መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት ቤተ ክርስቲያኒቱ በአንገብጋቢነት የምትሻውን ወቅታዊ ጥያቄ የሚመልስ አሳብ የያዘ ነው
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
ከአራት ዓመት በፊት 2001 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ተሻለ የአገልግሎት ደረጃ ለማድረስ በመከረበት ጉባኤው ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሉባትን ለአገልግሎቱ እንቅፋት የሆኑ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን ለማስወገድ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች፣ የተያዙ አቋሞች ነበሩ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በጊዜው በቤተ ክርስቲያኒቱ “የአስተዳደር ችግሮች፣ የሙስናና የቤተሰብ አስተዳደር” በቤተ ክርስቲያኒቱ የአገልግሎት መስመሮች ውስጥ ሁሉ መንሰራፋቱን አምኖ ያንን ለማጥራት፣ ዘመኑን የዋጀ በተጠና ዕቅድና አፈጻጸም የሚከናወን፣ ሓላፊነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው፡፡
በባሕረ ጥበባት /Encyclopedia of EOTC/ ዝግጅት ዙሪያ የምክክር ጉባኤ ተካሔደ
ግንቦት 30 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል አስተባባሪነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የባሕረ ጥበባት /Encyclopedia of EOTC/ ዝግጅት ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር ጉባኤ ተካሔደ፡፡
ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ አስር ሰዓት ጀምሮ በሰሜን ሆቴል በተካሔደው የምክክር ጉባኤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት /Encyclopedia of EOTC/ ማዘጋጀት
ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያትን አስመልክቶ በማኅበሩ ሰብሳቢ በቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ ተገልጿል፡፡ በንግግራቸውም በተለያዩ ጊዜያት የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክና ቅርሶች አጥኚዎች፤ ጎብኚዎችና ምእመናን መረጃዎችን ማእከላዊና ሕጋዊ ከሆነ ቦታ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን አውስተው አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው፤ ሊቃውንቱ የሚያውቁት የቤተ ክርስቲያንን ማንንት የሚገልጽ መረጃ ማዘጋጀት፤ በተለያዩ ጊዜያት በዘርፉ የተሞከረው እውቀት በአንድ ላይ በማሰባሰብ የታሪክ ቅሰጣ ለማስቀረትና ለመከላከል እንዲቻል ይህንን ባሕረ ጥበባት ማዘጋጀት እንዳስፈለገ አብራርተዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ
ግንቦት 30 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 2005 ዓ.ም. ድረስ ሲካሔድ የሰነበተው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያኗ አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ውሳኔዎች በማሳለፍ ተጠናቀቀ፡፡ በዚህም መሠረት የሚከተሉትን ጠቅለል ያሉ ውሣኔዎች ተላልፈዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚታዩ ብልሹ የአስተዳደርና የአሰራር ችግሮችን ማሻሻል፤ ጥራት የጎደለው የፋይናንስ አያያዝን መዋጋት፤ ሙስናንና ለብክነት የተጋለጡ አሰራሮችን ለመቅረፍ እንዲቻል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ ምሁራንና ምእመናን የሚገኙበት ዓብይ ኮሚቴ ማዋቀሩን ይፋ ማድረግ፡፡ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአንድ ሀገረ ስብከት፤ በአንድ የቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ የተደረገ ሲሆን ፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ምርጫም ተከናውኗል፡፡ ከሀገር ውጪ ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር የተጀመረው የሰላም ውይይት ጥረት እንደሚቀጥልም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ዝርዝር መግለጫውን ከዚህ በታች እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
የጀበራ ማርያም ገዳምን እንደገና ለማቋቋም ጥረት በመደረግ ላይ ነው
ግንቦት 3ዐ ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በበሰሜን ጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ በጣና ሐይቅ ደሴቶች ውስጥ ከሚገኙት ገዳማት አንዱ የሆነውና ለረጅም ዘመናት ጠፍ ሆኖ፤ ፈርሶ የቆየው የጀበራ ማርያም ገዳምን መልሶ ለማቋቋም ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡
የቅዱስ ሚካኤል ታቦት “ካህኑን” አቃጠለ
ግንቦት 30 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ቴዎድሮስ ኃይሉ
የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ ሳምንት ተዘጋጀ
ግንቦት 23 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ሐመር መጽሔት በግንቦት ወር እትሟ….!
ማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ሥርጭት አገልግሎቱን በይፋ መጀመሩን አበሰረ
ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲየን ማኀበረ ቅዱሳን ላለፉት ሃያ ዓመታት በመንፈሳዊ መገናኛ ብዙኃን ሲሰጥ የቆየውን አገልግሎት በማስፋት የቴሌቪዥን ሥርጭት በኦፊሴል መጀመሩን ለምእመናን የሚያበስርበት ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ስብሰባ ማእከል እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡
የቅዱስ ያሬድ 1500ኛ ዓመት መታሰቢያ በድምቀት ተከበረ
ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ከየአድባራቱና ገዳማት የመጡ ታላላቅ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምእመናን የተገኙ ሲሆን የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የቅዱስ ያሬድ ሥራዎችን በዩኔስኮ ማስመዝገብ እንደሚገባ ተገለጸ
የቅዱስ ያሬድ 1500ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓልን አስመልክቶ ማኀበረ ቅዱሳን በግዮን ሆቴል ባዘጋጀውና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት አውደ ጥናት ላይ የቅዱስ ያሬድ ሕይወትና ሥራዎቹ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት /UNESCO/ ለማስመዝገብ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ፡፡
ቅዳሜ ግንቦት 10 ሙሉ ቀን በተደረገው በዚህ ዐውደ ጥናት ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡባዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ከየአድባባራቱና ገዳማት ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቃለምዕዳን ዐውደ ጥናቱ ተከፍቷል፡፡
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በሠጡት ቃለ ምዕዳን ማኅበሩ የቅዱስ ያሬድን 1500ኛ መታሰቢያ በዓልን ማዘጋጀት በመቻሉ አመስግነው በአሁኑ ወቅት በቅዱስ ያሬድ የዜማ ትምህርት ከፍተኛ እውቀት ያላቸው አባቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ መምጣቱንና በሀገረ ስብከታቸው ከሚገኙ 1000 ገዳማትና አድባራት ውስጥ በጣም ጥቂት የድጓ መምህራን ብቻ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ይህም አሳሳቢነቱን ከፍ ስለሚያደርገው ከፍተኛ ጥረት መደረግ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡