መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ወሰአረ መርገመ በዲበ ዕፀ መስቀል
መስከረም 16 ቀን 2006 ዓ.ም.
በመ/ር ምስጢረ ሥላሴ ማናየ
በቅ
ድሚያ ከዘመን ወደ ዘመን ያሸጋገረን ለብርሃነ መስቀሉ ያደረሰን በሀብቱ የሳበን በረድኤቱም ያቀረበን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡
ከላይ በርዕሱ ያነሣነው ኃይለ ቃል ቅዱስ አትናቴዎስ የመስቀሉን ነገር በተናገረበት ድርሳኑ የተናገረው ነው፡፡ አስተሀፈረ ኃጢአተ በዲበ ምድር ወሰአረ መርገመ በዲበ ዕፀ መስቀል ወአብጠለ ሞተ በውስተ ሲዖል ወነሰተ ሙስና እምውስተ መቃብር”
“በምድር ላይ ኃጢአትን አሳፈረ መርገምን በመስቀል ላይ ሻረ ሞተ ነፍስን በሲዖል አጠፋ ፈርሶ በስብሶ መቅረትን በመቃብር አፈራረሰ” በማለት ጌታችን ለሰው ልጆች ነጻነት እና ድኅነት የከፈለውን የቤዛነት ሥራ በተናገረበት ክፍል የተናገረው ነው የሰው ልጆች ነጻነታቸው የተዋጀው በመስቀል ተሰቅሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በሥልጣኑ ለይቶ ዲያብሎስን በመስቀሉ ገሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ ነፍሳትን ከዲያብሎስ ባርነት ከአጋንንት ቁራኝነት ከሲዖል ግዛት ነጻ አውጥቷቸዋልና፡፡
አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
መስከረም 13 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
ለአቡነ አኖሬዎስ ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም ናርዶስ ሲሆን በሕፃንነታቸው የዳዊትን ንባብና የመጻሕፍትን ትርጓሜ ከተማሩ በኋላ በወቅቱ ከነበሩበት ግብፃዊ ጳጳስ ዲቁና ተቀበሉ፡፡ በወቅቱ ሐራንኪስ የተባለ የትርጓሜ መጻሕፍትና የዜማ ዐዋቂ በቤታቸው በእንግድነት ለብዙ ጊዜ በቆየበት ወቅት ለአቡነ አኖሬዎስ ዜማና ትርጓሜ መጻሕፍት በሚገባ አስተምሯቸዋል፡፡ በዚህም ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ ዜማና ትርጓሜ መጻሕፍት የበለጠ ለመረዳት ከነበራቸው ፍላጎት አንጻር ወደ ደብረ አስቦ (ደብረሊባኖስ) በመሔድ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር ተገናኙ፡፡ በደብረ አስቦ (ደብረሊባኖስ) በገዳም ለረዥም ዓመታት ካገለገሉና ከተማሩ በኋላ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ መንኩሰው አባ አኖሬዎስ ተባሉ፡፡
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርና አጠቃቀሙ ክፍል 2
መስከረም 22 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዲ/ን ኃ/ኢየሱስ ቢያ
መጥቅዕ እና አበቅቴ ከየት መጣ ቢሉ
የፀሐይና የጨረቃ ቀን አቆጣጠር ልዩነት ነው፡፡ አንድ ዓመት በፀሐይ 365 ቀን ከ15 ኬክሮስ ሲሆን በጨረቃ 354 ቀን ከ22 ኬክሮስ ነው፡፡ ስለዚህ የሁለቱ ልዩነት 365 – 354 = ይህ ልዩነት አበቅጽ ተባለ፡፡
ሁለተኛው የቅዱስ ዲሜጥሮስ ሱባኤ ውጤት ነው፡፡ በዓላትና አጽዋማት የሚውሉበት ቀን በጥንተ ዕለቱ እንዲውል ለማድረግ ይመኝ ነበርና ከሌሊቱ 23 ሱባኤ ከቀኑ 7 ሱባኤ ገብቷል፡፡ ይህንን 23×7=161 ይሆናል፡፡ 161 ሲካፈል ለ30= 5 ይደርስና 11 ይተርፋል ይህን ቀሪ አበቅቴ አለው፡፡ 7 x7 = 49 ይሆናል፡፡ 49 ለ 30 ሲካፈል 1 ጊዜ ደርሶ 19 ይቀራል ይህን ቀሪ መጥቅህ አለው፡፡
– ዓመተ ዓለሙን
– ወንጌላዊውን
– ዕለቱን
– ወንበሩን
– አበቅቴውን
– መጥቁን
– መባጃ ሐመሩን
– አጽዋማትን
በዓላትን ለይቶ ለማወቅ ሒሳባዊ ሰሌቱ እንዲሚከተለው ነው፡፡
በሶዲቾ ዋሻ የእመቤታችን ጽላት በአገር ሽማግሌዎች እየተጠበቀ ነው
መስከረም 9ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በከምባታ ጠምባሮ ዞን ልዩ ስሙ ሶዲቾ ዋሻ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ በ984 ዓ.ም. የነበረ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጽላት በአገር ሽማግሌዎች እየተጠበቀ ነው፡፡
በግንቦት ወር ላይ ቆሞስ አባ ኤልያስ የተባሉ አባት ወደ ሶዲቾ ዋሻ በመምጣት ከሚመለከታቸው የቤተክርስቲያንና የዞኑ የመንግስት አካላት ፈቃድ በማግኘት ከዋሻው ውስጥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግልማርያም ጽላት፤ የአንድ አባት አጽምና የእጅ መስቀል በቁፋሮ ማውጣታቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በሥፍራው በሚከናውነው የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ብዙዎች በጸበል እየተፈወሱ ሲሆን ኢ- አማንያንም ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡ ይህ ያሳሰባቸው አንዳንድ ግለሰቦች በቡድን በመደራጀት በቦታው ላይ የሚገኙትን አባት ቆሞስ አባ ኤልያስን ከአካባቢው እንዲለቁ በማስገደድ፤ በማስፈራራትና ድንጋይ በመወርወር ደብድበው ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው የሚታወስ ነው፡፡ በርካታ ጸበል ሊጠመቁ የመጡ ምእመናንም በድንጋይ ድብደባ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
5ኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ ዐውደ ጥናት ተካሔደ
መስከረም 3 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በመክፈቻ መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት መልእክት “እግዚአብሔር ሲፈቅድ ልጆቹን ለመልካም ነገር ያውላቸዋል፡፡ የዚህ ጉባኤ ዓላማም ለመልካም ሥራ ነው፡፡ መልካም ሰዎች ለመልካም ነገር ይውላሉና፡፡ ሰው ሰውን አፍቃሪ፤ ረጂ፤ ለሀገሩም ለእግዚአብሔር የተመቸ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ የዘመኑ የፈጠራ ትምህርት ከመንፈሳዊ ትምህርት ጋር በተያያዘ መመራመርን ይጠይቃል፡፡ ሰው ካወቀ ለሌላው ያሳውቃል፤ ለሌላው ያስረዳል፤ መልካም መሳሪያም ይሆናል፡፡ ይህ የተጀመረው ምርምርና ጥናት እኛንም የበለጠ ያፋቅረናል፤ በሃይማኖት እንድንቆም፤ የበለጠም እንድንሠራ ያደርገናል፡፡ የተሸሸገውን ታሪካችንን፤ያሳውቀናል፤ ልጆቻችንንም ተረካቢ ያደርጋቸዋል፡፡ ጥሩ ጅምር በመሆኑ በዚሁ እንድንቀጥል ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርና አጠቃቀሙ
ዲ/ን ኃ/ኢየሱስ ቢያ የዘመን አቆጣጠር ማለት፡- ዓመታትን፤ ወራትን፣ ሳምንታትን፣ ዕለታትን፤ ደቂቃንና ድቁቅ ሰዓታትን በየሥፍራቸው የሚገልጽ፤ የሚተነትን፤ የሚለካ የቤተ ክርስቲያን የቁጥር ትምህርት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ተመርምረው ተመዝነው ተቆጥረው ሲያበቁ ምድብና ቀመር ተሰጥቶአቸው የሚገኙበትን ውሳኔና ድንጋጌ የሚያሰማ የዘመን አቆጣጠር ሐሳበ ዘመን ይባላል፡፡ ዓመታታ፣ ወራት፣ ሳምንታት፣ ዕለታትና ሰዓታት የሚለኩት /የሚቆጠሩት በሰባቱ መሰፈሪያና በሰባቱ አዕዋዳት ነው፤ እነሱም፡- 1. ሰባቱ […]
ከሶዲቾ ዋሻ ጽላት ያገኙት አባት ከፍተኛ ድብደባ ደረሰባቸው
በከምባታ ጠምባሮ ዞን በሶዲቾ ዋሻ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጽላትና ንዋያተ ቅድሳት በቁፋሮ እንዲወጣ ያደረጉት አባት ቆሞስ አባ ኤልያስ ጳጉሜ 4 ቀን 2005 ዓ.ም. ከፍተኛ ድብደባ ደረሰባቸው፡፡ ዋሻው በ1998 ዓ.ም. የተገኘና የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በቅርስነት ከያዛቸው የመስህብ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ በአካባቢው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ቁጥር አነስተኛ ሲሆን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እንደሚበዙ […]
ቅዱስ ፓትርያርኩ የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ
ጳጉሜን 4 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ2006 ዓ.ም. አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤውን አካሔደ
ነሐሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን በየ ስድስት ወሩ አንድ ጊዜ የሚያካሒደውን የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ከነሐሴ 25 እስከ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. አካሔደ፡፡ የስድሰት ወራት የማኅበሩን የሥራ አፈጻጸም በመገምገም አጽድቋል፡፡
ፍኖተ ሐመረ ጽድቅ ዐውደ ርዕይ ተከፈተ
ነሐሴ 24 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ዐውደ ርዕዩ እሰከ ከነሐሴ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ይቆያል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን ኅትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ዋና ክፍልን የሃያ ዓመታት የአገልግሎት ጉዞ የሚያሳይ ፍኖተ ሐመረ ጽድቅ ዐውደ ርዕይ በማኅበሩ ሕንፃ ላይ ተከፈተ፡፡
ፍኖጸተ ሐመረ ጽድቅ ዐውደ ርዕይ ነሐሴ 23 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የቦረና፤ አማሮና ቡርጂ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት ባዕታ ለማርያም ገዳምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና አገልጋዮች በተገኙበት መርቀው ከፍተዋል፡፡