መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
‹‹እግዚአብሔር ይቅርታን ይረሳልን? በቁጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን?›› (መዝ. ፸፮፥፱)
ብዙዎች በአሁኑ ሰዓት ስጋትና ጭንቀት ላይ ናቸው፤ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር ይቅርታን ይረሳልን? በቁጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን?›› ብሎ በጸሎት እንደጠየቀው አዛውንቶችም የዚህ መቅሰፍት ማብቂያ የሚቆምበትን ጊዜ በመመኘት አምላካቸው ስለምን ቸል እንዳለ ሲጠይቁ ይሰማሉ፤ ምሕረትንም እንዲያበዛልን አብዝተው ሲለምኑ ይደመጣሉ፡፡ (መዝ. ፸፮፥፱)
ደብረ ምጥማቅ
ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት “ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ፤” በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት ብዙዎች ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው እጅግ አስደናቂ ውበቷን አይተዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በደብረ ምጥማቅ የነበሩ ምእመናን ሌሎችም ብዙዎች ንጹሓን ክርስቲያኖች ይገኙበታል፡፡ (መዝ. ፵፬፥፲፪;)
ፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ
እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደህና ናችው? እግዚያብሔር ይመስገን እንዳላችሁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ልጆች! ትምህርት እንዴት ነው? ከዓለማዊው ትምህርታችሁ ጎን ለጎን እናንተን ያስተምራል እንዲሁም በምግባር ያንጻል ብለን ያሰበነውን ታሪክ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ልጆች በዚህ ዕትማችን ይዘንላችሁ የቀርብነው የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ታሪክ ነው፡፡ ከታሪኩ ብዙ እንደምትማሩ ተስፋ እናደርጋለን፤ በጽሞና እንድታነቡም ተጋብዛችኋል፤ መልካም ንባብ ይሁንላችው፡፡
በመንፈሳዊ ሕይወታችን መለወጥ ለምን ተሳነን?
እግዚአብሔር ከእኛ የመልካም ሥነ ምግባርና የሃይማኖት ፅናትን ይፈልጋል፡፡ በሃይማኖት የሚኖር ሰው አስተማሪ ሕይወት ያለው ሰው መሆን አለበት፡፡ ሃይማኖቱንም በሥራና በምግባር መግለጽ አለበት፡፡ ለዚህ ነው ጌታችን “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል፤ በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፤” መብራት የተባለው ሃይማኖትና ምግባራችን ነው፡፡ (ማቴ.፭፥፲፫-፲፮)
‹‹በንስሓ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ›› (ሕዝ.፲፰፥፴፪)
ዓለም ኃጢአተኝቱን ላለማመን ይህንን የመጣብንን መቅሠፍት (ኮሮና ቫይረስ) ‹‹እንዲህ የምትባል ሀገር ናት ያመረተችው፤ ከእንትና ቤተ ሙከራ አፈትልኮ የወጣ ቫይረስ ነው፤›› በማለት የተለያዩ የሽፍጥ ምክንያቶችን ትደረድራለች፡፡ ይሁን እንጂ ማንም ምንም ቢል እውነታው ግን ‹‹የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው›› ተብሎ እንደተጻፈ የሰው ልጅ የኃጢአት ደመወዙን ከእግዚአብሔር እጅ እየተቀበለ ነው፡፡ (ሮሜ.፮፥፳፫)
“ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ በደመና ወደሰማይ ዐረገ” (ቅዱስ ያሬድ)
ጌታችን ኢየሱስ በደመና ዐረገ መባሉ ሊቃውንት እንደሚነግሩን ደመና ክብሩና ልዕልናው በመሆኑ ነው። “ዘበእንተ ዕበይከ ትትሜሰል በደመና፤ ስለ ልዕልናህ በደመናት ትመሰላለህ” እያሉ ሊቃውንቱ ያመሰግኑታል። በሐዋርያት ሥራም “ወነሥአቶ ደመና ወዐርገ ሰማየ እንዘ እሙንቱ ይኔጽሩ ኀቤሁ፤ ደመናም ተቀበለችው፤ እነርሱም ወደእርሱ እያዩ ወደሰማይ ዐረገ” ተብሎ ተጽፏል። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊትም “ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤ እግዚአብሔር በዕልልታ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዐረገ” በማለት እንደነገረን በክብር በይባቤ መላእክት ማረጉን ያስረዳል። (ሐዋ.፩፥፱፤ መዝ.፵፮፥፭)
‹‹እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው›› (ዕብ. ፲፩፥፩)
ማንኛውም የሕይወት ውጣ ውረድ ቢያጋጥመን በእምነት ከጸናን የማናልፈው ነገር የለም፡፡ የማንዘለው የችግር እና የመከራ ግንብ፣ የማንሻገረው ባሕር እና መሰናክል አይኖርም፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በእምነት ከእግዚአብሔር ጋር ከኖርን የሚያስፈራን አንዳች ነገር አለመኖሩን ሲያስረዳ ‹‹በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሔድ፤ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል›› ብሏል፡፡ (መዝ. ፳፪፥፬)
‹‹ድኀነት››
የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ያጣውን የተፈጥሮ ጸጋ ክብር በአዲስ ተፈጥሮ እንደገና ለመታደል መብቃቱን ለመግለጽ የሚነገር ልዑል ቃል ‹‹ድኀነት›› ነው፡፡ ድኀነት የሚለው ቃል አዳም በክርስቶስ የታደለውን የሕይወተ ሥጋና ሕይወት ነፍስ፣ በረከተ ሥጋና በረከተ ነፍስ ጸጋ ወይም በሌላ አነጋገር የሞተ ሥጋና የሞተ ነፍስ ድቀት የደረሰበት አዳም በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘው ትንሣኤውና ሕይወት የሚገለጽበት ሕያው ቃል ነው፡፡
‹‹የሱራፌል አምሳላቸው ቅዱስ ያሬድ››
እግዚአብሔር አምላክን ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያሉ በመንበሩ ፊት ቆመው እንደሚያመሰግኑ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያለ በመላእክት ቋንቋ ፈጣሪውን በማመስገኑ እና ዜማውን ከእነርሱ በመማሩ በመጽሐፈ ስንክሳር ‹‹አምሳሊሆሙ ለሱራፌል፤ የሱራፌል አምሳላቸው›› ተብሏል፡፡
“ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” (ትንቢተ ዮናስ ፪፥፲)
እግዚአብሔር ከበሽታ ይፈውሳል፤ ከችግርና መከራም ይሰውራል፡፡ በየጸበል ቦታው ተጠምቀው ከኤች አይ ቪ፣ ከካንሰር እና ከሌሎች በሽታዎች የተፈወሱ ሰዎች እንዳሉ ዓይናችን እንዲሁም የሕክምና ማስረጃዎች ምስክሮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ኃያል አምላክ፤ ሥራውም ድንቅ ነው፤ ተአምራትንም ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ከእርሱ ለማግኘት እምነት ያስፈልጋል፡፡