መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ /ማቴ. 5፥24/
ታኅሣሥ 10 ቀን 2005 ዓ.ም.
ለቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ስኬት የአባቶቻችን ስምምነት ወሳኝ ነው
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሥጋ ሕይወት በነበሩበት ባለፉት ዓመታት “ስደተኛ ሲኖዶስ” ተብሎ ከተጠራው በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ አባቶች ጋር ዕርቅ ለመፈጸም ጥረት ይደረግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገብ ሳይችል በእንጥልጥል እንዳለ ቅዱስነታቸው ዐረፉ፡፡
የእርሳቸው ዕረፍት ቀጣዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ከመመረጣቸው በፊት በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ተለይተው ከሚኖሩ አባቶች ጋር ውይይት ለመጀመር አስገዳጅ ሁኔታ አምጥቷል፡፡ ይህ እንዲታሰብ ግድ የሚያደርገውም ቀጣዩ ፓትርያርክ የሚሰየሙበት መንገድ ሁሉን የማያስማማ ከሆነ የነበረውን ልዩነት የሚያሰፋ ውዝግብ በዚህች ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊያስከትል እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ስለሚቻል ነው፡፡ ይህንን ከግምት አስገብቶ የወቅቱን አንገብጋቢነት ተረድቶ ወደ ዕርቅ የሚያደርስ ውይይት ማድረግ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን ወሳኝ አገልግሎቶች በብቃትና በስፋት ለመስጠት፣ ጠንካራ መሠረትም ለመገንባት ስለሚያስችል ነው፡፡
“ወበ እንተዝ ኢየኃፍር እግዚአብሔር ከመ ይትበሃል አምላኮሙ” (ክፍል 2)
ታኅሣሥ 10 ቀን 2005 ዓ.ም.
በቀሲስ ይግዛው መኰንን
4. ሰማያዊውን ሕይወት ናፋቂዎች ስለሆኑ
ክቡር ዳዊት “በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፤ ለዓለምና ለዘለዓለምም ያመሰግኑሃል፡፡ አቤቱ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው፡፡” በማለት ሰማያዊውን መናፈቅ እንደሚያስመሰግን በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ተናገረ፡፡ መዝ. 83፥4 ቅዱስ ጳውሎስም የሚጠበቅበትን አገልግሎት ካከናወነ በኋላ “ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፤ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤” በማለት ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ሕይወት ምን ያህል እንደሚናፈቅ ገልጿል፡፡ ፊል.1፥23 ለዚህ ነው ቅዱሳን በሥጋ የምኞት ፈረስ እንዲጋልቡ፥ በኀጢአት ባሕር እንዲዋኙ፥ በክፉ አሳብ ጀልባ እንዲቀዝፉ የሚፈታተናቸውን ርኩስ መንፈስ በመልካም ሥራቸው በመቃወም ድል የሚያደርጉት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ፡፡” በማለት የአሁኑን ችግርና ፈተና ከሚመጣው ጋር በማመዛዘን የተናገረው፡፡ ሮሜ.8፥18
ለሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን እድገት የገዳማት ድርሻለሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን እድገት የገዳማት ድርሻ
ታኅሣሥ 8 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ሪፓርታዥ
ከስዓት በኋላ በዐውደ ጥናቱ ላይ ለመገኘት በተዘጋጀላቸው መኪና ከማኅበሩ ዋና ጽሕፈት ቤት ወደ ኢትዮጵያ ስብሰባ ማእከል አዳራሽ ያመሩ ሲሆን ኢትዮጵያ ስብሰባ ማእከል እንደደረሱ በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን በዝማሬ በመታጀብ ወደ አዳራሹ ገብተዋል፡፡ በአዳራሹ ውስጥ የተገኙ ምእመናን በእልልታና ዝማሬ አቀባበል በማድረግ ገዳማውያን አባቶችም እጅ እየነሱና ምእመናን እየባረኩ ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ በማምራት ቦታቸውን ያዙ፡፡
አባቶቻችንን አንተው
ከታላላቅ ገዳማት ለመጡ አባቶች አቀባበል ተደረገ
ታኅሣሥ 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን ታላላቅ ገዳማት ለመጡ አበምኔቶችና እመምኔቶች አቀባበል ተደረገ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ለማሳካት የገዳማት ድርሻ በሚል በተዘጋጀው ዐውደ ጥናትና ለአምስት ቀናት በሚቆየው ሥልጠና፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ አሻራቸውን ትተው ያለፉትን የታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የገድል መጽሐፍ ምረቃ ላይ ለመገኘት ከሃምሳ በላይ ለሚደርሱ ገዳማት አበምኔቶችና እመምኔቶች በተደረገው ጥሪ መሠረት ከማክሰኞ ጀምሮ ርቀቱ ሳይገድባቸው አዲስ አበባ በመግባት ላይ ሰንብተዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም ዝግጅቱን አጠናቆ በጉጉት ከመጠባበቅ አልፎ በአክብሮት እየተቀበላቸው ይገኛል፡፡
ገዳሞቻችንን ለሁሉ ዓቀፍ ልማት አናዘጋጃቸው፡፡
ታኅሣሥ 5 ቀን 2005 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ገዳማት ባለቤት ነች፡፡ በፈቃደ እግዚአብሔር ከ5ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ እየተስፋፉና እያደጉ የመጡት እነዚሁ ገዳማት የምናኔና የጸሎት እንዲሁም ድኀነተ ሥጋ ወነፍስ የሚገኝባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ለቤተ ክርስቲያናችን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን የሊቃውንት መፍለቂያና የበርካታ ቅዱሳን ምንጭ በመሆንም ሲያገለግሉ እንደኖሩ ይታወቃል፡፡ በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አዎንታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠራቸውም በላይ የሀገሪቱ የትምህርትና የሥልጣኔ ማእከላት በመሆን አገልግለዋል፡፡
“ለቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት የገዳማት ድርሻ” በሚል ዐውደ ጥናት ይካሄዳል
ታኅሣሥ 4 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ምን ይላሉ?
ታኅሣሥ 4 ቀን 2005 ዓ.ም.
ፕሮፌሰር ባዬ ይማም
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በሞት ሲለዩ ማን ይተካቸዋል? የሚተኩት አባት እንዴት ይመረጣሉ
? የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም፡፡ ከተነሣ ደግሞ የምርጫ መስፈርት ይኖራል ብዬ አስባለሁ፡፡ ከአሁን በፊት ቤተ ክርስቲያኗ ፓትርያርክ መርጣ የምትሾምበት ሥርዐት ካላት፤ ያ ሥርዐት አሁንም በተግባር መዋል አለበት፡፡ ምናልባት አዲስ የመምረጫ መስፈርት ማውጣት የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ሲኖዶሱ ተጨማሪ መስፈርት ሊያወጣ፣ ያሉትን መስፈርቶች ሊያሻሽል የሚችልበት ሥልጣን አለው፡፡ በዚህም መሠረት ምርጫው ይከናወናል፡፡
ዕጣ በቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሥርዓት
ታኅሣሥ 1 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ምትኩ አበራ
ዕጣ /እጻ/ የሚለው ቃል ዐፀወ ዕጣ ተጣጣለ /አወጣ/ ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በግእዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው “አጭርና ቀጭን እንጨት፤ ከመካከለኛ ጣት የሚበልጥ፤” ብለው ይፈቱታል፡፡ ዕጣ እድል ድርሻም ሊባል ይችላል፡፡ የዕጣ አሠራር ከክርስቶስ ልደት በፊት ከኦሪቱ ጊዜ ጀምሮ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ በጥንት ጊዜ ሰዎች ዕጣን በእንጨት፣ ጽሑፍ ባለበት ድንጋይ /ጠጠር/ ይጥሉ ነበር፡፡
የዕጣ ሥርዓትን ለሰዎች ያስተዋወቀው ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ “እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፡- ለእነዚህ በየስማቸው ቁጥር ምድሪቱ ርስት ሆና ትከፈላለች… ለሁሉ እንደቁጥራቸው መጠን ርስታቸው ይሰጣቸዋል፡፡ ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፈላለች፤ በብዙዎችና በጥቂቶች መካከል ርስታቸው በዕጣ ትከፈላለች”፡፡ /ዘኁ.26፥52-56/ ይህንን ትእዛዝ እግዚአብሔር ሲያስተላልፍ ሥርዐተ ዕጣውን የሚመሩትንም ጭምር “….ርስት ትሆናችሁ ዘንድ በዕጣ የምትደርሳችሁን ምድር…. የሚከፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፡፡” በማለት አሳውቋቸዋል፡፡ /ዘኁ.30፥2-16/ በዚህ ዐቢይ ትእዛዝ መሠረት ተሿሚዎቹ በተፈጥሮ ወጣ ገባ፣ ጭንጫና ለም ወዘተ… የሆነችውን ምድር ከሐሜት በጸዳና ከአድልኦ በራቀ መለኮታዊ ሥርዓት ርስቱን አከፋፍለዋል፡፡
በደቡብ ኦሞ ከሰባት መቶ በላይ ሰዎች ተጠመቁ
ታኅሣሥ 1 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ