ስብከት

ስብከት | ክርስቲያናዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር


“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸነፍ” (ሮሜ ፲፪፥፳፩)

ክፉና በጎ የሰው ልጆች ባሕርያት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ለመልካም ነበረ፡፡ (ዘፍ.፩፥፲፪) ምንም እንኳን የፍጥረት አክሊል የሆነው ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከብርሃን ጨለማን፣ ከሕይወት ሞትን፣ ከመታዘዝ አለመታዘዝን ቢመርጥም እግዚአብሔር አምላክ የፈጠረው ስሙን እንዲቀድስ ክብሩን እንዲወርስ ነበረ፡፡ ለዚህም ክፉና ደጉን መለየት ይችል ዘንድ አስቀድሞ የሚያስተውል አእምሮ ሰጥቶት ነበር፡፡ በኅሊናው…




ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን | ትምህርተ ሃይማኖት | ክርስቲያናዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር | ወቅታዊ ትምህርት


ሥርዓተ አምልኮ

በዓላት ከማንኛውም ቀናት የበለጠ አምላካችን እግዚአብሔርን የምናመሰገንባቸውና የምናወድስባቸው፣ የተቀደሱትን ዕለታት በማሰብና በመዘከር በዝማሬ፣ በሽብሻቦና በእልልታ የምናከብርባቸው ናቸው፡፡ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው የሚወጡባቸውና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚባርኩባቸው ስለሆኑም በክብርና በድምቀት ይከበራሉ፡፡   




ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን | ስብከት | ክርስቲያናዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር


“ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ” (ሥርዓተ ቅዳሴ)

ምሥራቅ የቃሉ ፍቺ “የፀሐይ መውጫ” ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ገጽ ፮፻፹) በሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ “ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ” በማለት በዜማ ለምእመናኑ ያውጃል፤ በእርግጥ በቅዳሴ ጊዜ በመካከል የሚያነቃቁና የአለንበትን ቦታ እንድናስተውል የሚያደርጉ ሌሎች ዐዋጆች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል “እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ የተቀመጣችሁ ተነሡ” የሚለው ነው፡፡…





“ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ”

በዓላት | ወቅታዊ ትምህርት | ዝክረ ቅዱሳን


“ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ”

የካህን ልጅ ካህን፣ ምድራዊ የሆነ ሰማያዊ፣ ሰው ሲሆን መልአክ፣  ከሱራፌል ጋር የእግዚአብሔርን ዙፋን ያጠነ፣ ከመላእክት ጋር የተባበረ፣ ግዙፍ ሲሆን የረቀቀ፣ ባሕታዊ ሲሆን መምህር፣ ኢትዮጵያን በወንጌል ያበራ፣ የምድር ጨው፣ ስለአባታችን ተክለ ሃይማኖት ይህን እወቁ! የፀጋ ዘአብ ዘር ምን ያህል ቡርክት ነች፤ የእግዚእኃረያ ማህፀን ምን ያህል ለምለም ነች!? አንደበቱ ለምስጋና የተፈታ፣ መላእክት…




ስብከት | ኪነ ጥበብ


በዓይኖችህ ታየዋለህ

በሰማርያ ረኃብ በጸናበት ዘመን የሚቀመስም ጠፋ፤ ከረኃቡ ጽናት የተነሣ እናት ልጇን እስከ መብላት ደረሰች። በእዚያም ሀገር ኤልሳዕ የሚባል የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። እንዲህም አለ፤ ነገ በዚህች ከተማ በአንድ ሰቅል አንድ መሥፈርያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል ሁለት መስፈርያ ገብስ ይሸመታል። ያኔ ንጉሡ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደረ፤ እንዴት ይቻላልም አለ። የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳ እንዲህ…




ስብከት | ትምህርተ ሃይማኖት | ወቅታዊ ትምህርት


ሥርዓተ አምልኮ

በጸሎትና በስግደት እንዲሁም በምጽዋት የታገዘ ጾም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ በመሆኑ ድኅነትን ማሰጠት ብቻም ሳይሆን በረከትን ያስገኛል፡፡ በዚህም የተነሣ ሥራችን፣ ትዳራችን እንዲሁም አገልግሎታችን ይባረክልናል፡፡




ስብከት


ስብከተ ወንጌል

ቅዱስ ዳዊት "ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ፤ የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና”  እንዳለ  የቀደመ በደላችንን ሳያስብብን ጭንቀታችንን ችግራችንን ይቅር ብሎ ወደ እዚህ ምድር መጥቶ የምሥራች፣ ብርሃን፣ መንገድ፣ መስታወት፣ የሕይወት ዛፍ የሆነችውን ወንጌልን ሰበከን፤ አስተማረን። (መዝ.፸፰፥፰) ሐዋርያትንም “ሑሩ ውሰተ ኩሉ ዓለም ወስብኩ…




ስብከት


“በምንም አትጨነቁ” (ፊል.፬፥፮)

በሕይወታችን ለሚገጥመን ማንኛውም ችግር ከእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ ይኖረዋል፡፡ በእርሱ አምነንና ታምነን እስከኖርን ድረስ ከመከራና ከሥቃይ ያወጣናል፡፡ ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት በሕይወታቸው ውስጥ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ የሚረዳቸው ቤተሰብም ሆነ ዘመድ ከሌላቸው ደግሞ ችግራቸውን ስለሚያባብሰው ወደከፋ መከራ ውስጥ ሲገቡ ሰምተንም ሆነ ተመልክተን ይሆናል፡፡ ነገር ግን አምላካችን እግዚአብሔር ሰውን የሚፈትነው ለበጎ እንደሆነ በማወቅና በመረዳት…




ሥነ ፍጥረት | ስብከት


“ለፀሐይም ቀንን አስገዛው፤ ጨረቃንና ከዋክብትንም ሌሊትን አስገዛቸው” (መዝ.፻፴፭፥፰‐፲)

‹‹የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትን ሥራቸውን ዕወቅ፤ ከሁሉ የሚደንቅ ክበባቸውን ከሁሉ የሚበልጥ ብርሃናቸውን ሁሉ ዕወቅ፤ በየወገናቸው የሚያበሩ የሚመላለሱ የእነዚህን የምሳሌያቸውን ሥራ ዕወቅ፤ ሁሉ ጊዜ እርስ በእርሳቸው እንደምንም እንደሚቀራረቡ ዳግመኛም እንደምንም እንደሚራራቁ ዕወቅ…›› (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ባስልዮስ ምዕራፍ ፴፭፥፲፯)




ሥነ ፍጥረት | ስብከት


የዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት

ዕለተ ማክሰኞ የፍጥረት ሦስተኛ የምስጋና ሁለተኛ ቀን ነች፤ በባሕረ ሐሳብ ቀመር ደግሞ ዕለተ ቀመር ትባላለች፤ በፀሐይ አቆጣጠር ሰባተኛ ቀን ትባላለች፡፡ ዛሬ ግን የምናነሣው በዕለተ ፍጥረት ስለተከናወነባት ክንዋኔ ነው፡፡