መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የእግዚአብሔር ሠረገላዎች (መጽሐፈ ስንክሳር)
እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን በዕለተ እሑድ ሲፈጥር በነገድ መቶ በአለቃ ዐሥር አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ከእነዚህ ቅዱሳን መላእክት መካከል ኪሩቤል ይገኙበታል፤ኪሩብ አራት አራት ገጽ ካላቸው ከአራቱ ጸወርተ መንበር አንዱ ሲሆን፣ ፍችው መሸከምን፣ መያዝን ይገልጣል፡፡
በዓለ ደብረ ቁስቋም
በከበረች በኅዳር ስድስት ቀን የምናስበው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ከመድኃኒዓለም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር ከስደት መመለስ እንዲሁም በቁስቋም ተራራ መገኘት ታላቅ በዓል ነው፡፡
‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› (መሓ.፯፥፩)
አሁን ኢትዮጵያውያ ስደተኛ መቀበል አትችልም ስደተኛ ሆናለችና፤ ሱላማጢስ ሆይ አሁን እነዚያ ደጋግ ሰዎች ለእንግዳ ማረፊያ አይሰጡም፤ እነርሱም ማረፊያ መጠለያ አጥተዋልና፤ አሁን የተራበን ለማብላት አቅም የላቸውም፤ እነርሱም ረኃብተኞች ናቸውና፡፡ እናታችን ሆይ ተመለሽ! ሰላማችን ሆይ ነይ! ወደ ዐሥራት ሀገርሽ ተመለሽ! ቃል ኪዳንሽንም አድሽ! የአዲስ ኪዳን ስደተኞች በኩር ሆይ ተመለሽ! መከራችን ያበቃ ዘንድ፣ እንባችን ይታበስ ዘንድ ተመለሽ!
የጸሎት ጊዜያት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው!እንግዲህ ልብ በሉ!በመንፈሳዊውም ሆነ በዘመናዊውም ትምህርት ተምራችሁ ማደግ አለባችሁ፤ባለፈው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ከሆኑት ስለ ጸሎት ጥቂት ብለናችሁ ነበር!ለዛሬ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ስለ ጸሎት ጊዜያት እንማማራለን!
የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ትልልቅ ስጦታዎች መካከል ዋነኛው የንስሓ መንገድ ሲሆን የእግዚአብሔር ቸርነቱ በሰፊው የሚገለጥበት የሕይወት መንገድ ነው። ንስሓ ዘማዊውን ድንግል የምታደርግ ቅድስት መድኃኒት ነች።
ፍቅር ኃያል!
ፍቅር ኃያል ፍቅር ደጉ
ወልድን ሳበው ከጸባኦት ከማዕረጉ
ፍቅር ደጉ ወልድን ሊያነግሥ በመንበሩ
በአንድ ጥለት በየዘርፉ በአንድ ጸና ማኅበሩ
ቃልም ከብሮ የዘውድ አክሊል ተቀዳጅቶ
ከምድር ላይ ከፍ…ከፍ…ከፍ…ብሎ ታይቶ
ተሠየመ በመስቀል ላይ…የነገሥታት ንጉሥ አብርቶ
በዚያች ልዩ ዕለት…ቀን ቡሩክ ቀን ፈራጅ
በዓለ ሢመቱ ሲታወጅ
ኀዘኑም ደስታውም በረከተ
ፍቅር ኃያል ፍቅር ሞተ!
‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› (መሓ.፯፥፩)
ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በፊት የእመቤታችንን የስደቷን ነገር አንሥተን ‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› በሚል ርእስ ከክፍል አንድ እስከ ሦስት አድርሰናችሁ ነበር፡፡ ጥሩ ትምህርት እንዳገኛችሁበት ተስፋ እናደርጋለን፡፡
የዛሬው ትኩረታችን ያን ሁሉ መከራ የተቀበለችበት የስደቷን ምክንያትና ዓላማ መዳሰስ ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
‹‹ምን እናድርግ?›› (ግብ.ሐዋ.፪፥፴፯)
ፀሐይ ብርሃኗን በምትሰጥበት የመዓልት ጉዟችን የጨለማ ጉዞ እስኪመስል በፍርሃት ተሸብበናል፤ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመኖር ተስፋችን፣ እምነትን በወደድነውም ሆነ በፈለግነው ሥፍራ የመግለጽ ነጻነታችን ሲመነምን፣ ነገን በብሩህ ተስፋ የምንመለከትበት የእምነት መነጽራችን በጥርጥር ደመና ሲደበዝዝብን፣ ከአቀበቱ ጀርባ ሜዳ፣ ከጨለማው ማዶ ብርሃን እንዳለን ማስተዋል ተሳነን፡፡
ሥርዓተ ጸሎት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? የአዲሱ ዓመት የትምህርት ዘመን ከተጀመረ ሁለተኛውን ወር እያጋመስን ነው አይደል? ለመሆኑ ከተማርነው ትምህርት ምን ያህል እውቀት አገኘን? ይህን ለራሳችሁ መጠየቅና መበርታት አለባችሁ!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ባለፈው ጊዜ ስለ አጽዋማት መማራችን ይታወሳል! አሁን ደግሞ ስለ ሥርዓተ ጸሎት እንማማራለን፤