ግሽን ማርያም
በሀገራችን ኢትዮጵያ በወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ የሚገኘው ታላቁ የግሸን ማርያም ደብር የግማደ መስቀሉ መገኛ በመሆኑ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ትልቅ ተስፋና መመኪያ ነው፡፡ መስቀል የክርስትናችን መገለጫ፣ የብርሃናችን ዐምድ እንዲሁም የሰላማችን መገኛ ነውና፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያ በወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ የሚገኘው ታላቁ የግሸን ማርያም ደብር የግማደ መስቀሉ መገኛ በመሆኑ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ትልቅ ተስፋና መመኪያ ነው፡፡ መስቀል የክርስትናችን መገለጫ፣ የብርሃናችን ዐምድ እንዲሁም የሰላማችን መገኛ ነውና፡፡
ጉባኤ ኒቅያ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን የጠበቀችበት፣ አርዮስና አርዮሳውያን የተወገዙበት፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት፣ አዳኝነት፣ ጌትነት፣ መድኃኒትነት የተመሠከረበት፣ ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ትምክህት የሆነበት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህን ጉባኤ ትቀበላለች፤ ትልቅም ስፍራ አላት፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋግሮ በሰላም ለዚህ ዕለት አደረሳችሁ! ዕንቁጣጣሽ እንዴት አለፈ? መቼም ደስ ብሏችሁ እንዳሳለፋችሁ ተስፋችን እሙን ነው፡። መልካም! የአዲስ ዓመት ትምህርት ለመጀመር እንዴት እየተዘጋጃችሁ ነው? ባለፈው ዓመት በትምህርታችን ደከም ያለ ውጤት አስመዝግበን የነበርን ዘንድሮ በርትተን በመማር በጥሩ ውጤት ከክፍል ክፍል ለመሻገር ከአሁኑ ማቀድና መበርታት አለብን፡፡ እንዲሁም ደግሞ ለአገርና ለቤተ ክርስቲያን እየጸለይን የሰላምን ዘመን ተስፋ እናድርግ! መልካም!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ባለፉት ጊዜያት ለእናንተ ያስተምራሉ በማለት በጻፍንላችሁ በርካታ ቁም ነገሮችን ስንማማር እንደነበር ታስታውሳላችሁ አይደል? አሁን ደግሞ ስለ ቅዱስ መስቀሉ በዓል ጥቂት ልናካፍላችሁ ወደድን፤ መልካም ቆይታ!
ሕዝበ ክርስቲያን ከሚያከብሩት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፴፫ቱ በዓላት አንዱ ጼዴንያ ማርያም በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመስከረም ፲ ቀን ይከበራል፡፡ በተለይም በሀገራችን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ቡራዮ አካባቢ ጼዴንያ ማርያም በምትባል ቤተ ክርስቲያን በዕለቱ ታቦተ ክብሩ ከመንበሩ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡ ጼዴንያ በምትባል ሀገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር ተገልጧልና፤ ይህችን ድንቅ ሥዕልም ቅዱስ ሉቃስ እንደሣላት ይነገራል።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የእንኳን አደረሳችሁ ቃለ በረከት!
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ያረፈበት ዕለት መስከረም ሁለት የተከበረ ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጥምቁን ክብር ‹‹እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም” በማለት መሥክሮለታል፡፡ (ማቴ. ፲፩፥፲፩፣ ሉቃ ፯፥፳፰)
አምላካችን እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍስሐ የሰጠን መልካም እንድንሠራበት ነውና በመጪው ዘመን የትላንት ስሕተታችንን አርመን፣ የተጣላን ታርቀን፣ የበደልን ክሰን፣ ያለው ለሌለው እያካፈለ ለመኖር ማቀድ ይገባናል!
ጳጉሜን ሦስት ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል በዓል በየዓመቱ ይታሰባል፤ ይከበራልም፡፡ መልአኩ የጦቢትን ዓይን ያበራና ወለተ ራጉኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው ጋኔን ያላቀቀ ነውና፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው፡፡ ደግሞም ከእስክንድርያ ውጭ በደሴት የታነጸች ቤተ ክርስቲያን በከበሩ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸበትና የከበረችበት ዕለት ነው፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር ለነቢዩ ኤርምያስ “በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ፤ ከማኅፀን ሳትወጣ ቀድሸሃለሁ” በማለት እንደተናገረ የገናናው ጻድቅ የአባታችን ተክለ ሃይማኖት ዜና ሕይወቱን እንዘክራለን፡፡ (ኤር.፩፥፭)
ከ፹ ዓመት በላይ በበረሃ የተጋደሉ፣ በአስቄጥስ ገዳም ፭፼ መነኮሳትን በመመገብ የመሩ፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ስለ ሥጋ ወደሙ ክብር ሲሉ ለ፷ ዓመት ምራቃቸውን ሳይተፉ የኖሩት ታላቁ አባት አባ መቃርስ በነሐሴ ፲፱ ፍልሰተ አጽማቸው ሳስዊር ከሚባል ሀገር ወደ አስቄጥስ የተፈጸመበት የከበረ በዓል ነው፡፡