database Management) አለመኖር ነው።
ዘመኑ የቴክኖሎጂና የረቀቀ የመረጃ ዘመን እንደ መሆኑ መጠን፣ ካህናት የወቅቱን ትውልድ በትክክለኛ መንገድ ለመቅረጽና ቤተሰቦቻቸውን በሚገባ ለማሳደግ ዘመናዊ ዕውቀትን መታጠቅ ይኖርባቸዋል።
ቤተ ክርስቲያን ወደ ተለያዩ አህጉረ ስብከት የምትልካቸው ካህናት የሕግና የደኅንነት ዋስትና ሊኖራቸው ይገባል።ካህናትን መንከባከብ የዛሬዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊያሳስባት የሚገባ አንገብጋቢ የህልውና ጉዳይ ነው።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ “# “ፍለጋ” ” በሚል ኪነ ጥበብ ታስነብባለች ።
• #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ተግባር ምን እንደሆነ ” በጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ከሚገኙት መምህራን መካከል መምህር በትረ ማርያም ጋር የተደረገውን ጥያቄና መልስ ይዛለች ።
በአሁኑ ወቅት ውሳኔዎች ወደ ታች ሲወርዱ የሚያስፈጽመው አካል የሚከናወነውን ሥራ መከታተልና ገምግሞ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማቅረብ ላይ ክፍተቶች ይታያሉ፡፡
ሐመር መጽሔት ፴፫ ኛ ዓመት ቁጥር፭ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
━━━━━༺✞༻━━━━
@Mahibere Kidusan – ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል


