ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? እንኳን ለወርኃ ክረምቱ አደረሳችሁ! በእግዚአብሔር ቸርነት፣ የተዘራው እህል በቅሎ ምድር ድርቀቷ ተወግዶ በአረንጓዴ ለምለም የምታጌጥበት ወቅት ነው፡፡ ለምድር ዝናምን ሰጥቶ፣ በዝናብ አብቅሎ፣ በነፋስ አሳድጎና በፀሐይ አብስሎ ፍጥረታቱን የሚመግብ የእግዚአብሔር ቸርነቱን እያወሳን ለምስጋና የምንተጋበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ የዕረፍት ጊዜያችን ለቀጣይ የትምህርት ዘመን እየተዘጋጀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር በመሄድ በርትተን፣ ውለታውን እያሰብን ለጸሎት ለቅዳሴ መትጋት አለብን!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና የእናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ታሪክ ነው፡፡