መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የመምህር አካለ ወልድ የሐዲስ ኪዳን የመጻሕፍት ትርጓሜ ት/ቤት የበግ ማድለብ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው
መጋቢት 9 ቀን 2007 ዓ.ም
ከደሴ ማእከል
በዝቋላ ገዳም የተቀሰቀሰው እሳት ለማዳፈን ጥረት እየተደረገ ነው
የካቲት 26 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ምኩራብ(የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)
የካቲት 20 ቀን 2007 ዓ.ም.
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡
በዝቋላ ገዳም የኢሬቻ በዓል እንደሚከበር በሚዲያ የተሰራጨው ዜና ማረሚያ እንዲሰጥበት ቅዱስ ፓትርያርኩ አሳሰቡ
የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም.
የዐቢይ ጾም ሳምንታት
የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም.
ቅድስት(የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ
ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኅበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ፡፡
ኩኑ ቅዱሳን እስመ ቅዱስ አነ” ዘሌ.19፡2
የካቲት 12ቀን 2007 ዓ.ም.
፲ቱ ማዕረጋት
ቅዱሳን ማለት የተቀደሱ፣ የከበሩ፣ የተመሰገኑ፣ የተለዩ፣ የተመረጡ፣ ንጹሐንየሆኑ፣ የጠሩ….. ወዘተ ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን በዚህ ስም የሚጠሩበት ከሰው ወይም ከምድራዊ ባለሥልጣን የተቸሩት አይደለም፡፡ በሃይማኖት ጸንተው በምግባር ጐልምሰው የሥጋ ምኞታቸውን ጥለው አፍርሰው ሲገኙ የቅድስና ባለቤት ቅዱስ እግዚአብሔር እነሱን /ቅዱሳንን/ መሣሪያ አድርጐ ኃይሉንና ሥልጣኑን ቢገልጽባቸው ማኅደረ እግዚአብሔር መሆናቸው ይገለጻል፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱሳን ይባላሉ፡፡
የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ባለ 4 ፎቅ ሁለገብ ህንጻ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስመረቀ
የካቲት 09ቀን 2007ዓ.ም.
ዲ/ን ያለው ታምራት
የዘወረደ ምንባብ (ዕብ.13÷7-17)
የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን መምህሮቻችሁን ዐስቡ፤ መልካም ጠባያቸውን አይታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትናና ዛሬ እስከ ዘለዓለምም የሚኖር እርሱ ነውና፡፡
የማቴዎስ ወንጌል
የካቲት 2 ቀን 2007 ዓ.ም.
ምዕራፍ ዐሥራ አራት
በዚህ ምዕራፍ፡-
1. ስለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አሟሟት
2. ጌታችን አምስት ሺሕ ሰዎችን ስለመመገቡ
3. ጌታችን በባሕር ላይ ስለመራመዱ እንመለከታለን
ሱባዔና ሥርዓቱ
መጋቢት 17 ቀን 2008 ዓ.ም
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
ሱባዔ ምንድን ነው?
ሱባዔ በሰዋስው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2፥2፤ መዝ.118፥64፡፡ ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም አንድ ሱባዔ ጾመÃÂ ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም ሁለት ሱባዔ ጾመÃÂ እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡