ደብረ ምጥማቅ
ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሠራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩ ጀምሮ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሏን ያከብራሉ፡፡
ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሠራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩ ጀምሮ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሏን ያከብራሉ፡፡
ዓለም አንድ መንደር ለመገንባት የሚያደርገውን ሩጫ ባፋጠነበት በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያውያን በችግሮቻችን የተነሣ መለያየታችን እየባሰ በመሆኑ ሥቃያችን፣ ሞታችን፣ ስደታችንና መከራችን እየበዛ ነው፡፡ የመለያየቱ ጡዘት ሞትን እንጂ ሕይወትን፣ ማጣትን እንጂ ማግኘትን፣ ውርደትን እንጂ ክብርን አላመጣልንም፡፡ በመለያየት የዓለም ጅራት እንጂ ራስ አልሆንም፡፡ መለያየት ኋላ ቀርነትን እንጂ በረከትን ይዞልን አልመጣም፡፡ በመገዳደል ጠላትን ማሸነፍ ወይንም ድል ማድረግ አይቻልም፡፡ በመጻሕፍት እንደተማርነው ገድለው የወረሱ በጊዜ ሂደት ውስጥ ተገድለው ተወርሰዋል፡፡ ቆም ብለን ማስተዋል እስካልቻልን ድረስ ወደ ፊትም ይህ እውነት ይቀጥላል፤ አይቆምም፡፡
…ከዚያም ጉዞውን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ ሰሜን ተራሮች አደረገ፡፡ በዚያም አሁን በስሙ የታነጸው ቤተ ክርስቲያን ባለበት ቦታ ላይ በምናኔ ተወስኖ ፈጣሪውን በብሕትዉና እያገለገለ ኖረ፡፡ ደብረ ሐዊ ከተባለው ተራራ ላይ በምናኔ ብዙ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ በጸለምት ዋሻ በአንዱ ግንቦት ፲፩ ቀን በ፭፻፸፩ ዓ.ም ተሠውሯል፡፡
በዕለተ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ በመንፈቀ ሌሊት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ከመቃብር ተነሣ፤ ነቢዩ ዳዊትም ‹‹እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ›› ብሎ እንደተናገረው አምላካችን ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶአል፡፡ ትንሣኤ ሙታንን እናከብርም ዘንድ ይገባልና ክርስቲያኖች በሙሉ ደስ ይበለን! (መዝ. ፸፯፥፷፭)
በዚህ ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ በሙሉ ያደረገውን ትድግና ቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም ግብረ ሕማማት የተባለው የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ ነገረ ሕማማቱን መከራ መስቀሉን በሰፊው ይናገርለታል፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም መድኃኒታችን ክርስቶስ አንዳች በደል ሳይኖርበት በሰውነቱ የደረሰበትን ሕማሙንና መከራውን ሞቱንም እያሰብን ይህንን የዐቢይ ጾምን መጨረሻ ወቅት ወይም ስምንተኛውን ሳምንት በካህናቱ መሪነት ሁላችን ምእመናን በተረጋጋ ኅሊና አብዝተን በመጾም፣ በመጸለይና በመስገድ እንድናከብር ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ሁሉ ይህንን የጌታን የሕማማት ሰሙን ከተድላ ከደስታ በመራቅ ነገረ መስቀሉን እያሰቡ በኀዘንና በልቅሶ ሆነው የሚያሳልፉት፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን ወዶ እና ፈቅዶ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ለሆነው የነነዌ ጾም አድርሶናል፡፡ ሦስት ቀናት የሚጾመው ይህ ጾም የነነዌን ሕዝብ ከጥፋት መመለስ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዲሁም የነቢዩ ዮናስን የዋህነት ያስረዳናል፡፡
ስእለት ማለት ልመና፣ ምልጃ፣ ጸሎት፣ ጥየቃ እንደሆነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት ሐዲስ ገልጸዋል፡፡ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ስእለት ይሳላሉ፡፡ ለምሳሌ ‹‹እግዚአብሔር የልቤን ጭንቀት ቢፈጽምልኝ እንዲህ አደርግለታለሁ፡፡ እመቤቴ ማርያም ስእለቴን ወይንም ልመናዬን ብትሰማኝ ለቤተ ክርስቲያን እንዲውል ጃን ጥላ አስገባለሁ›› ብለው ይሳለሉ፤ ወይንም አቅማቸው የፈቀደውን ነገር እንደሚሰጡ ቃል ይገባሉ፡፡ ስእለታቸውም ሲደርስ ‹‹እመቤታችን እንዲህ አድርጋልኛለች›› ብለው ለክብሯ መገለጫ ድባብ ወይንም የተሳሉትን ነገር ለቤተ ክርስቲያን ይሰጣሉ፡፡(ገጽ ፰፻፵፪)
በእግዚአብሔር ተስፋ መኖር በእርሱ ላይ ሙሉ እምነት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር ከጎናችን ሲሆንም እያንዳንዳችን ከምናስበው ዳርቻ መድረስ እንችላለን፡፡ ስለዚህ ተስፋችን የሚወሰነው በአምላካችን ላይ ባለን የእምነት ጥንካሬ ነው፡፡ ተስፋ በሕይወታችን ውስጥ ወደፊታችን የምንራመድበት መወጣጫ ድልድይ፣ የኑሮአችን መሠረት እንዲሁም የደስታችን መጀመሪያ ነው፤ በተስፋ ኖረን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት እንሸጋገራለንና፡፡