ክርስቲያናዊ አንድነት

ክርስቲያናዊ አንድነት በእምነት አንድነትና በአስተምህሮ ስምምነት የሚገለጥ ነው፡፡ በዚህም በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን ሰዎች የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በማመን፣ ከሀብተ መንፈስ ቅዱስ በመወለድ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል በአጠቃላይ ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመገዛት መኖር ማለት እንደሆነ እንረዳለን፡፡

‹‹የሰው ሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል›› (መዝ. ፻፵፬፥፲፭)

ተስፋ ሲኖረን የነገን ለማየት እንናፍቃለን፤ ዛሬ ላይም በርትተን ለመጪው እንተጋለን፤ የመልካም ፍጻሜችንም መድረሻ በተስፋችን ይሰነቃልና፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ። ቀኝ እጅህን ትዘረጋለህ፤ በሥርዓትህ ለሚኖሩ እንስሳ ሁሉ ታጠግባለህ፡፡  እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው፤ በሥራውም ሁሉ ቸር ነው። እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል፥ ያድናቸዋልም። እግዚአብሔር የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ ኃጢአተኞችንም ሁሉ ያጠፋል›› በማለት ገልጿል፡፡ (መዝ. ፻፵፬፥፲፭-፳)

የነቢያት ጾም

በዘመነ ብሉይ ነቢያት እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን፤ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ለአዳም የገባለትን ቃል ይፈጽም ዘንድ ትንቢት በመናገር ለሕዝቡ የምሥራችን ቃል ያበሥሩ ነበር፡፡… ነቢያቱ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ሆኖ ዓለምን የሚያድንበትን ዘመነ ሥጋዌ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መሆን ተፈጽሟል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ታሳቢ በማድረግ በዘመነ ማቴዎስ፣ ማርቆስና ሉቃስ፤ ከኅዳር ፲፭ አስከ ታኅሣሥ ፳፱፤ በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ እስከ ታኅሣሥ ፳፰ ጾም ታውጃለች፡፡

በዓለ ሢመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል

ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት፤ በኃይላት ላይ የተሾምክ ሚካኤል› ሲል ያመሰገነው ቅዱስ ሚካኤል በኃይላት መላእክት ላይ የተሾመ ሊቀ መላእክት እንደመሆኑ በዓለ ሢመቱ ኅዳር ፲፪ ቀን በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል፡፡

«ስለ ሰላም ጸልዩ» (ሥርዓተ ቅዳሴ)

ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ እጅጉን ከሚያስፈልገን ነገር ዋነኛው ሰላም ነው፡፡ ያለ ሰላም መኖር አይቻልንም፡፡ ሰላም የተረበሹትን ያረጋጋል፤ ያዘኑትን ያጽናናል፤ ጦርነትን ወደ ዕርቅ ይለውጣል፡፡

በዓለ ደብረ ቁስቋም

ከሦስት የስደት እና መከራ ዓመታት በኋላ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ዮሴፍንና ሰሎሜን አስከትላ ወደ ግብፅ ስትሰደድ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቊስቋም ላይ ያረፉበችበት ኅዳር ፮ ቀን ይከበራል፡፡

ርእዮ ለይብኪ ዐይነ ልብ ዘቦ (ሰቈቃወ ድንግል)

አባ ጽጌ ድንግል ይህን ቃል የተናገረው የቅድስት ድንግል ማርያምን ስደቷን፣ በስደቷ ጊዜም የደረሰባትን መከራና ኃዘን አምልቶ በገለጸበትና አምላክን በኅቱም ድንግልና ፀንሳ በኅቱም ድንግልና የወለደች ድንግል ማርያምን ባመሰገነበት ክፍሉ ነው። ሙሉ ቃሉን እንደሚከተለው እንመልከተው።…

ምኞት

ሰው አንድን ነገር የራስ ለማድረግ በብርቱ ፍላጎት ወይንም ምኞት ይነሣሣል፤ በመልካም ምኞቱ የነፍስ ፍላጎትን ሲፈጽም የሥጋዊው ግን ወደ ጥፋት ይመራዋል፡፡ ሥጋዊ ምኞት በመጀመሪያ ጊዜያዊ ደስታን ቢሰጥም ፍጻሜው ግን መራራ ኅዘንን የሚያስከትል ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም ይህን በምሳሌው እንዲህ ሲል ገልጾታል፤ ‹‹የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ የኃጥአን ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው›› (ምሳሌ. ፲፩፥፳፫)

‹‹እመን እንጂ አትፍራ›› (ማር. ፭፥፴፮)

የደኅነታችን መሠረት እምነት በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ችግርና መከራ በበዛብን ጊዜ ጸንተን እንድናለፍ ይረዳናል፡፡ የሰው ዘር በኃጢአቱ የተነሣ በምድር እንዲኖር ከተፈረደበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ችግርና መከራ ተይዞ ሲሠቃይ ፈጣሪውን ያስባል፤ ይማጸናልም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፈውስን ሲያገኝ በሌላ ጊዜ ግን ወደማይመለስበት ዓለም በሞት ይለያል፤ ሆኖም ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ከአምላካችን እናገኝ ዘንድ እምነት ያስፈልጋል፡፡

‹‹የሞተ ሰውስ ዐረፈ፤ ነገር ግን መታሰቢያውን አድርግለት›› (ሲራክ ፴፰፥፳፫)

ሰዎች ሕያው ሆነን በፈጣሪ አምሳል እንደተፈጠርነው ሁሉ በኃጢአት ሳቢያ የተፈረደበትንን ሥጋዊ ሞት እንሞት ዘንድ አይቀሬ ነው፤ ‹‹አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህና›› እንደተባለውም የሰው ዘር በሙሉ ወደ አፈርነት ይመለሳል፡፡ በሕፃንነትም ይሁን በጎልማሳነት እንዲሁም በእርጅና ሰዎች ይሞታሉ፡፡ በበሽታ፣ በአደጋ ወይንም በግድያ የሰዎች ሕይወት በየጊዜው ይቀጠፋል፡፡ በተለይም በዚህ ትውልድ ዓለማችን በየጊዜው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አያጣች ነው፡፡ በእርስ በርስ ግጭትና ጦርነት እንዲሁም የሰዎችን ሕይወት እንደ ቅጠል እያረገፈ ባለው ኮሮና በሽታ እጅግ ብዙ ሰዎች ሞተዋል፡፡