በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ -  ማኅበረ ቅዱሳን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ማኅበሩ
    • ማእከላት
      • ሰሜን አሜሪካ
      • አውሮፓ
      • ሩቅ ምሥራቅ
      • ደቡባዊ አፍሪካ
      • የካናዳ ማእከል
      • አዲስ አበባ ማእከል
        • የወርሃዊ አስተዋጽኦ መሰብሰቢያ
    • ኅትመት እና ሚዲያ
      • ሐመር እና ስምዐ ጽድቅ
      • ማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ
      • የማኅበረ ቅዱሳን ዩቲዉብ
      • መጽሔተ ተልዕኮ
      • ማእከለ ሥዕላት
        • ካሜራው ምን ይላል
        • የቅዱሳት ሥዕላት ማኅደር
  • ትምህርቶች
    • የርቀት ትምህርት
    • ስብከት
    • መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች
  • ግቢ ጉባኤ
  • ሌሎች ድረ ገጾች
    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤት ድረ ገጽ
    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ድረ ገጽ
    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረ ገጽ
  • ቋንቋ
    • አማርኛ
    • ትግርኛ
    • ወላይትኛ
    • ሲዳምኛ
    • Affan Oromo
    • English
  • ያግኙን
  • Click to open the search input field Click to open the search input field Search
  • Menu Menu

ሦስቱ ነገሥታት

You are here: Home1 / ክርስቲያናዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር2 / ሦስቱ ነገሥታት

ሦስቱ ነገሥታት

ዲያቆን ተስፋዬ ቻይ

ታኅሣሥ ፳፰ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

ኢየሩሳሌም ከተማ ከወትሮው በተለየ መልኩ የፍርሃት ድባብ ተንጸባርቆባታል፤ በንጉሥ ሄሮድስ ቤተ መንግሥት ዙሪያ በሠራዊቱና በቤተ መንግሥቱ የቅርብ ሰዎች የሰሞኑ ወሬ የሦስቱ ነገሥታት ጉዳይ ነው፡፡ ከሩቅ ምሥራቅ ሠራዊቶቻቸውን አስከትለው የመጡት  ማንቱሲማር፣ በዲዳስፋ፣ እና ሜልኩ የተባሉ ነገሥታት በእስራኤል ምድር መምጣታቸው ብቻ ሳይሆን ተወልዷል ለተባለው ንጉሥ እጅ መንሻ ለመስጠት እንደመጡ መናገራቸው ንጉሥ ሄሮድስን ቅር አሰኝቶታል፤ ፍርሃት በልቡ እንዲነግሥም አድርጎታል፡፡ (ማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ ፪፥፫)

ንጉሥ ሄሮድስ ይህንን ዜና ከሰማ በኋላ ለዓይኖቹ ሽፋሽፍት በቂ እንቅልፍን፣ ለጀርባው በቂ ዕረፍትን ከሰጠ ቀናቶች ተቆጥረዋል፡፡ ነገሥታቱ ከሩቅ ምሥራቅ ኮከብ እየመራቸው ከንጉሥ ሄሮድስ ቤተ መንግሥት ከገቡ ጊዜ አንሥቶ የተወለደውን ንጉሥ አግኝተው ከአባቶቻቸው በአደራ የተረከቡትን ሥጦታ ለመስጠት ንጉሡንም ለማየት እጅግ ጓጉተዋል፡፡ ከማረፊያ ቤት እንዲቀመጡ ከተደረገ በኋላ ንጉሥ ሄሮድስ መምህራራን አስጠርቶ በእስራኤል ሀገር ይወለዳል ስለተባለው ንጉሥ የተነገሩ ትንቢቶች ካሉና የትውልድ ቦታውን እንዲነግሩት ጠየቃቸው፤ ሊቃውንቱ፣ ከአስፈሪውና ከጨካኙ ንጉሥ ሄሮድስ ዘንድ ቀርበው የተጠየቁትን ጥያቄ ለመመለስ በመጻሕፍት የተጻፉትን ማስታወስ ጀመሩ፤ ከዚያም ስለሚወለደው ንጉሥ በነቢዩ ሚክያስ ‹‹አንቺ ቤተ ልሔም የይሁዳ ምድር ከይሁዳ ምድር፣ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ  መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው›› አሉት፡፡  (ማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ ፪፥፮)

ንጉሥ ሄሮድስ ሦስቱን ነገሥታት ከእንግዳ ማረፊያ ቤት አስጠርቶ ‹‹… ይወለዳል የተባለው ንጉሥ በቤተ ልሔም ነው፤ ስለዚህ ወደዚያ ሂድ! ነገር ግን ካገኛችሁት ለእኔም ንገሩኝ፤ እኔም እሰግድለታለው›› አለ… (ማቴ.፪፥፯-፰) ሦስቱ ነገሥታት አመስግነው በተነገራቸው መሠረት ጉዞ ወደ ቤተ ልሔም አደረጉ…፤ በጉዟቸው ወቅት ከሀገራቸው ሲመጡ በሰማይ እያበራ ይመራቸው የነበረው የሚያበራ ኮከብ ዳግመኛ ታያቸው፤ ከዚያም አቅጣጫውን እየመራ ወደ ቤተ ልሔም ወሰዳቸው …. ፤ ቤተ ልሔም ከተማ ትሕትና በአካል ገዝፎ የታየባት ድንቅ ሥፍራ ናት፡፡ ከኢየሩሳሌም ከተማ ስምንት ኪሎ ሜትር ርቃ በስተደቡብ የምትገኝ ከተማ ናት፤ ቤተ ልሔም የቀድሞ ስሟ ኤፍራታ ይባላል፤ ጸዋሪተ ፍሬ (ፍሬን የያዘች) ማለት ሲሆን ቤተ ልሔም ማለት ደግሞ የእንጀራ ቤት ማለት ነው፤ እውነትም የእንጀራ ቤት ‹‹.. የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም…›› በማለት እንደተናገረው፤ ያውም በልተው የማይራቡት የሕይወት እንጀራ መድኅነ ዓለም ክርስቶስ የተወለደባት ቅዱስ ሥፍራ፡፡ በቤተ ልሔም ንጉሥ ዳዊት ተወልዶባታል፤ ያዕቆብ ሚስቱ ራሔልን ባረፈች ጊዜ የቀበራት በዚሁ ሥፍራ ነው፡፡ (ዮሐ.፮፥፴፭)

ከተማዋ መግቢያ ሲደርሱ ከተማዋ በብርሃን ተሞልታለች፡፡ ልብን በሐሤት የሚሞላ ልዩ ድባብ ይንጸባረቅበታል፤ ኮከቡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደበት በኤፍራታ ዋሻ ከእንስሳቱ ማደሪያ አመለከታቸውና ተሠወረ፤ ሦስቱ ዕድለኞች ነገሥታት በጽናት ተጉዘው የተወለደውን ንጉሥ በማግኘታቸው እጅግ ተደሰቱ፤ ሕፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ከንጽሕተ ንጹሓን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር አገኙት፤ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ፍጥረታቱን በቸርነቱ የሚመግብን ፈጣሪያችንን ታቅፋው አገኙ፤ እንደገቡም ለነገሥታት ንጉሥ ለክርስቶስ ሰገዱለት፤ ከዚያም ይዘው የመጡትን እጅ መንሻ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ ሌሎችንም ሥጦታዎች ሰጡት፤ የልባቸው መሻት በመፈጸሙ በጣም ተደሰቱ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በሌሊተ ተገልጾ በመጡበት ሳይሆን በሌላ መንገድ እንዲመለሱ ነገራቸው፤ ሦስቱ ነገሥታት ሲመጡ ረጅም ጊዜ የፈጀባቸውን መንገድ በአጭር ቀን ተመለሱ፤ ሲመጡ ‹‹የተወለደው ንጉሥ የታለ›› እያሉ ነበር፤ ሲመለሱ ‹‹አገኘነው›› እያሉ ተመለሱ፤ ሲመጡ ምድራዊ ንጉሥ መስሏቸው ነበር፤ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነገሥታትን የሚሾም ንጉሥ እንደሆነ አምነው ተመለሱ፡፡

ስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

Search Search

አዳዲስ ጽሑፎች

  • “ደቀ መዛሙርት የቤተ ክርስቲያን ደጀን ናቸው።” ሲሉ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ተናገሩ።
  • በዓለ ደብረ ታቦር
  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በማስጠበቅ ሥርዓቷን ለትውልድ እናስተላልፍ !(መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን )
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን ምክንያት አድርገው መልእክት አስተላለፉ።
  • የሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና የብፁዕ  አቡነ ጎርጎርዮስ መታሰቢያ መርሐ ግብር ተካሄደ
  • ቅድስት ኢየሉጣና ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ
  • እስመ ለመላእክቲሁ ይኤዝዞሙ በእንቲአከ/ መላእክቱን ስላንተ ያዛቸዋል. (መዝሙር ፺፥፲፩)
  • በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መመረቃቸው ተገለጸ።
  • መጽሔተ ተልእኮ
  • ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ ቋንቋዎች የመዝሙር አልበሞችን በማዘጋጀት ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገለጸ
  • አብርሃም ርእየ ፫ተ እደወ፤ በዛቲ ዕለት ምሥጢረ ሥላሴ ዜነወ።
  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  • ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
  • ዘመነ ክረምት
  • “መሠረተ ሃይማኖት” የተባለ የልጆች መጽሐፍ የፊታችን እሑድ እንደሚመረቅ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ገለጸ

የጽሑፎች ማውጫ – በወራት

© Mahibere Kidusan - All Rights Reserved. Website by MK-IT
  • Link to Facebook
Link to: አብረን እንዘምር! Link to: አብረን እንዘምር! አብረን እንዘምር! Link to: ‹‹ሚስቶች ሆይ፥ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ተገዙ›› (ኤፌ.፭፥፳፪) Link to: ‹‹ሚስቶች ሆይ፥ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ተገዙ›› (ኤፌ.፭፥፳፪) ‹‹ሚስቶች ሆይ፥ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ...
Scroll to top