መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
በመንበረ ፓትርያርክ አካባቢ ራሳቸውን “ጉባኤ አርድዕት” ብለው የሰየሙ ቡድኖች እየተፈጠሩ መሆናቸው ተገለፀ፡፡
ሰኔ 09 ቀን 2004 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባለፉት ረጅም ዓመታት በርካታ ፈተናዎችን አልፋ የተጓዘች መሆኗ ይታወቃል፡፡ በተለይም ራሳቸውን ተሐድሶ ብለው የሰየሙ ቡድኖች ተመሳስለው ውስጧ በመግባት ውስጥ ለውስጥ ሲያደሟት ቆይተዋል፡፡ የእነዚህ ድብቅ ቡድኖች አካሄድ ለብዙ ጠንካራ ኦርቶዶክሳውያን ግልፅ የነበረ በመሆኑ ላለፉት ተከታታይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያት ማንነታቸው ተገልጾ ውግዘት የተላለፈባቸውና በሕግ የሚጠየቁትም በሕግ እንዲጠየቁ መወሰኑ […]
ዝክረ አቡነ ጎርጎርዮስ ሊካሄድ ነው
ሰኔ 09 ቀን 2004 ዓ.ም
በእንዳለ ደምስስ
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል የማኅበሩን 20ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ “ዝክረ አቡነ ጎርጎርዮስ” በሚል ርእስ
የጥናትና የውይይት መድረክ ሰኔ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም አዲሱ አዳራሽ አዘጋጅቷል፡፡
የጥናትና ምርምር ማእከሉ ም/ዳይሬክተር አቶ ሰይፉ አበበ መርሐ ግብሩን አስመልክቶ እንደገለጹት “የጥናት መድረኩ ዋና ዓላማ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሕይወት ዘመናቸው ለቤተ ክርስቲያን ያበረከቱትን አገልግሎት፣ የሕይወት ልምዳቸውን፣ ወጣቱን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በአንድ ዓላማ ለማሰለፍ ያደረጉትን ተጋድሎ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት የነበራቸውን ርዕይ የሚዘክር ይሆናል” ብለዋል፡፡
ቤተ መጻሕፍቱ የመጻሕፍትና ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጀ፡፡
ሰኔ 04 ቀን 2004 ዓ.ም
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖአምላክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን ቤተ መጻሕፍት እየሰጠ ያለውን አገልግሎት አጠናክሮ ለመቀጠል ይረዳው ዘንድ የመጻሐፍትና ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጀ፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማዕከል ሥር የሚገኘው ቤተመጻሕፍት ፡-“ስትመጣ …በርኖሱንና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ” (2ኛ ጢሞ.4÷13) በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው በዚሁ የመጻሐፍትና ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር፡-
• ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ፣ ምክርና ትምህርት የሚሰጡ መጻሕፍት፣ መዛግብት፣ መጽሔቶችና ጋዜጦችን፣ የአስኳላ (አካዳሚካል) መጻሕፍት፣
• ጥናታዊ ጹሑፎችን እንዲሁም
• ቤተመጻሕፍቱን ለማደራጀት የሚያግዙ ቁሳቁሶችን በመስጠት ምእመናን የበኩላቸውን እገዛ እንዲያበረክቱ ጠይቋል፡፡
ኢንኅድግ ማኅበረነ
የማኅበሩ 20ኛ አመት ምሥረታ ተከበረ
ግንቦት 28 ቀን 2004 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ የማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ አመት የምሥረታ በኣል በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. ተከበረ፡፡ ከረፋዱ 4፡ 00 ስኣት ጀምሮ የተካሔደው መርሐ ግብር በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ፤ የኢሉባቦርና ጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ መሪነት ጸሎተ ወንጌል በማድረስ ተከፍቷል፡፡ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የምዕራብ ሐረርጌ […]
አገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ እየተካሔደ ነው፡፡
ግንቦት 25 ቀን 2004 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አስተባባሪነት አገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መሥራች ጉባኤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ እየተካሔደ ነው፡፡
በዓሉን ለማክበር ርብርቡ ቀጥሏል
ግንቦት 25 ቀን 2004 ዓ.ም የማኅበሩ 20ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል የእግር ጉዞ በማዘጋጀት አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው በመንበረ ክቡር ቅዱስ ሚካኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ለማክበር ቀደም ብሎ የታቀደ ቢሆንም መርሐ ግብሩ እሑድ ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ለማክበር ተወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት መርሐ ግብሩን የተሳካ ለማድረግ የተግባር ቤት (ምግብ ዝግጅት) […]
ሰበር ዜና፡ የእግር ጉዞው መርሐ ግብር ተቀየረ፡፡
ግንቦት 24 ቀን 2004 ዓ.ም. እንዳለ ደምስስ መርሐ ግብሩ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ይካሔዳል፡፡ ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ ሊካሔድ የነበረው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ጠቅላይ ቤተ ክህነት መጻፍ ያለበትን ደብደቤ ባለመጻፉ በታቀደለት መሠረት ሊከናወን አልቻለም፡፡ መርሐ ግብሩ እሑድ ጠዋት ከ 3፡00 ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ […]
ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም ዮሐ.14፥18
ግንቦት 24/2004 ዓ.ም.
ይህንን የተስፋ ቃል ለቅዱሳን ሐዋርያት የተናገረው ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት ደቀ መዝሙርነት የተጠሩት በልዩ ልዩ ሙያ ተሰማርተው ሳለ ነው፡፡ በየሙያቸው ሥራ እየሠሩ ከሚተዳደሩበት ሥፍራ ሁሉ ደርሶ ፈጣሪያችን በቸርነቱ ለከበረው የወንጌል አገልግሎት ጠራቸው፡፡ “ወእንዘ ያንሶሱ መንገለ ባሕረ ገሊላ፤ ርእየ ክልኤተ አኅወ፥ ስምዖንሃ ዘተሰመየ ጴጥሮስ ወእንድርያስሃ አኅዋሁ እንዘ ይወድዩ መርበብቶሙ ውስተ ባሕረ፤ እስመ መሠግራነ እሙንቱ፡፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ንዑ ትልዉኒ፤ ወእሬስየክሙ ትኩኑ መሠግራነ ሰብእ፡፡…. በገሊላ ባሕር ዳር ማዶ ሲመላለስ ሁለት ወንድማሞችን አገኘ፡፡ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንና ወንድሙን እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፣ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና፡፡ ጌታችንም “ለጊዜው በእግር ተከተሉኝ ፍጻሜው በግብር ምሰሉኝ፡፡ እኔም ሰውን እንደ ዓሣ ወንጌልን እንደ መረብ፣ ይህን ዓለም እንደ ባሕር አድርጋችሁ እንድታስተምሩ አደርጋችኋለሁ” አላቸው፡፡ ያን ጊዜ መርከባቸውንና መረባቸውን ትተው ተከተሉት” የተቀሩትም ሁሉ እንዲህ ባለ ጥሪ ጠራቸው /ማቴ.4፥18-22፣9፣ ዮሐ.1፥46፤ 44፥51/
ቅዱሳን ሐዋርያትም ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ጌታችን በዋለበት ውለው ባደረበት እያደሩ የቃሉን ትምህርት ሰምተው የእጁን ተአምራት አይተው ከእርሱ ጋር ሆኑ፡፡ በኋላም የተጠሩለትን አገልግሎት በመፈጸም ክብርን አግኝተውበታል /ማቴ.13፥42፣ ሕዝ.47፥10/፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን ሁሉ ትተው ጥለው የተከተሉትን ሐዋርያትን “ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም” አላቸው፡፡ አጽናኝ ጰራቅሊጦስ ይሰጣችኋል፡፡
በጎ አድራጊ ምእመናን ለማኅበሩ ሕንፃ ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አደረጉ፡፡
ግንቦት 22/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
• የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በዮድ አቢሲንያ ተካሄዷል፡፡
• “ቅዱስ ሲኖዶስ ከእናንተ ጋር ነው፡፡”ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ
• “ይህን ቤት ለመሥራት የነበረው ውጣ ውረድ፣ የደረሰባቸሁ መከራ ብዙ ነው፡፡ ብዙውን ፈተና አልፋችሁታል፡፡” ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፡፡
በግንባታ ላይ የሚገኘውን የማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት ሕንፃ ማስፈጸሚያ የሚውል በበጎ አድራጊ ምእመናን አነሣሽነትና አስተባባሪነት ሰኞ ግንቦት 20 ቀን 2004 ዓ.ም. ቦሌ በሚገኘው ዮድ አቢሲንያ የባሕል ምግብ ቤት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡መርሐ ግብሩ በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡብ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳትና የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የኢሉባቦርና የጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡