ዝርዝር ርባታ

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! ባለፈው የትምህርታችን ክፍለ ጊዜ የ ‹‹ሀ፣ አ፣ ወ እና የ›› የሚያመጡት የርባታ ለውጥ በግሥ ርባታ አስተምረናችሁ ነበር፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ለሰጠናችሁ መልመጃ ምላሽና ስለ ዝርዝር  ርባታ እንመለከታለን፤ በጥሞና ተከታተሉን!

ቅድስት

ቅድስት ማለት ‹የተለየች፣ የነጻች፣ የከበረች› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የጀመረባት፣ ልዩ፣ የተቀደሰች፣ የከበረች፣ ንጹሕ፣ ክቡር በሚሆን በጌታችን የተጾመች መሆኗን ያመላክታል፡፡ ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል የተገለጠች ስትሆን፣ አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡ (ማቴ.፬፥፪)

‹‹ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊትም ጾመ›› (ማቴ.፬፥፪)

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁ? የመንፈቀ ዓመቱ ትምህርት ተጠናቆ ፈተና ተፈትናችሁ ጥሩ ውጤት እንዳመጣችሁ ተስፋችን ነው፤ በርቱ!
ልጆች! ለዛሬ የምንማረው ስለ ዐቢይ ጾም ነው፤ ዐቢይ ማለት ታላቅ ማለት ነው፤ አባቶቻችን በሠሩልን ሥርዓት መሠረት ከሰባት ዓመት በላይ የሆኑ ክርስቲያኖች ሁሉ እንዲጾማቸው የታወጁ ሰባት አጽዋማት አሉ፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ አንዱ ዐቢይ ጾም ነው::

ፈቃደ እግዚአብሔር

በሰዎች ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር ክቡር ፍቃድ አለ፤ እነዚህም ሁለት ፍቃዳት ናቸው፡፡ አንደኛው ግልጽ ፈቃድ ሲባል ሁለተኛው ደግሞ ስውር ፈቃድ ይባላል፡፡ ግልጽ ፍቃዳት የሚባሉት በመጽሐፍ ተጽፈው የምናነባቸው ናቸው፤ በሕግ መልክ በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን የተቀመጡልን ትእዛዛቱ እንድንሰማቸው፣ እንድንማራቸው፣ እንድንኖራቸው የተሰጡትን ነው፡፡ መጽናናትን፣መረጋጋትን ገንዘብ የምንዳርባቸው፣ ተግሣጽንና ምክርን የምንሸምትባቸው ገባያችን ናቸው፡፡