አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

‹‹ኮከበ ክብር ጽዱል ፀሐዬ አግዓዚ ብሩህ አቡነ ጊዮርጊስ ጥዑመ ስመ ወሠናየ ግዕዝ መጋቤ  ሃይማኖት ወመሠረተ ቤተ ክርስቲያን፤ አባታችን ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የሚያበራ የክብር ኮከብ፣ የኢትዮጵያ ብሩህ ፀሐይ፣ ስሙ የሚጣፍጥ፣ ምግባሩ የቀና ነው።›› (ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

ሁለቱ የቤተ ክርስቲያን አዕማዶች

ቅዱሳኑ ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ቃል ለዓለም የሰበኩ፣ ብዙዎችን በክርስትና ጥምቀትና በገቢረ ተአምራት ያዳኑ የቤተ ክርስቲያን አዕማዶች ናቸው፡፡

ልደቱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

ከካህን አባቱ ዘካርያስና ከቅድስት እናቱ ኤልሣቤጥ የተወለደው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የስሙ ትርጓሜ ‹‹ፍሥሐ፣ ሐሴት፣ ርኅራኄ›› ነው። የመወለዱም ነገር እንዲህ ነው፤ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በአምላኩ ትእዛዝ ወደ ዘካርያስ በመምጣት በመጀመሪያ በመሠዊያው በስተቀኝ በኩል ተገልጦ ታየው፡፡ ከዚያም ‹‹ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፤ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፡፡ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጅምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡…

ነቢዩ ኢያሱ ወልደ ነዌ

የነዌ ልጅ ኢያሱ የታላቁ ነቢይና መስፍን የነቢያት አለቃ የሙሴ ደቀ መዝሙር የነበረ በኋላም እግዚአብሔር የመረጠው ነቢይ ነው፡፡ የስሙ ትርጓሜም‹‹ እግዚአብሔር አዳኝ›› ማለት ነው፤ ‹‹የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው። ባሪያዬ ሙሴ ሞቶአል፤ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ። ለሙሴ እንደ ነገርሁት የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።…

ሐዋርያው ይሁዳ

በስመ ይሁዳ የሚጠሩ በርካታ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ተጠቃሾች ቢኖሩም በሰኔ ፳፭ ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የምታከብረው ሐዋርያው ይሁዳ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የሆነው የፀራቢው የዮሴፍ ልጅ እንዲሁም ያዕቆብ ለተባለው ሐዋርያ ወንድም ነው፡፡ አስቀድሞም ስሙ ታዴዎስ ይባል ነበር፡፡ ይህም ሐዋርያ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ያመነና በብዙ ሀገሮች የሰበከ ነው፤ ከእነርሱም መካከል በአንዲት ዴሰት ገብቶ በማስተማር በዚያ የነበሩትን ሰዎች በጌታችን ስም አሳምኖ ቤተ ክርስቲያን እንደሠራላቸውና በቀናች ሃይማኖትም አጽንቷቸዋል፡፡

‹‹ሙሴ ሆይ፥ እነሆ በውስጥም በውጭም ሁለመናህ ነጭ ሆነ››

ሰዎች ከገድሉ የተነሣ የሚያደንቁት ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባት አባ ሙሴ ጸሊም አስቀድሞ ለሥጋው የሚኖር ወንበዴና አመንዛሪ እንዲሁም ቀማኛ ነበር፡፡ እንዲያውም የሥጋውን መሻት ለመፈጸም ሰዎችን እስከ መግደል የሚደርስ ጨካኝ ሰው እንደነበር ገድሉ ይናገራል፡፡ መብልንና መጠጥንም ከልክ ባለፈ መልኩ ይወስዳል። መጽሐፈ ስንክሳር ላይ እንደተመዘገበው በአንድ ጊዜ አንድ ሙሉ በግ እና አንድ ፊቅን ወይን ጠጅ እንደሚጨርስ እራሱ ይናገር ነበር፡፡

‹‹ከአንተ በፊትም ከአንተ በኋላም የሚመስልህ የለም›› (፩ኛነገ.፫፥፲፪)

የጠቢቡ ሰሎሞን ጥብብ መደነቅና ተሰሚነት በሰዎች ዘንድ ብቻ አልነበረም፤ ‹‹አራዊትና ወፎች ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ፣ ቃሉን ይሰሙ፣ ጥበቡንም ያደንቁ፣ ከእርሱ ጋር ይነገጋሩና ወደ ሥፍራቸው ይመለሱ ነበር፡፡››

የቅዱሳንን ገድል የመማር አስፈላጊነት

የቅዱሳንን ገድል ለምን እንደምንማር ለማወቅ ቅዱሳት መጻሕፍት ላይ የተጠቀሱትን ታሪኮች ምሳሌ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በቃሉ የተናገረላቸው ቅዱሳን ስለመኖራቸው በቀዳሚነት መጽሐፍ ቅዱስ ተጠቃሽ ነው፡፡

ቅዱስ ላሊበላ

ቅዱስ ላሊበላ ከአባቱ ዣን ስዩምና ከእናቱ ኪርወርና በታኅሣሥ ፴፱፣ ፲፻፩ ዓ.ም በላስታ ቡግና ወረዳ ልዩ ስሟ ሮሀ በተባለችው ሥፍራ ተወለደ፡፡ አባቱ በላስታ አውራጃ የቡግናው ገዢ ነበር፤ እናቱ ደግሞ አገልጋይ ነበረች፡፡ የልደቱን ነገር አስቀድሞ ቅዱስ ሚካኤል ለእናቱ ነግሯት ነበር፤ ቅዱስ ላሊበላ በተወለደ ጊዜም ብዙ ነጫጭ ንቦች መጥተው በሰውነቱ ላይ አርፈው እንደ ማር እየላሱት ስለታዩ እናቱ ‹‹ልጄን ንብ ዘበኛ ሆኖ ይጠብቅልኛል›› ስትል ስሙን ‹‹ላል ይበላል›› ብላዋለች፡፡ ‹ላል› በአገውኛ ‹ንብ› ማለት ነው፡፡ በጊዜ ብዛት በተለምዶ ነው ‹‹ላሊበላ›› ተብሎ መጠራት ተጀመረ፡፡ ንቦቹ ግን ሥጋዊ ንቦች ሳይሆኑ በንብ የተመሰሉ መላእክት ናቸው፡፡ ንጉሥ መሆኑን እያመለከቱ ሃይማኖትና ምግባር ማር ከእርሱ እንደሚቀዳ ለማመልከት በንብ ሠራዊት ተመስለው ሰውነቱን ላሱት፡፡

ቅዱስ ገላውዴዎስ

የሮሙ ንጉሥ የኑማርያኖስ ወንድም ከሆነው አባቱ አብጥልዎስ የተወለደው ገላውዴዎስ የመላእክት አርአያ የተባለ ቅዱስ ነው፡፡ የአንጾኪያ ሰዎችም አባቱን እጅግ ይመኩበትና ይወዱት ነበረ፤ በሕይወት እያለም በጦርነት ድል ሲያደርግ የሚያሳይ ሥዕሉን በከተማው ላይ አሠርተው ያከብሩት ነበር፤ ልጁ ቅዱስ ገላውዴዎስ ግን የቤተ ክርስቲያንን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር ያነብ ነበር፡፡