መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ
ቅዱሳን ሐዋርያት ገድላቸው የተጻፈላቸው፣ በዓላቸው የተከበረላቸው የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ናቸው። በቤተ ክርስቲያናችን በሐምሌ ፭ ቀን በታላቅ ድምቀት በዓላቸው ከሚከበረው ሐዋርያት መካከል የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስና የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስን ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።…
ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሊጠብቁ ይገባል!
ማኅበረ ምእመናን የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ብዙ ቢሆኑም እንኳን አንድ ልብና አንድ ሐሳብ ሆነው እንዲጸልዩ፣ እንዲሰግዱ፣ እንዲያመሰግኑ፣ እንዲያስቀድሱ፣ እንዲቆርቡ እንዲሁም እንዲዘምሩ ለማድረግ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ካህናት ሲቀድሱ ምእመናን በኅበረት ተሰጥኦ ይቀበላሉ፤ በጋራ ሆነው ይጸልያሉ፤ በዓላትን በአንድነት ያከብራሉ፤ በሰንበት ጽዋ ማኅበር በአንድነት ያዘጋጃሉ፤ ቅዱሳንን በጋር ይዘክራሉ፡፡
ነገር ግን ይህን የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የሚጻረሩ ተግባራትን የሚፈጽሙ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን በድፍረት ሲገቡ መመልከት ከጀመርን ሰንብተናል፡፡ ለምሳሌ የቅዳሴ ሥርዓትን አቋርጦ መግባትና መውጣት፣ በትምህርተ ወንጌልም፣ በቅዳሴ እንዲሁም በሌሎች የጸሎት ሰዓታት ላይ ማውራት፣ ሥርዓት የሌለው አልባሳት በተለይም ሴቶቸ (አጭር እና ሰውነትን የሚያሳይ ልብስ) መልበስ…
ልደቱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
ጌታችን ኢየሱስም ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም›› ብሎ የመሠከረለት ነቢይ፣ ሐዋርያ፣ ሰማዕት ነው፡፡
‹‹ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ›› (ዘፀ.፲፥፲፰)
ጸሎት እግዚአብሔር አምላክን እንድንማጸን የሚረዳን ኃይል ነው፡፡ በተለያዩ ችግርና መከራም ሆነ በባርነት ውስጥ ያሉ ሰዎች በጸሎት አምላካቸውን በመማጸን መፍትሔም ያገኛሉ፤ ለዚህም ምሳሌ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንመልከት፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ቤተ ክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ዋጅቶ የመሠረታት፣ በክርስቶስ ክርስቲያን ለተባልን በሙሉ መሰብሰቢያችን የተቀደሰች ቤታችን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ስንልም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን፣ የክርስቲያን ወገን፣ የምእመናን አንድነት ወይንም ማኅበረ ምእመናን እንዲሁም እያንዳንዱ ምእመናን ማለታችን ነው፡፡…
ሕንጸታ ቤታ
በሀገረ ቂሣርያ፣ ኬልቄዶንያ አውራጃ የመጀመሪያዋ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የታነጸችበት ዕለት ሰኔ ፳ ‹‹ሕንጸታ ቤታ›› የተከበረ ነው፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውኀ በሦስት ድንጋዮች ቤተ ክርስቲያኗን ያነጸበት ዕለት ነውና፡፡
በፊትህ ናት
በኀምሳኛው ዕለት መንፈስ ቅዱስ ሲያድርባቸው
በ፸፪ የተለያየ ዓይነት ቋንቋቸው
ሲናገሩ ተገረሙ አሕዝቡ ሰምተው
በእግዚአብሔር ሥራ እጅግ ተደንቀው
የወንጌሉን ቃል ሲረዱ ተነክቶ ልባቸው
ሦስት ሺህ ነፍሳትም ተጠመቁ አምነው…
አባ ገሪማ ዘመደራ
…አባ ገሪማ መጽሐፍ እየጻፉ ከቆዩ በኋላ መምሸት በመጀመሩ ፀሐይ ሊጠልቅ ተቃረበ፤ ያን ጊዜም በጸሎታቸው ጽሕፈታቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ፀሐይን በቦታው እንዲቆም አደረጉ፤ በኋላም ከእጃቸው የወደቀው ብዕር ወዲያው በቅሎ፣ አቈጥቍጦ አደገ፡፡ ምራቃቸውን ትፍ ያሉበት ሥፍራም እስከ ዛሬ ድረስ ሕሙማንን ይፈውሳል፡፡
‹‹በሥጋችሁ ፈቃድ ለነጻነታችሁ ምክንያት አታድርጉላት›› (ገላ. ፭፥፲፫)
ነጻነት አለኝ ብሎ እንደ ልብ መናገር፣ ያሰቡትን ሁሉ መፈጸም አእምሮውን ያጣ ሰው መገለጫ እንጂ ጤነኝነት አይደለም፡፡ ፍጡራን እንደመሆናችን መጠን ነጻነታችን ገደብ አለው፡፡ ለነጻነቱ ገደብ የሌለው ቸርነቱ ካልከለከለው በቀር ሁሉን ማድረግ የሚችል እርሱ ልዑል አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ቀዳማዊው ሰው አዳም አምላካችን እግዚአብሔር ሲፈጥረው ነጻ አድርጎ የፈጠረው መሆኑ ባያጠያይቅም ፍጡር እንደመሆኑ መጠን ደግሞ ‹‹በገነት ካለው ዛፍ ብላ፤ ነገር ግን መልካሙንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና›› ብሎ ገደብ አስቀምጦለታል፡፡ (ዘፍ. ፪፥፲፮-፲፯)
የሐዋርያት ጾም
ሐዋርያት ወንጌለ መንግሥት እንዲስፋፋና በሕዝብም ሆነ በአሕዛብ ዘንድ አገልግሎታቸው የሠመረ እንዲሆን መንፈስ ቅዱስን በተቀበሉ በበዓለ ሃምሳ ማግሥት ጾም ጀመሩ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ በሰጣቸው ሥልጣን ድውያንን መፈወስና አጋንንትን ማውጣት እንዲሁም የተለያዩ ገቢረ ተአምራትን ይፈጽሙ ዘንድ ጸሎትና ጾም ያስፈልጋቸው ነበርና፡፡ በማቴዎስ ወንጌል እንደተጻፈው ጌታችን ጋኔን ያለበትን ልጅ ካዳነው በኋላ ሐዋርያቱ ስለምን እነርሱ ጋኔን ከሰው ማውጣት እንዳልቻሉ በጠየቁት ጊዜ እንዲህ ሲል መልሶላቸዋል፤ ‹‹…ይህ ዓይነቱ ግን ያለጾምና ጸሎት አይወጣም፡፡›› (ማቴ.፲፯፥፳፩)