“እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።”

፩ኛ ዜና መዋዕል ፲፮፥፲፩ 

በዲያቆን በረከት አዝመራው

እግዚአብሔርን መፈለግ እና ወደ እርሱ ሰው ሁሉ መቅረብ ይገባዋል? ወይስ ጥቂቶች ብቻ የሚጣጣሩበት ሕይወት ነው ብለን እንደፈለግን መሆን ይቻለናል? በውኑ አእምሮ ያለው ፍጡር ያስገኘውን ፈጣሪውን ከመፈለግ፣ ከፈጣሪው ጋር ኅብረት ከመፍጠር እና የተፈጠረበትን ዓላማ ከመፈጸም የበለጠ ምን ታላቅ ተግባር አለው?

መልካም አባት ሁልጊዜ ለልጁ ጥሩ ነገርን እንደሚያስብ እና እንደሚያደርግ የታወቀ ነው። በዚህም ምክንያት “ጤነኛ” ልጅ ሁሉ አባቱን ይወዳል:: ካለማወቅ እና ከድካም የተነሳ አንዳንድ ጊዜ ቢሳሳትም በአብዛኛው ግን የአባቱን ትእዛዝ ይጠብቃል:: ታዲያ እግዚአብሔር “ከልብ ለሚፈልጉኝ ሁሉ እገኛለሁ፤ ከምድራውያን ወላጆች ጋር የማልነጻጸር መልካም አባት ነኝ፤ ለሚወዱኝ ዓይን ያላየው፣ ጆሮ ያልሰማው፣ በሰው ልብ ያልታሰበ ታላቅ ሥጦታን እሰጣለሁ” (፪ኛ ዜና መዋዕል ፲፭፥፪፣ ማቴ. ፯፥፲፩፣ ፩ኛ ቆሮ. ፪፥፱) እያለ ዘወትር እየተጣራ፤ ሰዎች ወደ እርሱ በሙሉ ልብ ለመቅረብ ፈቃዳችን የሚደክመው እና ዳተኛ የምንሆነው ለምንድን  ነው? Read more

ሕይወትን በማስተዋልና በዓላማ ስለመምራት

ዲያቆን መዝገቡ ዘወርቅ

“ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፤ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፡፡” (1ኛ ቆሮ. 9፥26)

በማስተዋልና በዓላማ የሚመራ፣ ወደ አንድ አቅጣጫ የተሰበሰበ ኑሮ (Focused Life) የሰውን ልጅ በሥጋም በነፍስም ስኬታማ የሚያደርግ እና በተፈጥሮአችን የተሰጠንን አቅም ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳን የኑሮ መሥመር ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ሕይወታችንን እግዚአብሔር ወደሚደሰትበት መልካም አቅጣጫ ለመምራት የሚጠቅሙንን መንገዶች ለመዘርዘር እንሞክራለን፡፡ Read more

ጥቂት ስለ ነጻነት

በዲያቆን በረከት አዝመራው

ከጥቂት ወራት በፊት ነው፤ በተሳፈርኩበት ታክሲ ውስጥ በአለባበሳቸውም ሆነ በአነጋገራቸው ወጣ ያሉ ሦስት ወጣቶች አብረው ተሳፍረዋል። እነዚህ ወጣቶች ድምጻቸውን ለቀቅ አድርገው አብዛኛውን ተሳፋሪ የሚረብሽና አንገት የሚያስደፋ ንግግር ይነጋገራሉ።ድምጻቸው ከፍ ከማለቱ የተነሳ በታክሲው ውስጥ ያለው ሰው ሳይፈልግም ቢሆን እነርሱን ከመስማት ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ አልነበረውም። Read more