ዕንባ በንስሓ ሕይወት
በመንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ ዕንባ በብዙ ምክንያት ይፈጠራል፤ በየዋህነትና በልብ መነካት፣ የዓለምን ከንቱነት በመረዳት፣ ኃጢአትን በማሰብ፣ በፈተናና በችግር፣ ሞትን በማሰብ፣ በደስታና በስሜት፣ በጸሎት፣ በአቅመ ቢስነት፣ በብቸኝነት ስሜት፣ በሌላ ሥቃይ እና የሚታይ ፈንጠዚያ የተነሣ ሰዎች ያነባሉ፡፡በወንጌል በተጻፈው የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ታሪክ ውስጥ ለመግደላዊት ማርያም የቀረበላት ‹‹ስለምን ታለቅሻለሽ?›› የሚለውን የመላእክት ጥያቄም ሁላችን ልንመልስ ይገባል፤ ዕንባ ሁሉ ዋጋ የሚያስገኝ አይደለምና፡፡ (ዮሐ.፳፥፲፫)
በዚህ ዝግጅታችንም ኃጢአትን በማሰብ ለንስሓ የሚያበቃንን የዕንባ ዓይነት የፀፀትና የንስሓ ዕንባን እንመለከታለን፤ መልካም ንባብ!