ጥምቀት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮርዳኖስን ብርህት ማኅፀን እንድትሆን፣ ምእመናንም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግም ተወልደው መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ እንደዚሁም ሥርዓተ ጥምቀትን ለማስተማርና አብነት ለመሆን በጥር ዐሥራ አንድ ቀን ተጠምቋልና ይህችን የተከበረች ቀን ሕዝበ ክርስቲያን ያከብር ዘንድ ይገባል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮርዳኖስን ብርህት ማኅፀን እንድትሆን፣ ምእመናንም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግም ተወልደው መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ እንደዚሁም ሥርዓተ ጥምቀትን ለማስተማርና አብነት ለመሆን በጥር ዐሥራ አንድ ቀን ተጠምቋልና ይህችን የተከበረች ቀን ሕዝበ ክርስቲያን ያከብር ዘንድ ይገባል፡፡
በትዳር ሕይወት ስንኖር ባል ራስ ነውና ሚስቶች ለባሎቻቸው እንዲገዙና እንዲታዘዙ ሲያዛቸው፣ ለባሎች የሰጠው ትእዛዝ ደግሞ ከዚህ የጸና ትእዛዝ ነው። ይኸውም የገዛ ሕይወቱን አሳልፎ እስኪሰጥላት ድረስ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንደወደዳት ባልም እንዲሁ ሚስቱን እንዲወዳት ጽኑዕ ትእዛዝን አዟል። ታዲያ ከመታዘዝና ከመገዛት ይልቅ ምን ያህል የሚጸና እንደሆነ ልናስተውለው ይገባል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን በፍቅር ሞቷል እና ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ ትገዛለች፤ በተመሳሳይ ፍቅር ምክንያት ‹‹ሚስቶች ሆይ፤ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁም ተገዙ፤ ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስዋ እንደሆነ ሁሉ፣ አዳኝዋም እንደ ሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና፡፡
ኢየሩሳሌም ከተማ ከወትሮው በተለየ መልኩ የፍርሃት ድባብ ተንጸባርቆባታል፤ በንጉሥ ሄሮድስ ቤተ መንግሥት ዙሪያ በሠራዊቱና በቤተ መንግሥቱ የቅርብ ሰዎች የሰሞኑ ወሬ የሦስቱ ነገሥታት ጉዳይ ነው፡፡ ከሩቅ ምሥራቅ ሠራዊቶቻቸውን አስከትለው የመጡት ማንቱሲማር፣ በዲዳስፋ፣ እና ሜልኩ የተባሉ ነገሥታት በእስራኤል ምድር መምጣታቸው ብቻ ሳይሆን ተወልዷል ለተባለው ንጉሥ እጅ መንሻ ለመስጠት እንደመጡ መናገራቸው ንጉሥ ሄሮድስን ቅር አሰኝቶታል፤ ፍርሃት በልቡ እንዲነግሥም አድርጎታል፡፡…
ጥበብ ከእግዚአብሔር አምላክ የሚሰጥ፣ ከሁሉ የበለጠና የላቀ የዕውቀት ሥጦታ እንዲሁም ሰማያዊ ርስትን የሚያወርስ መንፈሳዊ ጸጋ ነው፡፡ በሰዎች አእምሮ ውስጥም ማስተዋልን ያጎናጽፋል፡፡ በዚህም ጸጋ የእውነት መንገድን ማወቅና ጽድቅን መሥራት ይቻላል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን በምሳሌው እንደተናገረው ‹‹ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፤ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው ዕውቀትን ያበዛል፡፡›› (ምሳ. ፱፥፱)
በዓለም የምናያቸው መልካምም ሆኑ ክፉ ነገሮች ሁሉ መነሻቸው ሐሳብ መሆኑን ስናስተውል ኅሊና ምን ያህል ታላቅ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ኅሊና የሚለው ቃል ‹ሐሳብ፣ ምኞት፣ ከልብ የሚመነጭ ሐሳብ› ማለት ነውና፡፡ በሰው ልጆችም የአእምሮ ሥራ ሂደት ውስጥ ሐሳብ ሲደጋገም ወደ አመለካከት፣ ከሐሳብ የተነሣ አመለካከት ሲያድግም ክፉ ወይም በጎ ወደ ሆነ ማመን፣ አንድ ሰው ከሐሳቡ ወደ ማመኑ የደረሰበት መንገድም ማንነቱን እንደሚወስኑት ባለሙያዎች ያስተምሩናል፡፡ ከሐሳባችን ተነሥቶ ወደ ማንነታችን የደረሰ ነገርም ፍጻሜያችንን ይወስነዋል፡፡…
ሰዎች አንደበታችንን እግዚአብሔርን ለማመስገንና በጎ ነገርን ለመናገር ልንጠቀመው ይገባል። በእያንዳንዱ ንግግራችን የምናወጣቸው ቃላትም ሆነ የምንመሠርታቸው ዓረፍተ ነገሮች ከክፋት የጸዱ መሆን አለባቸው። ለዚህም ነው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ›› በማለት የተናገረው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በጾመ ድጓው ሲናገር ‹‹ይጹም ዐይን ይጹም ልሳን እዝንኒ ይጹም እምሰሚዐ ሕሡም፥ ዐይን ይጹም፣ አንደበትም ይጹም፣ ዦሮም ክፉን ከመስማት ይጹም›› ብሎ እንደተናገረ አንደበት በቃለ እግዚአብሔር እና በበጎ መንፈሳዊ ምግባራት ካልተገታችና ካልታረመች የሰውን ልጅ ወደ ጥልቅ የበደልና የጥፋት መንገድ ሊጥሉት ከሚችሉ ሕዋሳት አንዲቱ ናት። (መዝ.፴፫ (፴፬)፥፲፫)
ጭንቀት እንደ የማኅበረሰቡ አኗኗርና የኑሮ ፍልስፍና የሚሰጠው ትርጉም ከቦታ ቦታና ከሰው ሰው ይለያያል። የሕዝቦቻቸው መሠረታዊ ፍላጎቶች ባልተሟሉባቸው አንዳንድ ሀገራት ምጣኔ-ሀብታዊ አለመረጋጋት በብዛት የሚስተዋል የጭንቀት መንሥኤ ነው። በአንጻሩ ብዙዎቹ ዜጎቻቸው የቅንጦት ሕይወት በሚመሩባቸው ‹ሥልጡን› ሀገራት ደግሞ፥ ደስታ ይገኝባቸዋል ተብለው የሚጀምሩ የዝሙት፣ የሱስ፣ የዘፈን… የመሳሰሉት እኩይ ተግባራት ከጊዜያት በኋላ እግዚአብሔርን ፍለጋ በሚቃትተውና እውነተኛ ደስታ ምን ማለት እንደሆነ አንጠርጥሮ በሚያውቀው ውሳጣዊ ኅሊናቸው ዕረፍት የለሽ ሙግት የተነሣ ደስታ ሰጪነታቸው አብቅቶ መዳረሻቸው ጭንቀት ይሆናል። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ለዚህ ኅሊናዊ ምሪት የሚሰጡት መልስ በአብዛኛው አሁንም ተቃራኒውን መሆኑ ነው። ‹‹ለምንድነው የምኖረው?›› ለሚለው ጥያቄያቸው መልሳቸው ‹‹ለምንም!›› የሚል ይሆንና የሕይወታቸውን ፍጻሜ ያበላሸዋል።…
ወገንተኝነትን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስንገነዘበው ለወገን፣ ለዘመድ፣ ለጓደኛ፣ ወይም የራስ ለሚሉት አካል ማድላት ነው፡፡ አያሌ ተቋሟት ዓላማና ግቦቻቸውን በሚገልጡበት ጊዜ ከሚያስቀምጡዋቸው ዕሤቶቻቸው መካከል አንዱ አለማዳላት ነው፡፡ አለማድላት ደግሞ ወገንተኝነትን የሚኮንንና ፍጹም ተቃራኒው የሆነ ታላቅ ዕሤት ነው፡፡ ወገንተኝነት ወገኔ ለሚሉት አካል ጥፋት ሽፋን በመስጠት ይገለጣል፡፡ ቆሜለታለሁ ለሚሉትም አላግባብ ቅድሚያ መስጠት ሌላኛው መገለጫው ነው፡፡
‹‹አይሁድ ይክዱታል፤ እኛ ግን እናምነዋለን፤ ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን፤ ድነናልም››