የከተራ በዓል ቅድመ ዝግጅት
ጥር 11 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የከተራ በዓልን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረትና ግቢ፤ ታቦታት በሚያልፉባቸው ጎዳናዎችና አደባባዮች ማኅበራትና ወጣቶች ተሰባስበው የተለያዩ ኅብረ ቀለማትን በመጠቀም በማስዋብ ላይ ይገኛሉ፡፡
በተዘዋወርንባቸው ቦታዎች ሁሉ ወጣቶቹ በጥድፊያ ላይ ናቸው፡፡
በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ግቢውን በማስዋብ ላይ ከሚገኙት ወጣቶች አንዱ ስለ አገልግሎታቸው ላቀረብንለት ጥያቄ ሲመልስ “የጥምቀት ክብረ በዓል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የእምነታችን መገለጫ ከሆኑት ዓበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ በረከት እንድናገኝ፤ ታቦታት በሰላም ከመንበራቸው ወጥተው በሰላም እንዲመለሱ ዓውደ ምሕረት፤ ጎዳናዎችና አደባባዮችን ምንጣፍ በማንጠፍ፤ ምእመናንን በማስተናገድ በዓሉን በድምቀት እንድናከብር በየዓመቱ ተሰባስበን እናገለግላለን” ብሏል፡፡
በተዘዋወርንባቸው ቦታዎች የያዝናቸውን ፎቶ ግራፎች እነሆ፡-