ሀገሬ!

በአንቺ ነው መኖሬ

የምወድሽ ሀገሬ

ፊደላትን ቆጥሬ

ሃይማኖትን ተምሬ

ያፈራሁብሽ ፍሬ!

ወልድ ተወለደልን!

ኧረ ይህች ቀን ምንኛ ድንቅ ናት!

በዓይን የማይታየው የተገለጠባት

የማይዳሰሰው በአካል የተገኘባት

አንድ አምላክ ፈጣሪ የተወለደባት

እርሱ ነው ተስፋችን የዓለም መድኃኒት

የሆነው ቤዛ ለሁሉ ፍጥረት!

ወልድ ተወለደልን መድኃኒዓለም

በከብቶች በረት በቤተ ልሔም!

ብርሃንህን ላክልን!

ድቅድቁ ጨለማ ተጋርዶ ከፊቴ
ሰላም ቢያሳጣኝ ካለሁበት ቤቴ
ነፍሴን ካስጨነቃት ጥንቱ ጠላቴ
በእስራቱ ኖርኩኝ ጸንቶ ፍርሃቴ
ከልጅነት ጸጋ ለይቶኝ ከአባቴ

በጸሎትህ ጠብቅ!

ከቅዱሳን አበው የሆነ ውልደትህ
የጸሎታቸው መልስ ለእናት ለአባትህ
ክብርህ እጅግ በዛ ተወደደ ሥራህ

ፍጥረት ያስደሰተ የውልደትህ ዜና
ገና ሕፃን ሳለህ የጀመርክ ምሥጋና፡፡
ጽድቅን ተጎናጽፈህ ወንጌል ተጫምተሃል
በጉብዝናህ ወራት መስቀሉን ሽተሃል፡፡

እንደ ጠዋት ጤዛ በምትረግፈው ዓለም
ልብህ ሳይሸነፍ ለምቾት ሳትደክም
ከትዳርህ ይልቅ ምንኩስናን መርጠህ
ከጫጉላ ቤት ወጥተህ በረኃ ተገኘህ፡፡

ፍቅር ግን እርሱ ነው!

ፍቅር ግን ምንድነው? ብዬ ስጠይቀው
ሁሉም ሊያብራራልኝ ሊገልጸው አቃተው!
ፍቅር ግን እርሱ ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወሰብእ የሆነው
ራሱን በመስቀል ለእኛ ሲል የሰዋው!

ፍቅር ኃያል!

ፍቅር ኃያል ፍቅር ደጉ

ወልድን ሳበው ከጸባኦት ከማዕረጉ
ፍቅር ደጉ ወልድን ሊያነግሥ በመንበሩ

በአንድ ጥለት በየዘርፉ በአንድ ጸና ማኅበሩ

ቃልም ከብሮ የዘውድ አክሊል ተቀዳጅቶ

ከምድር ላይ ከፍ…ከፍ…ከፍ…ብሎ ታይቶ

ተሠየመ በመስቀል ላይ…የነገሥታት ንጉሥ አብርቶ

በዚያች ልዩ ዕለት…ቀን ቡሩክ ቀን ፈራጅ

በዓለ ሢመቱ ሲታወጅ

ኀዘኑም ደስታውም በረከተ

ፍቅር ኃያል ፍቅር ሞተ!

ዳግም ሥራኝ!

የጽድቅ አበባዬ ጠውልጎ የኃጢአት ችግኜ አፈራ

አዝመራው ለምልሞ በለሱም የጎመራ

ለዓለም ሳጎበድድ  ጊዜዬን የጨረስኩ

በኃጢአት ብል ተበልቼ ባዶ ሆኜ የቀረሁ

ክርስትናዬን በነጠላ የሸፈንኩ

የራሴ ምሶሶ  እያለ ጉድፍ ለማውጣት የሮጥኩ

እኩይ ግብሬ ጸጽቶኝ በንስሓ ያልታጠብኩ

ማይኪራህ

ከሌሊት ወፍ በመዓልቱ:
…… እልፍ እንቁላል ሊሰበሰብ፣
የወንዱ ጽንስ እንዲገፋ
…… ከበቅሎው ወተት ሊታለብ፤
ከማር ቀፎ የዝንብ መንጋ
…… አውሬው ጓዳ ገብቶ እንዲያድር፣
የተፈጥሮ ሕጉን ስቶ
…… ያለቦታው እንዲሰደር፤

የትዕግሥት ፋና

ኢዮብ ጻድቅ ሰው ነው

ምክር የመከረ

ኢዮብ ፍጹም ሰው ነው

የትዕግሥት ፋና

በገድል የከበረ!

በፍቅር ተቀበለኝ!

ኃጢአቴን ደምስሶ ወገኑ ሊያደርገኝ

ኢየሱስ ክርስቶስ በፍቅር ተቀበለኝ

ይህን የዓለም መድኅን የበጐች እረኛ

የድንግል ማርያም ልጅ የእውነት መገኛ

ከአብ የተላከ ለአዳም ዘር ሁሉ እንዲሆን መዳኛ