ሐዊረ ሕይወት ማለት…
ይህ ሁለት ቃል ተናቦ ፫ ሱባዔ (፳፩) ትርጉምን ይሰጠናል።
፩. ቃል በቃል የሕይወት ጉዞ ማለት ነው።
፪. የሕይወት ኑሮ ማለት ይሆናል።
“ሕይወት እንተ አልባቲ ሞት = ሞት የሌለባት የሕይወት ፍሬ/ኑሮ።” ዕዝ. ሱቱ. ፭፥፲፫
ደግሞም “ይኄይስ መዊት እመራር ሕይወት = ከመራር ኑሮ ሞት ይሻላል።” ሢራ ፴፥፲፯
፫. የመዳን ጉዞ፣ ወይም የደኅንነት ጉዞ፣
“ዛቲ ይእቲ ቀዳሚት ሕይወት = ይህች የመጀመሪያዋ ትንሣኤ ድኅነት ናት።” ራእ ፳፥፭
ደግሞም “መጻእኪ ለሕይወትኪ = ለሕይወትሽ፣ ለደኅንነትሽ መጣሽ።” ዮዲ. ፲፮፥፫
፬. የፈውስ ጉዞ፣ ወይም የጤንነት ጉዞ፣
“ወሰሚዖሙ ሕይወተ እሙታን = ከሙታን ተለይቶ መነሣትንም በሰሙ ጊዜ” ግ.ሐዋ. ፲፯፥፴፪
፭. የመኖር ጉዞ፣
፮. የመሥራት ጉዞ፣
“ዘለዓለም ዘየሐውር በጽድቅ = ለዘለዓለም ሕግን የሚሠራ” ኢሳ. ፴፫፥፲፭
፯. የዕድሜ ልክ ጉዞ
“እሴብሖ ለእግዚአብሔር በሕይወትየ = በሕይወቴ ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ።” መዝ ፻፵፭፥፪
፰. የትንሣኤ ወይም የመታደስ ጉዞ፣
፱. የጸሎተ ምሕላ ወይም የመማፀን የምጥንታ ጉዞ
፲. የደስታ ጉዞ “ሐይወ ልቡ ወነፍሱ ለያዕቆብ = የያዕቆብ ልቡናው ሰውነቱ ደስ አላት ታደሰች።” ዘፍ ፵፭፥፳፮
፲፩. የነፍስ ጉዳይ ጉዞ፣ ወይም የሰውነት ጥበቃ ጉዞ
፲፪. መልአካዊ ጉዞ
፲፫. ክርስቶሳዊ ጉዞ
፲፬. የአካላዊ ሕይወት፣ የልብሰ ሕይወት፣ የእሳተ ሕይወት፣ የብርሃነ ሕይወት፣ የመንፈስ ቅዱስ ጉዞ፣
፲፭. የክርስቲያን ጉዞ
፲፮. የቀና ልብ ወይም የመልካም ሐሳብ ጉዞ
፲፯. የነፍስ ዕውቀት ማለት የብልኅነት ጉዞ
፲፰. የትዕግሥት፣ የጸጥታ ጉዞ
፲፱. ትምህርታዊ ጉዞ
፳. የመንፈሳዊ ፈቃድ ጉዞ
፳፩. የምክር፣ የጉባኤ ጉዞ
፳፪. የሥልጣናዊ ምርጫ የችሎታ ጉዞ ማለት ሁሉ ነው።