google play news 4

«ተዋሕዶ ለአንድሮይድ» የተሰኘ የስልክ ላይ አገልግሎት ተጀመረ

 የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም.

በዝግጅት ክፍሉ ሪፖርተር

 google play news 4

google play news 2በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሚድያና ቴክኖሎጂ ክፍል «ተዋሕዶ ለአንድሮይድ» የተሰኘ የቴሌፎን አገልግሎት መስመር ዘረጋ፡፡ አገልግሎቱ በተለይ የእጅ ስልካቸው ወይም የኪስ ኮምፒዩተራቸው /ታብሌት/ አንድሮይድ በተሰኘው ግብረ ቴክኖሎጂ /ኦፕሬቲንግ ሲስተም/ አማካይነት የሚሠራ ምእመናን በያሉበት ኾነው በቀላሉ ልዩ ልዩ ትምህርቶችን፣ መዝሙራትን፣ የዕለትና የበዓላት ንባባትን /ግጻዌን/፣ በድምጽና በምስል የቀረቡ መንፈሳዊ ትረካዎችንና ጭውውቶችን፣ ልዩ ልዩ የጸሎት መጻሕፍትን እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ በልዩ ልዩ ግዛቶች ስለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያደርስ ኾኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ 

 

 

ክፍሉ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳሳወቀው ቀደም ሲል ተመሳሳይ አገልግሎት አይ ፎንን መሠረት በማድረግ ሲጀምር ለምእመናን ቃል በገባው መሠረት፤ አገልግሎቱ በአንድሮይድ ግብረ ቴክኖሎጂም ይሰፋ ዘንድ የጀመረው መኾኑንgoogle play news 3 ገልጿል፡፡

ይህንን አገልግሎት ለማግኘት የሚሹና አንድሮይድ የተሰኘውን ግብረ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የእጅ ስልክ ወይም የኪስ ኮምፒዩተር ያላቸው ሁሉ አገልግሎት ማግኛ መንገዱን /አፕሊኬሽኑን/ ከጎግል ፕሌይ ስጥ ተዋሕዶ ከሚለውን የአገልግሎት ማዕቀፍ በመጫን መጠቀም እንዲችሉ ክፍሉ በአክብሮት ጋብዟል፡፡ ምእመናን ይህንን ጠቃሚ አገልግሎት ላልሰማ በማሰማት እንዲተባበሩም ጠይቋል፡፡