ዝርዝር  ርባታ-ክፍል ሁለት

መምህር በትረማርያም አበባው

መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! ባለፈው የትምህርታችን ክፍለ ጊዜ የግሥ ርባታ የመጀመሪያውን ክፍል አቅርበንላችኋል፤ እንደተረዳችሁት ተስፋ እንዳርጋለን፤ ለዛሬ ደግሞ ሁለተኛውን ክፍል እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፤ በጥሞና ተከታተሉን!

ይእቲ ውእቱን ስትወድ፦

አፍቀረቶ፤ወደደችው

ታፈቅሮ፤ትወደዋለች

ታፍቅሮ፤ትወደው ዘንድ

ታፍቅሮ፤ትውደደው

ይእቲ ውእቶሙን ስትወድ፦

አፍቀረቶሙ፤ወደደቻቸው

ታፈቅሮሙ፤ትወዳቸዋለች

ታፍቅሮሙ፤ትወዳቸው ዘንድ

ታፍቅሮሙ፤ትውደዳቸው

ይእቲ ይእቲን ስትወድ፦

አፍቀረታ፤ወደደቻት

ታፈቅራ፤ትወዳታለች

ታፍቅራ፤ትወዳት ዘንድ

ታፍቅራ፤ትውደዳት

ይእቲ ውእቶንን ስትወድ፦

አፍቀረቶን፤ወደደቻቸው

ታፈቅሮን፤ትወዳቸዋለች

ታፍቅሮን፤ትወዳቸው ዘንድ

ታፍቅሮን፤ትውደዳቸው

ይእቲ አነን ስትወድ፦

አፍቀረተኒ፤ወደደችኝ

ታፈቅረኒ፤ትወደኛለች

ታፍቅረኒ፤ትወደኝ ዘንድ

ታፍቅረኒ፤ትውደደኝ

ይእቲ ንሕነን ስትወድ፦

አፍቀረተነ፤ወደደችን

ታፈቅረነ፤ትወደናለች

ታፍቅረነ፤ትወደን ዘንድ

ታፍቅረነ፤ ትውደደን

ውእቶን ውእቱን ሲወዱ፦

አፍቀራሁ፤ወደዱት

ያፈቅራሁ፤ይወዱታል

ያፍቅራሁ፤ይወዱት ዘንድ

ያፍቅራሁ፤ይውደዱት

ውእቶን ውእቶሙን ሲወዱ፦

አፍቀራሆሙ፤ወደዷቸው

ያፈቅራሆሙ፤ይወዷቸዋል

ያፍቅራሆሙ፤ይወዷቸው ዘንድ

ያፍቅራሆሙ፤ይውደዷቸው

ውእቶን አንትንን ሲወዱ፦

አፍቀራክን፤ወደዷችሁ

ያፈቅራክን፤ይወዷችኋል

ያፍቅራክን፤ይወዷችሁ ዘንድ

ያፍቅራክን፤ይውደዷችሁ

ውእቶን አነ ሲወዱ፦

አፍቀራኒ፤ወደዱኝ

ያፈቅራኒ፤ይወዱኛል

ያፍቅራኒ፤ይወዱኝ ዘንድ

ያፍቅራኒ፤ይውደዱኝ

ውእቶን ንሕነን ሲወዱ፦

አፍቀራነ፤ወደዱን

ያፈቅራነ፤ይወዱናል

ያፍቅራነ፤ይወዱን ዘንድ

ያፍቅራነ፤ይውደዱን

አንተ ውእቱን ስትወድ፦

አፍቀኮ/አፍቀርካሁ፤ወደድከው

ታፈቅሮ/ታፈቅራሁ፤ትወደዋለህ

ታፍቅሮ/ታፍቅራሁ፤ትወደው ዘንድ

አፍቅሮ/አፍቅራሁ፤ውደደው

አንተ ውእቶሙን ስትወድ፦

አፍቀርኮሙ/አፍቀርካሆሙ፤ወደድካችው

ታፈቅሮሙ/ታፈቅራሆሙ፤ትወዳቸዋለህ

ታፍቅሮሙ/ታፍቅራሆሙ፤ትወዳቸው ዘንድ

አፍቅሮሙ/አፍቅራሆሙ፤ውደዳቸው

አንትሙ ውእቶሙን ስትወዱ፦

አፍቀርክምዎሙ፤ወደዳችኋቸው

ታፈቅርዎሙ፤ትወዷቸዋላችሁ

ታፍቅርዎሙ፤ትወዷቸው ዘንድ

አፍቅርዎሙ፤ውደዷቸው

አንትሙ ይእቲን ስትወዱ፦

አፍቀርክምዋ፤ወደዳችኋት

ታፈቅርዋ፤ትወዷታላችሁ

ታፍቅርዋ፤ትወዷት ዘንድ

አፍቅርዋ፤ውደዷት

አንትሙ ውእቶንን ስትወዱ፦

አፍቀርክምዎን፤ወደዳችኋቸው

ታፈቅርዎን፤ትወዷቸዋላችሁ

ታፍቅርዎን፤ትወዷቸው ዘንድ

አፍቅርዎን፤ውደዷቸው

አንትሙ አነን ስትወዱ፦

አፍቀርክሙኒ፤ወደዳችሁኝ

ታፈቅሩኒ፤ትወዱኛላችሁ

ታፍቅሩኒ፤ትወዱኝ ዘንድ

አፍቅሩኒ፤ውደዱኝ

አንትሙ ንሕነን ስትወዱ፦

አፍቀርክሙነ፤ወደዳችሁን

ታፈቅሩነ፤ትወዱናላችሁ

ታፍቅሩነ፤ትወዱን ዘንድ

አፍቅሩነ፤ውደዱን

ይእቲ አንተን ስትወድ፦

አፍቀረተከ፤ወደደችህ

ታፈቅረከ፤ትወድሃለች

ታፍቅርከ፤ትወድህ ዘንድ

ታፍቅርከ፤ትውደድህ

ይእቲ አንትሙን ስትወድ፦

አፍቀረተክሙ፤ወደደቻችሁ

ታፈቅረክሙ፤ትወዳችኋለች

ታፍቅርክሙ፤ትወዳችሁ ዘንድ

ታፍቅርክሙ፤ትውደዳችሁ

ይእቲ አንቲን ስትወድ፦

አፍቀረተኪ፤ወደደችሽ

ታፈቅረኪ፤ትወድሻለች

ታፍቅርኪ፤ትወድሽ ዘንድ

ታፍቅርኪ፤ትውደድሽ

ይእቲ አንትንን ስትወድ፦

አፍቀረተክን፤ወደደቻችሁ

ታፈቅረክን፤ትወዳችኋለች

ታፍቅርክን፤ትወዳችሁ ዘንድ

ታፍቅርክን፤ትውደዳችሁ

ውእቶን ይእቲን ሲወዱ፦

አፍቀራሃ፤ወደዷት

ያፈቅራሃ፤ይወዷታል

ያፍቅራሃ፤ይወዷት ዘንድ

ያፍቅራሃ፤ይውደዷት

ውእቶን ውእቶንን ሲወዱ፦

አፍቀራሆን፤ወደዷቸው

ያፈቅራሆን፤ይወዷቸዋል

ያፍቅራሆን፤ይወዷቸው ዘንድ

ያፍቅራሆን፤ይውደዷቸው

ውእቶን አንተን ሲወዱ፦

አፍቀራከ፤ወደዱህ

ያፈቅራከ፤ይወዱሃል

ያፍቅራከ፤ይወዱህ ዘንድ

ያፍቅራከ፤ይውደዱህ

ውእቶን አንትሙን ሲወዱ፦

አፍቀራክሙ፤ወደዷችሁ

ያፈቅራክሙ፤ይወዷችኋል

ያፍቅራክሙ፤ይወዷችሁ ዘንድ

ያፍቅራክሙ፤ይውደዷችሁ

ውእቶን አንቲን ሲወዱ፦

አፍቀራኪ፤ወደዱሽ

ያፈቅራኪ፤ይወዱሻል

ያፍቅራኪ፤ይወዱሽ ዘንድ

ያፍቅራኪ፤ይውደዱሽ

አንተ ይእቲን ስትወድ፦

አፍቀርካ/አፍቀርካሃ፤ወደድካት

ታፈቅራ/ታፈቅራሃ፤ትወዳታለህ

ታፍቅራ/ታፍቅራሃ፤ትወዳት ዘንድ

አፍቅራ/አፍቅራሃ፤ውደዳት

አንተ ውእቶንን ስትወድ፦

አፍቀርኮን/አፍቀርካሆን፤ወደድካቸው

ታፈቅሮን/ታፈቅራሆን፤ትወዳቸዋለህ

ታፍቅሮን/ታፍቅራሆን፤ትወዳቸው ዘንድ

አፍቅሮን/አፍቅራሆን፤ውደዳቸው

አንተ አነን ስትወድ፦

አፍቀርከኒ/አፍቀርካኒ፤ወደድከኝ

ታፈቅረኒ/ታፈቅራኒ፤ትወደኛለህ

ታፍቅረኒ/ታፍቅራኒ፤ትወደኝ ዘንድ

አፍቅረኒ/አፍቅራኒ፤ውደደኝ

አንተ ንሕነን ስትወድ፦

አፍቀርከነ/አፍቀርካነ፤ወደድከን

ታፈቅረነ/ታፈቅራነ፤ትወደናለህ

ታፍቅረነ/ታፍቅራነ፤ትወደን ዘንድ

አፍቅረነ/አፍቅራነ፤ውደደን

አንትሙ ውእቱን ስትወዱ፦

አፍቀርክምዎ፤ወደዳችሁት

ታፈቅርዎ፤ትወዱታላችሁ

ታፍቅርዎ፤ትወዱት ዘንድ

አፍቅርዎ፤ውደዱት

ውድ አንባብያን! ከላይ የተመለከትናቸውን የግሥ ርባታዎች እንደተረዳችሁ ተስፋ እንናደርጋለን፤ የቀሩትን ዝርዝር ርባታዎች ደግሞ በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡

ይቆየን!