• እንኳን በደኅና መጡ !

አዲስ ዓመት እና ግቢ ጉባኤያት

ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፪፲፯ ዓ.ም በእንዳለ ደምስስ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው በረከቶች መካከል ጊዜአቸውን ጠብቀው የሚፈራረቁ ወቅቶች ይገኙበታል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ” (መዝ. ፷፬፥፲፩) እንዲል የበጋውን፣ የበልጉንና ክረምቱን ወቅቶች አፈራርቆ መጸው  ደግሞ ምድር በአረንጓዴና በልዩ ልዩ አበባዎች በምትደምቅበት በመስከረም ወር ሰዎችም የእግዚአብሔርን ቸርነት አድንቀውና አዲስ ተስፋን ሰንቀው “እንኳን አደረሳችሁ” በማለት ዓመቱ […]

ግሸን ደብረ ከርቤ

‹‹ግሸን ማርያም›› በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ደብር ናት፤ ይህች ደብር በሐይቅና በመቅደላ፣ በደላንታ፣ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ የምትገኝ አንድ መግቢያ በር ብቻ ያላት ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ናት፡፡ በ፲፩ኛው ክፍለ ዘመን ዐፄ ላሊበላ ከቋጥኝ ድንጋይ ፈልፍለው ‹‹እግዚአብሔር አብ›› የተሰኘ ቤተ ክርስቲያን በዚሁ ቦታ ሲያሠሩ ‹‹ደብረ እግዚአብሔር›› ተብላ ተሰየመች። ብዙም ሳይቆይ ‹‹ደብረ ነገሥት›› ተባለች። ከዚያም የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት […]

ቅዱስ መስቀል

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን፡፡ መስቀል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ኃጢአት ያስወግድ ዘንድ በቀራንዮ አደባባይ በመስቀል ላይ መሰቀሉን፣ ተጣልተው የነበሩትን ሰባቱ መስተፃርራን (ሰውና እግዚአብሔርን፣ መላእክትና ሰውን፣ ነፍስና ሥጋን፣ ሕዝብና አሕዛብን) ያስታረቀበት ነው፡፡ በቀራንዮ “ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም“ (ዮሐ. ፲፭፥፲፫) እንዲል፡፡ በዚህም የመዳን ምልክት መሆኑ የተረጋገጠበት በክርስቶስ […]

ማስታወቂያ

ጉባኤ-ቃና መጽሔት-ነሐሴ-2016-ዓ.ም

ጉባኤ-ቃና መጽሔት-ነሐሴ-2016-ዓ.ም

መልእክትዎን ይላኩልን