መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የአባ ማሩ ተረት /ለሕፃናት/
ግንቦት 7/2004 ዓ.ም.
በልያ አበበ
እንደምን አላችሁ ልጆች! እግዚአብሔር ይመስገን ደኅና ነን እንደምትሉ አልጠራጠርም፡፡ ዛሬ የምነግራችሁ ተረት ስለ አንበሳ፣ ጥንቸልና አሳማ ነው እሺ በጣም ጥሩ ልጆች ተረቱን ልንገራችሁ? ግን እኮ ስለራሴ አላስተዋወኳችሁም፡፡ ስሜ አባ ማሩ ዘነበ ይባላል፡፡ ቁመቴ በጣም አጭር ነው፡፡ ፊቴ ደግሞ ልክ እንደ ብርቱካን ክብ ሆኖ ዓይኖቼ ትናንሽ ናቸው፡፡ ሁል ጊዜ የምለብሰው ነጭ ሱሪና ነጭ ሸሚዝ ነው፡፡ ከእጄ ነጭ ጭራ አይለይም፡፡ ለምን ነጭ ጭራ እንደምይዝ ታውቃላችሁ? በሰፈሬ የሚኖሩ እንደ እናንተ ያሉ ሕፃናት ወደ 12፡00 ሰዓት አካባቢ ፀሐይ ስትገባ ተሰብስበው ይመጡና “አባ ማሩ ዘነበ ተረት ይንገሩን?” እያሉ በዙሪያዬ ስብስብ ይላሉ፡፡ እኔም ልጆችን በጣም ስለምወዳቸው ትንሸን ወንበሬን ይዤ ከቤቴ እወጣና ከግቢያችን ካለው ሰፊ ሜዳ ቁጭ እላለሁ፡፡ ልጆችም በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ እሳት እየሞቅን ተረቱን አጫውታቸዋለሁ ታዲያ ያን ጊዜ ትንኞች በአፌ ውስጥ እንዳይገቡ በነጩ ጭራዬ እከላከላቸዋለሁ፡፡ ስለራሴ ይኸን ያኽል ከነገርኳችሁ ወደ ተረቴ ልመለስ፡፡ ዝግጁ ናችሁ ልጆች? ጎበዞች፡፡
የደጉዋ እናት ልደት/ለሕፃናት/
ግንቦት 3/2004 ዓ.ም.
በኢየሩሳሌም አገር የሚኖሩ ኢያቄምና ሃና የተባሉ በጣም ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ ኢያቄምና ሃና ለእግዚአብሔር የታዘዘ በተቀደሰ ጋብቻ ውስጥ በብዙ ዘመናት አብረው ቢኖሩም በነዚያ ጊዜያት ወስጥ አንድ ልጅ እንኳ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው ይለምኑት ነበር፡፡
የመጻሕትና የድምጽ ወምስል የምረቃ መርሐ ግብር ተካሔደ
ግንቦት 3/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን የልማት ተቋማት አስተዳደር ያሳተማቸውን መጻሕፍትና የድምጽ ወምስል የምረቃ መርሐ ግብር ሚያዚያ 27 ቀን 2004 ዓ.ም. በብሔራዊ ሙዚየም ትልቁ አዳራሽ አስመረቀ፡፡ ከተመረቁት መጻሕፍትና የድምጽ ወምስል ሥራዎች መካከል ዐስሩ የትርጉምና ወጥ መጻሕፍት ሲሆኑ በቪሲዲ እና በሲዲ የተዘጋጁ የአማርኛና የሞሮምኛ ስብከቶች ዘጋቢ ፊልሞች፣ ትርጉም ፊልሞችና መዝሙራት ይገኙበታል፡፡
የጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የአንድነት ኑሮ ማኅበር ሰባኪያነ ወንጌልን አስመረቀ
ግንቦት 3/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የአንድነት ኑሮ ማኅበር በ14ኛው ዙር ለ3 ወራት ያሰለጠናቸውን 47 ሰባኪያነ ወንጌልን ሚያዚያ 21 ቀን 2004 ዓ.ም. አስመረቀ፡፡ በማኅበሩ የተመሠረተው የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የስብከተ ወንጌል
ማሰልጠኛ ተቋም በ12 የትምህርት ዓይነቶች ከጥር 21 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ከ16 ሀገረ ስብከቶች በተለይም ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተውጣጥተው የተመረጡና እያንዳንዳቸው ከሁለት እስከ ሦስት ቋንቋ መናገር የሚችሉ ሰባኪያነ ወንጌልን ቡራዩ አካባቢ በሚገኘው በተቋሙ ግቢ ውስጥ በደመቀ መንፈሳዊ መርሐ ግብር አስመርቋል፡፡ ከተመራቂ ደቀ መዛሙርት መካከል መነኮሳት፣ ካህናት፣ መሪጌቶች፣ ዲያቆናትና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት ያካተተ ሲሆን ‹‹ለቤተ ክርስቲያናችን እጣን፣ ጧፍና ንዋያተ ቅድሳት ብቻ ሳይሆን ሰውም እንስጥ›› የሚል መመሪያ ይዞ በመነሣት በተለይም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የመምህራን እጥረት ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አቶ ማናዬ አባተ የማኅበሩ መንፈሳዊ አገልግሎት መምሪያ ሓላፊ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡
የእግር ጉዞው መርሐ ግብር ተራዘመ
ግንቦት 3/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመት ምስረታን ምክንት በማድረግ ለሚያዚያ 27 ቀን 2004 ዓ.ም ተዘጋጅቶ የነበረው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ወደ ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. ተራዘመ፡፡ የመርሐ ግበሩ አስተባባሪ ሰብሳቢ ዲ/ን ዋሲሁን በላይ ቀኑ የተቀየረበትን ምክንያት እንደገለጹት የእግር ጉዞው በታቀደለት ጊዜ ለማካሔድ ከፍተኛ ጥረቶች መደረጋቸውን፤ በርካታ ቲኬቶችና ካናቴራዎችን ማሰራጨታቸውን፤ ነገር ግን ከምእመናን በተደጋጋሚ በቀረቡ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች አንደኛ ከሰሙነ ሕማማት ጀምሮ በትንሳኤ በአል ምክንያት ምእመናን የተለያዩ ወጪዎችን ማውጣታቸውንና በጉዞው ላይ ለመሳተፍ ትኬቱን መግዛት ያለመቻላቸው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከትንሳኤ በአል በኋላ የቀኑ ማጠር፤ እንዲሁም በበአለ ሃምሳ ምክንያት የተለያ የማኅበራዊ ሕይወት ተሳትፎ ጎልቶ የሚታበት ወቅት በመሆኑ ቀኑ እንዲቀየርላቸው ከፍተኛ ግፊት በማድረጋቸው ጥያቄያቸውን ተቀብለን የእግር ጉዞው መርሐ ግብር ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. እንዲሆን ተወስኗል ብለዋል፡፡ ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም የተመረጠበትን ምክንያት ሲያብራሩ፤ ምእመናን ከትንሣኤ በአል ጋር ተያይዞ ከማኅበራዊ ሕይወት ፋታ ያገኙበታል ተብሎ መታሰቡና ቅድስት ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው በዓላት አንዱ የጰራቅሊጦስ ዕለት በመሆኑ ቀኑን በአንድነት ሆነን እግዚአብሔርን እያመሰገንን እንድንውል በማሰብ ነው ብለዋል፡፡
የሩስያው ፕሬዝዳንት ለሀገራቸው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምስጋና አቀረቡ
ግንቦት 3/2004 ዓ.ም.
በስንሻው ወንድሙ
የሩስያ ፕሬዝዳንት ዴሚትሪ ሜድቬዴቭ የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ዜጎች ዘንድ መንፈሳዊ ሥርዐት እንዲጐለብት ለምታደርገው እንቅስቃሴ ከሁለት ሳምንት በፊት ምስጋና ማቅረባቸውን ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ለሩስያና ቡልጋርያ ግንኙነት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የበኩሏን እንድትወጣ ተጠየቀ፡፡
ግንቦት 3/2004 ዓ.ም.
በስንሻው ወንድሙ
ሩስያ ከቡልጋርያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች በኦርቶዶክስ እምነት አባቶች በኩል ለማጠንከር የሀገሪቱ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በቡልጋርያ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡
እንደ ዘጋርድያን ጋዜጣ ዘገባ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ክሪል ከቡልጋርያው አቻቸው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማክሲም ጋር ተገናኘተው ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ያላቸውን መልካም ግንኙነት በማጠንከር በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በድልድይነት በሚያገለግሉበት ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመት ምሥረታ በመከበር ላይ ነው
ግንቦት 2/2004 ዓ.ም.
በ እንዳለ ደምስስ
የእመቤታችን በዓለ ልደት ተከበረ፡፡
ግንቦት 2/2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኩኖአምላክ
በየዓመቱ ግንቦት አንድ ቀን በልዩ መንፈሳዊ ድምቀት የሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል ትናንት በመላው ዓለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ተከብሮ ዋለ፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማዕከል አስተባባሪነት በማኅበሩ ሕንፃ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አዳራሽ በተከናወነው የእመቤታችን የልደት በዓል መርሐ ግብር ከስድስት መቶ በላይ የሚሆኑ የማኅበሩ አባላትና ሌሎች ተጋባዥ ምእመናንም ተገኝተዋል፡፡ የእመቤታችንን በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን መልእክት የአዲስ አበባ ማዕከል ሰብሳቢ ዲ/ን አንዱ ዓለም ኀይሉ አቅርበዋል፡፡
የደቡብ ክፍለ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ተካሄደ
ግንቦት 2/2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኩኖአምላክ