በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን (ገላ. 5÷1)
በዲ/ን ታደለ ፈንታው
ይህ መልእክት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በምዕራፍ አምስት ቁጥር አንድ ላይ የተቀመጠ ኀይለ ቃል ነው፡፡ የገላትያ ሰዎች አስቀድመው እግዚአብሔርን ያወቁ፣ ክፉ ከሆነው ከዚህ ዓለም የሥጋ ዐሳብ ያመለጡ፣ በሃይማኖት የሚኖሩ፣ ከክፋት የራቁ፣ መልካም የሆነውን ነገር ፈትነው የተቀበሉ፣ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ የተጠሩ፣ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ደፋ ቀና የሚሉ፣ ሌትና ቀን በቤተ መቅደሱ በጸሎት ሁሉ የሚተጉ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ አስቀድመው በተጠሩበት መጠራት መመላለስ ሲያቅታቸው ከመንፈሳዊው ነገር ይልቅ ትኩረታቸው ጉጉታቸውና አላማቸው ሥጋዊ ነገር ላይ ሲያርፍ ትውክልታቸው እግዚአብሔር መሆኑ ቀርቶ ምድራዊ ነገር ሲሆን የሚፈሩት ነፍስንና ሥጋን አንድ አድርጎ በገሀነም የሚቀጣውን እግዚአብሔርን ሳይሆን ጊዜ የሰጣቸውን ወገኖች ሆኖ ቢያገኛቸው እንዲህ የሚል መልእክት ጻፈላቸው፡፡ ‹‹በክርስቶስ እናንተን ከጠራች ከእርሱ ወደልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ እርሱ ግን ሌላ አይደለም የሚያናውጧችሁ የክርስቶስን ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንድ ወገኖች አሉ እንጂ›› (ገላ.1፥6) በማለት ይጽፍላቸዋል፡፡ ክርስቲያኖችን ሁል ጊዜ በሚያባብል ቃል መቅረብ አስፈላጊ አይደለም፡፡ Read more