አውስትራሊያ ማእከል ዝክረ ቅዱስ ያሬድ መርሐ ግብር አካሄደ
በማኅበረ ቅዱሳን አውስትራሊያ ማእከል የተዘጋጀው “ዝክረ ቅዱስ ያሬድ” መርሐ ግብር ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም (May 24, 2026) ተካሄዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ያሬዳዊ ወረብ፣ የቅዱስ ያሬድን የሕይወት ታሪክ ከትውልድ እስከ መሰወር እንዲሁም ቅዱስ ያሬድ ከነገረ መለኮት ባሻገር ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያደረገው አስተዋፅኦ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ስለ ሦስቱ የዜማ ስልቶችና ስለ አምስቱ የዜማ መጻሕፍት ጥልቅ ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
በመጨረሻም ትውልዱ ከቅዱስ ያሬድ ሕይወት ምን መማር አለበት? የሚለው ተነሥቶ ትዕግሥትን፣ ጽናትን፣ ብርታትን እና ስኬትን በመማር ቤተ ክርስቲያንን ማገልገል ይገባል ተብሏል።
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
See less
