መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የደሴ ማእከል ቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል ስለቤተክርስቲያን ዘላቂ ልማት ከበጎ አድራጊዎች ጋር ውይይት አደረገ፡፡
የካቲት 28 ቀን 2006 ዓ.ም.
ወርቁ በላይሁን ደሴ ማእከል
የደሴ ማእከል ቅዱሳት መካናትና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል “ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት በጋራ እንሥራ” በሚል መርህ ለሁለተኛ ጊዜ ከደሴ ከተማ በጎ አድራጊዎች ጋር የካቲት 23 ቀን 2006 ዓ.ም ውይይት አደረገ፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው በጎ አድራጊዎች የተገኙ ሲሆን፤ ለዘላቂ የቤተ ክርስቲያን ልማት መሠራት ስለሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ውይይት ተደርጓል፡፡
ምኲራብ
የካቲት 27 ቀን 2006 ዓ.ም.
ታመነ ተ/ዮሐንስ
“ዘወትርም በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር” ሉቃ.19፥47
ምኲራብ የአይሁድ የጸሎት ቤት ሲሆን በብሉይ ኪዳን ዘመን የአይሁድ አምልኮ በኢየሩሳሌም በነበረው ቤተ መቅደስና በሥርዓቱ የተመሠረተ ነበር፡፡ ናቡከደነጾር ግን ቤተ መቅደሱን አፈረሰ ሕዝቡንም ወደባቢሎን አፈለሰ፡፡ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚገኙባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ለጸሎትና ለማኅበረተኛነት ልዩ ቤት ሊሠሩ እንደጀመሩ ይታሰባል፡፡ /የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት/
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በዓለ ሢመት ተከበረ::
የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
የብፁዕ ወቅደስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ 1ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የኢትዮጵያ አባት አርበኞች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ምእመናን በተገኙበት ተከበረ፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሚና በፀረ ቅኝ ግዛት ትግል” በሚል ርእስ ጥናት አቀረበ
የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሚና በፀረ ቅኝ ግዛት ትግል” በሚል ርዕስ በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ዋና ክፍል አዘጋጅነት በአቶ አለማ ሐጎስ አቅራቢነትና በአቶ አበባው አያሌው አወያይነት በማኅበሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የካቲት 22 ቀን 2006 ዓ.ም ቀረበ፡፡
ማእከሉ ወደ ሲሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጉዞ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የካቲት 20 ቀን 2006 ዓ.ም.
ከአርባ ምንጭ ማእከል
በማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል መራሔ ፍኖት በሚል መሪ ቃል ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መጋቢት 21 ቀን 2006 ዓ.ም ወደ ሲሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጉዞ ያዘጋጀ መሆኑን ገለጸ፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎቱን ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገለጸ፡፡
የካቲት 18 ቀን 2006 ዓ.ም.
በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ንዑስ ክፍል ለቤተ ክርስቲያን እና ለማኅበሩ አገልግሎት ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አሠራሮችን በቀላሉ ለማቅረብ የተቁዋቁዋመ ክፍል ነው። ይህ ክፍል ከ1999 ዓ.ም (2008) ጀምሮ በሰሜን አሜሪካ ከተቋቋመ ጀምሮ በርካታ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከንዑስ ክፍሉ ባገኘነው መረጃ መሠረት ክፍሉ፡-
ጥናትና ምርምር የጥናት ጉባኤው ሊያካሂድ ነው
የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
በታመነ ተ/ዮሐንስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሚና በፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል” በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሑፍ ሊያዘጋጅ ነው፡፡
«ተዋሕዶ ለአንድሮይድ» የተሰኘ የስልክ ላይ አገልግሎት ተጀመረ
የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
በዝግጅት ክፍሉ ሪፖርተር
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሚድያና ቴክኖሎጂ ክፍል «ተዋሕዶ ለአንድሮይድ» የተሰኘ የቴሌፎን አገልግሎት መስመር ዘረጋ፡፡ አገልግሎቱ በተለይ የእጅ ስልካቸው ወይም የኪስ ኮምፒዩተራቸው /ታብሌት/ አንድሮይድ በተሰኘው ግብረ ቴክኖሎጂ /ኦፕሬቲንግ ሲስተም/ አማካይነት የሚሠራ ምእመናን በያሉበት ኾነው በቀላሉ ልዩ ልዩ ትምህርቶችን፣ መዝሙራትን፣ የዕለትና የበዓላት ንባባትን /ግጻዌን/፣ በድምጽና በምስል የቀረቡ መንፈሳዊ ትረካዎችንና ጭውውቶችን፣ ልዩ ልዩ የጸሎት መጻሕፍትን እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ በልዩ ልዩ ግዛቶች ስለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያደርስ ኾኖ የተዘጋጀ ነው፡፡
ሐዊረ ሕይወት ወደ አዲስ ዓለም ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሊካሄድ ነው
የካቲት 14 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዲ/ን ቴዎድሮስ ኃይሉ
በዚህ ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ የታሰበው ሐዊረ ሕይወት ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን መጋቢት 21 ቀን 2006 ዓ.ም ሊካሄድ መሆኑን፤ የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ዋና ጸሐፊና የጉዞው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ተሾመ ገለጹ፡፡
ለአብነት መምህራኑ የህክምና ምርመራ ተደረገ፡፡ ክብካቤና ክትትል ካልተደረገ ለዐይነ ስውርነት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡
የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በቅርቡ ለሦስተኛ ጊዜ በማኅበረ ቅዱሳን አዘጋጅነት ሊካሄድ የነበረውን የአብነት መምህራን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከመጡት 202 ሊቃውንት ከ70 በላይ የአብነት መምህራን ካታራክት እና ትራኮማ ችግር እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡ክብካቤና ክትትል ካልተደረገ ለዐይነ ስውርነት ሊዳረጉ እንደሚችሉ የማኅበሩ የሞያ አገልግሎት ዋና ክፍል የሕክምና ቡድን ገለጸ፡፡