“በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ” (ትንቢተ ዮናስ ፪፥፫)

በመጀመሪያ ራሳችን “በደለኛው እኔ ነኝ፤ ኃጢአተኛ ነኝ፤” ብለን አምነን መጸጸት አለብን፤ ጸጸትም ወደ ንስሓ ይመራናል፡፡ እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውና ውስጣችንን ከክፋት ሳናነጻ በሐሰተኛ አንደበት በንጸልይና ምሕረትን ብንለመን ልመናችንን አይቀበለንም፤ ሁሌም እርሱን በመፍራት መኖር እንዳለብን ቃሉ ይገልጻል፤ “ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር” (መጽሐፈ ምሳሌ ፳፫፥፲፯) እንደተባለው እግዚአብሔርን አምላክን በንጹሕ ልቡና ልንማጸን ይገባል፡፡

“የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ” (ገላ. ፮፥፪)

የክርስቶስ ሕግ ፍጻሜ ፍቅር ነው። ፍቅር አንድ ሰው ከሌላው ጋር በየዕለቱ የሚያደርገው ግንኙነት፣ በመተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ልባዊ መዋደድና ጥልቅ መንፈሳዊ ጸጋ ነው። በሰዎች መካከል በሚኖረው መልካም ግንኙነት የተነሳ አንዱ ለሌላው የሚያደርገው መልካም ነገር ሁሉ ፍቅር ነው።

“ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” (ሉቃ.፩፥፵፰)

እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምናመሰግናት ስለተሰጣት ጸጋ እና ክብር ነው። የተሰጣት ክብር ደግሞ ከጸጋ ባለቤት ከልዑል እግዚአብሔር መሆኑን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ስለ ተሰጣትም የእግዚአብሔር ጸጋ የሔዋን መርገም በእርሷ ላይ ተቋረጠ እንዲህ ያለ ስጦታ ለአዳም እና ለዘሩ እስከ ዘለዓለም ለሌላ አልተሰጠም።›› በዚህ ብቻ ሳይሆን ስለ ንጽሕኗዋ፣ ስለ ቅድስናዋ ጭምር ምስጋና እናቀርባለን ።

“ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ቅዱስ ያሬድ)

በመጻሕፍት አምላካውያት (አሥራው መጻሕፍት) እና በሊቃውንት አበው አስተምህሮ የተነገሩ የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕናዋን ቅድስናዋን የሚመሰክሩ መውድሳት ቅኔያትና ዝማሬያት እንዲሁም በሰፊው የተገለጡትን ምስክርነቶች ስንመለከት እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ የተገኙ እንዳልሆነ አስተዋይ ሰው በቅጥነተ ሕሊና ቢረዳው የሚያውቀው እውነት ነው፡፡

“ጽና፥ እጅግም በርታ” (መጽሐፈ ኢያሱ ፩፥፯)

እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጅ አብዝቶ ሲበድል ሌላ ጊዜ ደግሞ የሰውን ልጅ ለበለጠ ዋጋ ማዘጋጀት ሲፈልግ መቅሰፍትን ወደ ምድር ይልካል፡፡ በበደል ምክንያት የሚመጣው መቅሠፍት አሁን ዓለምን እያስጨነቀ ያለው ኮሮና በሽታ አይነት ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ሰዓት እኛም በክርስቶስ ክርስቲያን የሆንን የክርስቶስ ልጆች እንደመሆናችን መጠን በጾም በጸሎት ይህን የመከራ ጊዜ ልናንልፍ ይገባል፡፡

‹‹ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና›› /ኦ.ዘፀ.፲፭፥፳፮/

ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ነች፤ ስለዚህ ይህን የአምልኮተ እግዚአብሔር ሥርዓት ተጠቅሞ በሽታውን መከላከል አዋቂነት እንጅ ቂልነት አይደለም፤ ለሌሎች ሀገራትም ይህን መልእክት ማስተላለፍ ይገባል፡፡

‹‹ታጠቡ ንጹሐንም ሁኑ›› /ት.ኢሳ. ፩፡፲፮/

ኮሮና ቫይረስ ዓለም አቅሙን ያወቀበት ነው፡፡ በዚህ ወቅት  ከበሽታና ከሞትም ለመዳን ራስን በንጽሕና መጠበቅ፣ በነፍስ በኩል ደግሞ ከኃጢአት ራስን ማንጻት ያስፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ  በመንፈሳዊ ሕይወት በሰላም ለመኖር ራስን ማንጻት እንደሚገባ ቅዱስ ቃሉ ያስተምረናል፡፡

‹‹ታጠቡ ንጹሐንም ሁኑ›› /ት.ኢሳ. ፩፡፲፮/

ቤተ ክርስቲያን የግል ንጽሕናንና የአካባቢ ንጽሕናንም መጠበቅ እንደሚገባ የጤና ሥርዓት ሳይዘረጋ በቀድሚነት አስተምራለች፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ታጠቡ ንጹሐንም ሁኑ፤ የሰውነታችሁን ክፋት ከዐይኖቼ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግንም ተው፤ መልካም መሥራትንም ተማሩ›› /ት.ኢሳ. ፩፡፲፮/ እንዲል የሥጋንም የነፍስንም ንጽሕና መጠበቅ ክርስቲያናዊ መመሪያ ነው፡፡

ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ

ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ባሉት ዕለታት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ሥርዓት ኾኖ ይከናወናል፡፡ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ እሑድ ድረስ የሚገኙት ዕለታትም ‹ሰሙነ ፋሲካ› ወይም ‹ትንሣኤ› እየተባሉ ይጠራሉ፤ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡

ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን)

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡