ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ አገልግሎቱን በማጠናከር በግቢ ጉባኤያት ላይ ውጤታማ ሥራ ለመሥራትና ብቁ አገልጋዮችን ለማፍራት ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቶቹን ለማስፈጸም ይረዳውም ዘንድ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ትኬት ሽያጭ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በማሠራጨት ላይ ይገኛል፡፡ እርስዎም ትኬቱን በመግዛት ትውልድን ለመቅረጽ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አሻራዎን ያኑሩ፡፡
ጉባኤ-ቃና መጽሔት-ነሐሴ-2016-ዓ.ም
ጉባኤ-ቃና መጽሔት-ነሐሴ-2016-ዓ.ም
“የቀደመውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ” (፪ቆሮ. ፭፥፲፰)
እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን፡፡ መልካም አዲስ ዓመት! በኢትዮጵያውያን ዘመን አቆጣጠር የመስከረም ወር የወራት ሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ገበሬው በክረምቱ ወራት መሬቱን አልስልሶ፣ ዘሩንም ዘርቶ ምድሪቱም አደራዋን ለመመለስ በልምላሜ የምታጌጥበት ወር ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እንስሳት ለምለሙን ሣር ግጠው፣ የጠራውን ውኃ ጠጥተው ረክተው፣ አምረው የሚታዩበት […]
በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል
“ሩፋኤል” የሚለው ቃል “ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ” ማለት ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ጳጉሜን ፫ ቀን በዓሉ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል (ጦቢ. ፲፪፥፲፭)፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሩፋኤል ማለት ከዕብራይስጥ ሁለት […]
ነገረ ጳጕሜን
በመ/ር ተስፋ ማርያም ክንዴ በዚህም የመጽሐፍ ቃል መሠረት የኢትዮጵያ ሊቃውንት በዓመት ከ፲፪ቱ ወራት የተረፉትን ዕለታት ከወር ባነሱ ዑደቶች በዕለት፣ በኬክሮስ፣ በካልኢት፣ በሳልሲት፣ በራብኢት፣ በሐምሲትና በሳድሲት ሰፍረውና ቀምረው በዓመት ፭ ቀን፣ ከ፲፭ ኬክሮስ፣ ከ፮ ካልኢት አድርገው እነዚህ ዕለቶች ጳጕሜን ፲፫ኛ ወር አድርገውታል። ኢትዮጵያዊያንና ግብፃዊያን ብቸኛ የባለ ፲፫ ወር መባላቸው ግን ዕለቷ በሌሎች አልኖር ብላ ሳይሆን ሌሎች […]