ሠለስቱ ደቂቅ
/in ለሕፃናት /by Mahibere Kidusan
ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም(ክፍል አንድ)
/in የቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት /by Mahibere Kidusanበኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የረጅም ዘመን ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ በጎ ተፅዕኖ ካላቸው የአራተኛው መ/ክ/ዘመን አባቶች መካከል አንዱ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ነው፡፡ይህ አባት ምንም እንኳን በቋንቋ ውሱንነትና በቦታ ርቀት በርካቶች ሥራዎቹና ጽሑፎቹ የታወቁለት ባይሆንም ሕይወቱን በብሕትውና የመራ የትርጓሜ መጻሕፍትን ፣የቅኔ፣ የግጥምና የወግ ጽሑፍ በማዘጋጀት የኖረ ባለ በጎ ገድል አባት ነው፡፡
ታቦት
/in ትምህርተ ሃይማኖት /by Mahibere Kidusan ትምህርት ሃይማኖት (የሃይማኖት ትምህርት) በሁለት ይከፈላል፡፡ ይኸውም፦
1ኛ፡- ዶግማ 2ኛ፡- ቀኖና በሚል ነው፡፡
ዶግማ፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም እምነት ማለት ነው፡፡
ቀኖና፡- ደግሞ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ ዶግማ ወይም እምነት አይጨመርበትም፤ አይቀነስበትም፤ አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምር እንጂ የማይመረመር ሁሉን ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገር የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔር ነው፡፡
ቃና ዘገሊላ
/in ስብከት /by Mahibere Kidusanየሃይማኖት አባቶች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን ወክለው ይቅርታ አቀረቡ።
/in ስብከት /by Mahibere Kidusanመ/ር መንግስተአብ አበጋዝ
የአራት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን የይቅርታ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት አቀረቡ።
ክፉ ለሚያደርጉባችሁ ሰዎች መልካምን አድርጉ::
/in ለሕፃናት /by Mahibere Kidusanበአንድ ወቅት ሳኦል የሚባል የእስራኤላውያን ንጉሥ ነበር፡፡ ይህ ንጉስ በዳዊት ላይ እጅግ ይቀናበት ነበር፡፡ ምክንያቱም ዳዊት ፍልስጤማዊው ጎልያድን ስላሸነፈ እስራኤላውያን በጣም ወደውት ነበር፡፡ ታዋቂም ሆኖ ነበር፡፡ ሳኦልም እግዚአብሔር እርሱን ትቶ ከዳዊት ጋር እንደሆነ ማሰብ ጀመረ፡፡ ስለዚህ በተለያየ ጊዜ ዳዊትን ለመግደል ሙከራ ያደርግ ነበር፡፡
በለንደን ያሉ ምእመናን ለቅዱሳት መካናት እርዳታ ሰጡ፡፡
/in ስብከት /by Mahibere Kidusanበዩናይትድ ኪንግደም ቀጠና ማዕከል
ለገዳማትና የአብነት ት/ቤቶች መርጃ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያና የምሳ መርሐ ግብር ኅዳር 12 ቀን 2003 ዓ.ም በለንደን ከተማ ተካሂዷል። ይህ ሪፖርት እስከ ተጠናቀረበት ኅዳር 27 /2003 ዓ.ም በጥሬ ገንዘብ £5,000.00 ፣በዓይነት አንድ የአንገት የወርቅ ሐብል እና አንድ የወርቅ የእጅ አምባር ሊገኝ ተችሏል።
ለቅዱስ ቁርባን ስለ መዘጋጀት
/in ለሕፃናት /by Mahibere Kidusanልጆች ልንቆርብ ስንል ምን ማድረግ እንዳለብን ታውቃላችሁ? የሠራነው ኃጢአት ካለ ለእግዚአብሔር እና ለንስሐ አባታችን መናገር አለብን፡፡ የተጣላነው ሰው ካለ ይቅርታ መጠየቅ፣ ውሸት አለመዋሸት አለብን፡፡ ሌላው ልጆች ገላችንን መታጠብና ንጹሕ የሆነ ልብስ መልበስ አለብን፡፡
በተሰደብክ ጊዜ
/in ስብከት /by Mahibere Kidusanይህ ሳሚ የተባለ ሰው ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ድንጋይ ይወረውርና ትቢያ ይበትን ነበር፡፡ ይህንን ተቃውሞ በሚያሰማበት ወቅት አንደበቱ አላረፈም ነበር፡፡ ይህ ሳሚ በቤተ ክርስቲያናችን የጸሎት መጻሕፍት ላይ በበርካታ ስፍራዎች በተራጋሚነቱ የሚወሳ ሲሆን በቅኔም ተሳዳቢ ሰውን ወክሎ የሚጠቀስ ነው፡፡ በሠራዊት ተከብቦ ያለውን ንጉሥ ዳዊትን ከፍ ዝቅ አድርጎ እየተሳደበና እየተራገመ ነበር፡፡ ‹‹ውጣ! አንተ የደም ሰው ምናምንቴ ሂድ! በፋንታው ነግሠሃልና እግዚአብሔር የሳኦልን ቤት ደም ሁሉ መለሰብህ፤ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ለልጅህ ለአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ እነሆም አንተ የደም ሰው ነህና በመከራ ተይዘሃል!›› እያለ የስድብ ናዳ አወረደበት፡፡